Monday, December 31, 2012

የተቃዋሚ 33 የፓለቲካ ድርጅቶች ያቆቆሙት ጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን ሊከሰው መሆኑን አስታወቀ


የምርጫ  ቦርድ ከፍተኛ ሀላፊ የኢህአዴግ አባል ሆነው ለክልልምምክር ቤት አባልነት ምርጫ መወዳደራቸውንም አጋልጦል::
ጊዜዊ ኮሚቴው ለምርጫ ቦርድ ባቀረበው 18 ጥያቄዎች ማስረጃ ያላቸውን ይፋ ያደረገ ሲሆን ምርጫ ቦርድን ለፓርላማ አፈጉባኤ እንደሚከስ አስታውቆል::
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በአስተባባሪ ኮሚቴው የቀረቡት 18 ጥያቄዎች ማስረጃ የላቸውም ብሎ ጥያቄዎቹን ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ ነው ወሳኝ ያላቸው ማስረጃዎች ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች ኮሚቴው ይፋ ያደረገው:፡
ምርጫ ቦርድ በተቃዋሚዎች የቀረቡትን ቅሬታዎች ለወር ያህል ከገመገምኩ በሆላ ሰጠሁ ያለው ምላሽ አሳፋሪና ነገ በህዝብ ዘንድ የሚያስወቅስ መሆኑን ያመለከተው ብሄራዊ ምርጫ ቦርድማስረጃ እንድናቀርብ ሳይጠይቀንና ሳያነጋግረን ውሳኔውን በመንንግስት ሚዲያ ማወጁ አሳዝኖናል ብለዋል::
የጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴው አባልና የቦርድ አመራር አቶ ገብሩ ገብረማሪያም ከጋዜጠኞች ምን ማስረጃ አላችሁ ተብለው ለቀረበ ጥያቄ ለሁሉም በቂ ማስረጃ አለን በማለት የምርጫ ቦርድ  የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሬት ዳይሪክተር ወ/ሮ የሺ ፍቃደ የኢህአዴግ አባል ሆነው ለምርጫ የተወዳደሩበት ማስረጃ አቅርበዋል::
የክልል ም/ቤት አባላት ምርጫ ጣቢያ የድምጽ ቆጠራ ውጤት መተማመኜ በሚለውና የምርጫ የምርጫ ቦርድ አርማ ባለበት በዚህ ሰነድ የእጩ ተወዳዳሪዋ የወ/ሮ የሺ ፍቃደ ስም የሚገኝበት፡ በብአዴን ፓርቲ በንብ ምልክት ፡ እየታዩ ያመጡት የድምጽ ብዛትና ደረጃቸው የሰፈረበት ፡ ለአማራ ክልል ምክር ቤት የደብረ ብርሀን እጩ ተወዳዳሪ ሆነው መቅረባቸውን ያሳያል::
የጊዜያዊ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አስራት ጣሴ አንድም ማስረጃ የሌለው ጥያቄ አላቀረብንም ፡ ካሉ በሆላ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኢህአዴግ ጉዳይ አስፈጸሚ በመሆኑና ሊያነጋግረንም ፡ ማስረጃ እንድናቀርብ ሳይጠይቀንም ጥያቄያችሁን ውድቅ አድርጌያለሁ ማለቱ እንዳሳዘናቸው ገልጠዋል::

በአማራ ክልል 500 ፖሊሶች ስራቸውን ለቀቁ


ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው በክልሉ በአንድ አመት ውስጥ ብቻ 500 ፖሊሶች ስራቸውን ለቀዋል። ፖሊሶች ስራቸውን መልቀቃቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በአንድ ስብሰባ ላይ አምነዋል።
ፖሊሶች ስራቸውን የለቀቁት በአስተዳደር ጫና እና ከስራቸው ጋር የማይጣጣም እና የኑሮ ውድነቱን ለማቋቋም የማያስችል ክፍያ ስለማይከፈላቸው መሆኑን ይገልጻሉ።
በክልሉ ውስጥ የሚታየው የኑሮ ውድነት ፖሊሶችን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የመንግስት ሰራተኞችን እያስመረረ መምጣቱን ለኢሳት የሚደርሱት መረጃዎች ያመለክታሉ። በዚህ የኑሮ ውድነት ላይ ለአባይ ግድብ ማሰሪያና ለትራንስፎርሜሽን እቅዱ ማሳኪያ በሚል ሰራተኞች መዋጮ እንዲከፍሉ መገደዳቸው ኑሮአቸውን የከፋ እንዲሆን እንዳደረገው ሰራተኞች ይገልጻሉ።

