Wednesday, October 2, 2013

ግንቦት 7 ዋሽንግተን ዲሲ ዉስጥ ትልቅና የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ አካሄደ


ግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ባለፈዉ እሁድ መስከረም 13 ቀን 2006 ዓም አሜሪካዋ መናገሻ ከተማ ዋሽንግተን ዲሲ ዉስጥ ስብሰባ አካሂዶ በተለያዩ ህዝባዊ ትግሉንና ንቅናቄዉን በተመለከቱ ጉዳዮች ዲሲ፤ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ ዉስጥ ከሚኖሩ አያሌ ኢትዮጵያዉያን ጋር ሲመክር መዋሉን ዋሽንግተን ዉስጥ የሚገኙ የንቅናቄዉ ቃል አቀባዮች ተናገሩ። በዚህ የንቅናቄዉ ሊ/መንብር ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ፤ ዋና ጸሀፊዉ አቶ አንድአርጋቸዉ ጽጌና የህዝብ ግኑኝነት ዘርፍ ሀላፊዉ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ በተገኙበት ስብሰባ ላይ ጋ ጥሪ የተደገላቸዉ አንግዶቸ፤ ዜጠኞችና የተለያዩ ፓርቲና ሲቪክ ድርጅት መሪዎችና ተወካዮች የተገኙ ሲሆን አቶ አንዳርአቸዉ ጽጌና ዶ/ር ብርሐኑ ነጋ ከህዝብ ለቀረበላቸዉ በርካታ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ሰጥተዋል። የዕለቱን ስብሰባ በተላያዩ የፓልቶክ መወያያ መድረኮች ቁጥሩ ከ3500 በላይ የሆነ ሰዉ የተከታተለዉ ሲሆን አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌና ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ከፓል ቶክ ለቀረበላቸዉ ጥያቁም መልስ ሲሰጡ ዉለዋል።
የእለቱን ስብሰባ የመሩት የንቅናቁዉ የህዝብ ግኑኝነት ዘርፍ ሃለፊ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ስብሰባዉን በንግግር ሲከፍቱ ባሰሙት ንግግር ግንቦት 7 ብዙ ግዜ ከተገንጣዮች ጋር ይደራደራል ተብሎ በተደጋጋሚ የሚነሳዉን ክስ አስመልክተዉ ሲናገሩ ከተገንጣይ ኃይሎች ጋር እንመክራለን እንደራደራለን፤ ለምን ቢባል እነሱም እንደማናችንም ኢትዮጵያዉያን ናቸዉ ብለን እናምናለን፤ ደግሞም ትናንት በጡንቻችን ተማምነን በኤርትራ ጉዳይ ላይ የሰራነዉን ስህተት መድገም አንፈልግም። የምናወራዉ ስለ አንድነታችን ከሆነ፤ የምናዉራዉ ስለሁሉን አቀፍ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ከሆነ፤ የምናወራዉ ስለዘላቂ የአገራችን ሰላም ከሆነ መደራደርና መወያየት ያለብን ከወዳጆቻችን ጋር ሳይሆን የአገራችንን አንድነትና ሰላም አደጋ ላይ ጥለዋል ከሚባሉ ኃይሎች ጋር ነዉ እንጂ ከወዳጅ ጋርማ አብሮ መምከርና መስራት ነዉ እንጂ ድርድር አያስፈልግም ብለዋል።