Monday, December 24, 2012

የግንቦት7 ህዝባዊ ሐይል ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ




ኢሳት ዜና:-የድርጅቱ ቃል አቀባይ ታጋይ ዜና ጉታ ለኢሳት እንደገለጠው ከትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ወይም ደሚት፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ ፍትህና እኩልነት ግንባር፣ ከጋምቤላ ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፣ ከቤንሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ እንዲሁም የአማራ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ከተባሉት ድርጅቶች ጋር በጥምረት ለመስራት አስፈላጊው ዝግጅት አጠናቋል።ታህሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ታጋይ ዜና ጉታ ህዝባዊ ሀይሉ በዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ከሚመራው የግንቦት7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ጋር ግንኙነት እንዳለው ጥያቄ ቢቀርብለትም አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።

No comments:

Post a Comment