    Ring in Redress to All Humankind


    by Alemayehu G. Mariam2012 is gone. 2013 is on the way. Let us ring in redress to all humankind.

    I wish a happy and prosperous new year to all of my readers throughout the world. To those who have unwearyingly2013 is on the way. Let us ring in redress to all humankind followed my columns for nearly three hundred uninterrupted weeks, I wish to express my deep gratitude and appreciation. I am thankful for all of the support and encouragement I have received from my readers in Ethiopia and the Ethiopian Diaspora and others throughout the world.
    I ask my readers to ring in the new year with a firm resolution to seek redress for human rights violations in Ethiopia, other parts of Africa and throughout the world. As Dr. Martin Luther King taught, “Injustice anywhere is a threat to justice everywhere. We are caught in an inescapable network of mutuality, tied in a single garment of destiny. Whatever affects one directly, affects all indirectly…”
    Let us bid farewell to the old year and greet the new one with the poetic words of Lord Alfred Tennyson:
    Ring out the old, ring in the new,…
    Ring out the false, ring in the true.
    Ring out the grief that saps the mind,…
    Ring out the feud of rich and poor,
    Ring in redress to all mankind.
    Ring out a slowly dying cause,
    And ancient forms of party strife;
    Ring in the nobler modes of life,
    With sweeter manners, purer laws…
    Ring out false pride in place and blood,
    The civic slander and the spite;
    Ring in the love of truth and right,
    Ring in the common love of good…
    Ring out the thousand wars of old,
    Ring in the thousand years of peace.
    Ring in the valiant man and free,
    The larger heart, the kindlier hand;
    Ring out the darkness of the land,…
    Ringing Out 2012
    I thought I would ring out 2012 by extracting snippets from selected weekly commentaries I wrote during the year.
    In January 2012, I wondered aloud if there will be an “African Spring” or “Ethiopian Tsedey (Spring)” in 2012. I cryptically answered my own question taking cover in Albert Camus’ book “The Rebel”. “What is a rebel?”, asked Camus. “A man who says no… A slave who has taken orders all his life suddenly decides that he cannot obey some new command. What does he mean by saying ‘no’? He means, for example, that ‘this has been going on too long,’ ‘up to this point yes, beyond it no’, ‘you are going too far,’ or, again, ‘there is a limit beyond which you shall not go.’ But from the moment that the rebel finds his voice — even though he says nothing but ‘no’ — he begins to desire and to judge. The rebel confronts an order of things which oppresses him with the insistence on a kind of right not to be oppressed beyond the limit that he can tolerate.”
    Africa’s Spring will arrive when enough Africans including Ethiopians collectively resolve to rise up from the winter of their discontent and make glorious spring and summer by declaring, “No! Enough is Enough!”

    Sunday, December 30, 2012

    Civilized people uncivilized regime: how did it happen?

    Everybody is wondering how did such civilized people as Ethiopians ended up under the rule of uncivilized regime like Tigrayan People’s Liberation Front (TPLF) “Woyane”?

    Before I go on exploring about how the uncivilized regime remained in power it is appropriate to explain what civilized society means, so that the ‘uncivilized’ understand not to divert us from the main question.

    Free Dictionary defines civilized society:

    Having a highly developed society and culture.
    Showing evidence of moral and intellectual advancement; humane, ethical, and reasonable:
    Marked by refinement in taste and manners; cultured; polished
    Contrast that with the Woyane regime’s culture, moral, intellect, ethics, and manner, noting come close to what Ethiopians are all about.

