Thursday, December 27, 2012

በደቡብ ክልል የዳውሮ ወረዳ ዞን ም/ቤት አባላት ዛሬ ከጠሩት ስብሰባ 1500 ሰራተኞች ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸው ተገለጠ


የኢሳት ምንጮች  ከዞኑ እንዳመለከቱት የክቢኒ አባላቱ የምረጡን ስብሰባ አድርገው በነበረ ጊዜ ህዝቡ የኔሰው ገብሬ የተሰዋበትን የሎሜ ከተማ ዋና ከተማ ዋካ ትሁን ጥያቄ ሳይመለስ ስለምርጫ  አናወራም ብለው ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸው ተመልክቶል::
የዳውሮ ዞን ዋና ከተማ በየኔ ሰው ገብሬና በህዝቡ ዘንድ ዋካ መሆን ይገባታል የሚል የነበረ ሲሆን የዞኑ የዴህዴን አመራር አባላት ዋካ መጤ ነዋሪ የመጣባት ከተማ በመሆኖ አይቻልም ሲሉ መቆየታቸው ተገልጦል::
ዛሬ በሎሜ ወረዳ የዞኑ የካቢኔ አባላት ሰራተኞችን ሰብስበው በቅርቡ በሚደረገው የወረዳ ምርጫ ደኢህዴን ኢህአዴግን ምረጡን ለመስበክ ሰራተኞችን ሰብስበው የነበረ ቢሆንም የዋካ ዋና ከተማነት ካልጸደቀ ከናንተ ጋር አንወያይም ሲል ነው 1500 ሰራተኛ ስብሰባውን ረግጠው የወጡት::
ምንጮቻችን ከሎሜ ወረዳ ባደረሱን ዘገባ መሰረት የዞኑ የካቢኔ አባላት መከፋፈላቸውንም ለማወቅ ተችሎል::

No comments:

Post a Comment