    Even Woyane supporters attest to that fact by remaining silent and covering up the atrocities and corruptions of their favorite regime for so long confirming their uncivilized behavior. The evidence is overwhelming to justify their behavior. For example, they never demand independent inquiry on all the accusation of genocide, human right violation, corruption, force resettlement, human trafficking, money laundering, extortion, land grabbing…and more. They simply take the word of Woyane at face value and defend it tooth-and-nail while attacking the innocent and everyone else. If that is not uncivilized behavior colluding with an offending party we don’t know what could be.

    Saturday, December 29, 2012

    ESAT Daily News Amsterdam 29 December 2012 Ethiopia

    በኢሳት እርዳታ ሳጅን ሽታየ ወርቁ ራሱን ከማጥፋት ተቆጠበ



    ከሁለት ቀናት በፊት በደቡብ ክልል በዳዉሮ ዞን በሎማ ወረዳ ገሣ ከተማ ላይ ይደረግ በነበረዉና የሎማ ዲሣ ህዝብ የአዲስ ወረዳ አግባብነት ስብሰባ ላይ የግል አስያየቱን የሰጠዉ የፖሊስ ባልደረባ ሳጅን ሽታየ ወርቁ እራሱን ከምግብ እና ከውሀ ለ24 ሰዓታት ከልክሎ በወጣበት ዛፍ ላይ ራሱን ከማጥፋቱ በፊት ከኢሳት ጋር ተገናኝቶ አላማውን ለህዝብ ይፋ ለማድረግ በመፈለጉ የኢሳት ባልደረቦች በስልክ አግኝተው ራሱን እንዳያጠፋ በመምከራቸው፣ ከድርጊቱ ታቅቦ በፖሊስ ታጅቦ ወደ እስር ቤት ተጉዟል።
    ሣጅን ሽታዬ ወርቁ ሺበሺ ከሁለት ቀናት በፊት “ወረዳ አያስፈልም ካላችሁ ለምን ድሮ ለሲዳማ 9 ለወላይታ 5 እያለችሁ ሸንሽናችሁ ሰጣችሁ በማለት” በስብሰባ ላይ በሰጠዉ አስተያየት ምክንያት በዕለቱ ለስብሳበ የወጡ የወረዳዉ የመንግሥት ሠራተኞች የእርሱን ሀሳብ በመደገፍ ስብሰባዉን አቋርጠዉ በመዉጣታቸዉ ምክንያት ከትላንቱ ስብሰባ የወረዳዉ ፖሊስ አባላት በሙሉ እንዳይገቡ መከልከላቸዉን መግለጻችን ይታወሳል፡፡
    ሳጅን ሽታየ በእለቱ ያጋጠመውን ድርጊት በዝርዝር አስረድቷል ።

    ሳጅን ሽታየ ራሱን ለማጥፋት የወሰነው  በእርሱ እና በቤተሰቡ ላይ የደረሰበት በደል ከሚችለው በላይ ሆኖበት መሆኑን ለኢሳት ተናግራል
    ምናልባት ህይወትን ብታጠፋ መንግስት የአእምሮ በሽተኛ ነህ ሊልህ ይችላልና አእምሮ በሽተኛ ነህ ወይ ተብሎ ለቀረበት ጥያቄ፣ ሙሉ ጤነኛ ሆኖማ ስራውን ችግሩ እስከተፈጠረበት ድረስ ሲሰራ እንደነበር ገልጿል፡፡
    የኢሳት ባልደረቦች ሳጅን ሽታየ ራሱን እንዳያጠፋ ለርጅም ሰአት ምክር የለገሱት ሲሆን፣ በመጨረሻም እጁን ለፖሊስ በመስጠት ወደ ዞኑ እስርቤት ተወስዷል።
    ረዳት ሣጅን ሽታዬ ወርቁ ሎማ ዲሣ አካባቢ የዲሣን ወረዳ ጥያቄ የሚያንቀሳቅሱ ሦስት ግለሰቦችን እንዲያስር ከዳዉሮ ዞን የፖለቲካ ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ሽመልስ ታምራት መመሪያ ተሰጥቶት ያለ ጥፋት ሰዉ አይታሰርም በማለቱም በዞኑ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ዘንድ ቅሬታ እንደተያዘበት ታውቋል።
    የዲሣን ወረዳ ጥያቄ ያንቀሳቅሳሉና መታሰር አለባቸዉ ተብለዉ ከዞኑ ፖለቲካ ሀላፊ ከአቶ ሽመልስ ትዕዛዝ ከተላለፈባቸዉ ግለሰቦች መካከል አቶ አባቴ አሰፋ ፤ አቶ መስፊን ማሞ ፤ እና አቶ ደስታ ቶልባ ይገኙበታል።
    በዳዉሮ ዞን የወረዳና ተያያዥ የመብት ጉዳዮች ገፈፋ ጋር በተያያዠ ከመምህር የኔሰዉ ገብሬ ራሱን በቤኒዚን ከማጋየት በኋላ ዓመት ባልተቆጠረ ጊዜ ዉስጥ ከ6 ያላነሱ ሰዎች ራሳቸውን በዛፍ ላይ በመስቀል እና ከገደል ላይ በመወርወር ሞተዋል።

    በቡሬ ግንባር የሚገኙ እና በግጭቱ ታስትፈዋል የተባሉ ወታደሮች መሳሪያቸውን እንዲያስረክቡ ታዘዙ


    የኢሳት ወታደራዊ ምንጮች እንደገለጹት ባለፈው ማክሰኞ ሌሊት በሰራዊቱ መካከል የተፈጠረውን የእርስ በርስ ግጭት ተከትሎ በርካታ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ከሆኑ በሁዋላ ባለፈው ሀሙስ ከመቀሌ እ             ከአፍዴራ የተንቀሳቀሱ ወታደራዊ አዛዦች በግጭቱ የተሳተፉት ሁሉ ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ማድረጋቸው ታውቋል። በእለቱ ከፍተኛ ግምገማ መካሄዱንም ለማወቅ ተችሎአል።
    በአሁኑ ሰአት አንጻራዊ ሰላም መስፈሩን በአካባቢው የሚኖሩ የአፋር ተወላጆች ለኢሳት ገልጸዋል።
    በቡሬ ግንባር በሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት  አባላት መካከል ማንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ማክሰኞ ሌሊት የእርስ በርስ ግጭት ተፈጥሮ እንደነበርና ቁጥሩ ከ12 እሰከ 40 የሚደረስ የሰራዊት አባለት መሞታቸውን መዘገባችን ይታወሳል። 15 ወታደሮች በማንዳ ሆስፒታል የሞቱ ሲሆን፣ 12ቱ ደግሞ በሞትና በህይወት መካከል እንደነበሩ መዘገባችን ይታወቃል። በጽኑ የቆሰሉ አዛዦችም ወደ መቀሌ ሆስፒታል ተወስደዋል።
    የግጭቱን መንስኤ እስካሁን በትክክል ለማወቅ አልተቻለም። በአካባቢው የተመደቡ የሰራዊት አባላትን ለማናገር ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም ሊሳካልን አልቻለም። በቡሬ ግንባር አካባቢ የሞባል ስልክ ኔት ወርክ ለማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን መረጃዎን ያደረሱን ምንጮች ገልጸዋል።
    ማንዳ ከቡሬ ግንባር 21 ኪሎሜትር የሚርቅ ሲሆን፣ ግጭቱ በትክክል የተነሰባት ቦታ አሊ ፉኑ ዳባ እየተባለ በሚጠራው የጎሳ መሪ ስም በተሰየመ አሊ ፉኒ አካባቢ ነው።

    Friday, December 28, 2012

    መንግሰት የኢንተርኔት ድረገጾችን እና ብሎጎችን እንደሚያፍን በይፋ አመነ

    አንዳንድ የኢንተርኔት ድረገጾች እና ብሎጎች በኢትዮጽያ እንደሚታገዱ የኢንፎርሜሽን ደህንነት ኤጀንሲ ዋና
    ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ በይፋ አረጋገጡ፡፡
    ብ/ጄኔራሉ ሰሞኑን ለንባብ ከበቃው መንግስታዊው “ዘመን” መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንዳረጋገጡት
    አንዳንድ አስጊ ናቸው ያሏቸውን የኢንተርኔት ድረገጾችና ብሎጎችን ማገድ የኤጀንሲው ዋንኛ ስራ አለመሆኑን፤ ነገር
    ግን በመርህ ደረጃ መደረግ አለባቸው ብሎ ማስቀመጡን ጠቅሰዋል፡፡“ለዚህ ደግሞ ቴሌ እንዲያጣራቸው አቅም
    የመገንባት ስራ እንሰራለን፡፡ከተቻለ ደግሞ ከሃይማኖት፣ከዘር፣ከሽብርተኝነት፣ከሕዝብ ሞራል ጋር የተያያዙ ድረገጾች
    ወደ ኢትዮጽያ እንዳይገቡ ጥረት ይደረጋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
    “የሃይማኖት አክራሪነት አንድ ስጋት ነው፡፡ከዚያ አልፎ ሽብርተኝነት አለ፡፡ሕዝቡ በስነልቦና እንዲሸበር
    ፍርሃት፣ጭንቀት፣አለመተማመን እንዲሰፋ፣ ወጣቱ በሙሉ አቅሙ ወደ ልማትና ዴሞክራሲ ግንባታ እንዳይገባ የሚያደርጉ
    ኃይሎች አሉ ” ያሉት ብ/ጄኔራሉ  ”ይህን ለመቆጣጠር ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የመከላከያ አቅም መገንባት
    ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
    ብ/ጄኔራሉ በዚሁ ቃለምልልሳቸው መረር ብለው “የኢትዮጽያ ቴሌኮምኒኬሽን የኀብረተሰቡን ሰላም የሚያጠፉ ዌብሳይቶችን
    የመቆጣጠር አቅም ሊኖረው ይገባል፡፡መርሁ ይህ ነው፡፡ለኀብረተሰቡ የሰላምና የልማት አጀንዳ እንቅፋት ሊሆኑ
    የሚችሉ የመቆጣጠር ብቃት አስፈላጊ ነው” ብለዋል፡፡
    “ስርዓት ያልተበጀለት ኢንተርኔት ጉዳቱ ሰፊ ነው” የሚሉት ብ/ጄኔራል ተክለብርሃን “ሕገመንግስቱን ም ሆነ የሕዝቡን ሰላም
    የሚጻረሩ እንቅስቃሴዎች ሊፈቀድላቸው አይገባም” ብሎ አስቀምጧል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
    የኢትዮጽያ መንግስት በኢንተርኔት ድረገጾች እና ብሎጎች ላይ አፈና በማድረግ የዜጎችን ኀሳብን በነጻ የመግለጽ
    ነጻነት የሚጻረሩ ሕገወጥ እርምጃዎችን ይወስዳል በሚል የሚቀርብበትን ተደጋጋሚ ክሶች፤ መሰረተ ቢስ ናቸው በሚል
    ሲያጣጥል መቆየቱ አይዘነጋም፡፡

    The unschooled and uncultured top war criminal Gen Samora is dying…

    A poor peasant and a primary school dropout, who was described by senior political commentator as cold blooded
    The unschooled and uncultured top war criminal Gen Samora is dying
    murderer with thinking and reasoning capacity of a dinosaur, Gen Samora is dying…

    According to a sensitive document leaked to the Horn Times from Bella military referral hospital in Addis Ababa, the frail TPLF army chief-of-staff and top November criminal, the dastardly Gen Samora Yenus Mohamedfereja, has less than a year to live.
    And if he dies before being arrested and tried, Samora Yenus will be the fourth high profile TPLF war criminal to escape justice after the late fuehrer Meles Zenawi, former intelligence chief  Kinfe G.medhin and after former army commander the late Gen Hayelom Araya, who was killed during gun fight over a prostitute in one of Addis Ababa’s brothels.
    Diagnosed with HIV AIDS in 2006 and declared a habitual defaulter for not taking his medication regularly, the illiterate and lowbrow Samora has been receiving treatment consisted of strengthening the body’s natural defense, killing bacteria and battling infection at Essen university hospital in Germany.
    However, despite the impoverished Ethiopia footing his massive medical bill including the purchase of an expensive drug called zidovudine, the bawling warlord has developed new strain known as extensively drug-resistant (XDR) tuberculosis, which resisted all 8 second line drugs.
    The intercepted document further revealed that the murderous warlord is suffering from other scourges as well; diabetes mellitus and hypertension, which complicated the costly multi-system treatments. And currently, he is not responding well to available medications both at home and abroad.
    Hence insiders said he has reached the end of his tether.
    The man who visited heartrending terrors up on the peoples of Ethiopia, Somalia and Eritrea is finally succumbing to the terror of the AIDS pandemic.
    Born to Muslim family who were eking out a hard-scrabble living from subsistence farming in poverty stricken town of Axume-Tigraye in 1955, the wanderer assassin never practiced Islam due to his secular job as TPLF killing machine for nearly 40 years.
    Samora first gained notoriety in 1977 when he executed 6 TPLF combatants for miner sexual offences and barbaricly urinated on their corpuses.
    Although holocausts of deaths from such nerve-racking terrors were common in an outdated organization like the TPLF, an equally notorious former commander of Bado-6 prisons (a network of underground cells strewn across Tigraye), who is now living in the US town of Ohio as fugitive, Bisrat Amare, once described the dying Samora “a Terror guru” after watching him commit various other atrocities.
    But most Ethiopians will remember Samora Yenus for the bloodcurdling war crimes he committed during the 2005 nationwide anti-TPLF uprising.
    The oaf teamed up with federal police boss Workeneh Gebeyehu and nonchalantly pulled off a victory for his fuehrer by using ambulances filled with obdurate Tigre hoodlum dressed as paramedics to penetrate the crowed and exterminate leaders and organizers of the peaceful demonstration.
    Nevertheless, the biggest crime of all was the use of Bella military referral hospital as army and federal police headquarter, where nonplussed and wounded protesters brought in by “ambulances” were watched bleed to death.
    “We have defeated our enemy and straighten the path for Tigre People Liberation Front, TPLF, to rule until the second coming of Jesus Christ.” The unrepentant Samora said in 2007 after the late Zenawi gave him a comparative reward by promoting him to the rank of a General.
    Furthermore, well placed sources inside the TPLF camp told the Horn Times that Samora used the promotion to amass wealth through corrupt practices and now he is the sole owner of a multi-million dollar shopping complex built in Addis Ababa’s Gofa Sefer district, next to St Gabriel orthodox church.
    “I recently visited his glittering bronze statue which is placed at the prestigious Bete Mezeker library in Addis Ababa. Samora is well prepared for life after death.” A political analyst who requested anonymity said.

    በቡሬ ግንባር የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰራዊት እርስ በርሱ ተዋጋ

    የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጡት በቡሬ ግንባር በሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል ማንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ማክሰኞ ሌሊት የተጀመረው የእርስ በርስ ጦርነት እስከ እኩለቀን ዘልቆ እንደነበርና አሁንም ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።

    የእርስ በርስ ጦርነቱ እንደተጀመረ የአካባቢው ነዋሪ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት ጀመሩ በሚል ቀየውን ለቆ የተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት በሄሊኮፕተር እየተንቀሳቀሱ ጦርነቱን ለማስቆም ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ምንጮቻችን ገልጸዋል።

    40 ወታደሮች መሞታቸውን እንዲሁም ከ39 በላይ ደግሞ መቁሰላቸውን ከማንዳ ሆስፒታል የተገኘ መረጃ ያመለካተ ሲሆን፣ ሆስፒታል ሳይደረሱ የሞቱ፣ ወደ መቀሌ ሆስፒታል በሄሊኮፕተር የተወሰዱ ወታደራዊ አዛዦች መኖራቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።

    ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ 15 ወታደሮች ወዲያውኑ መሞታቸውን ፣ 12ቱ ደግሞ ለሞት ሲያጣጥሩ በአይናቸው ማየታቸውን አንድ ስማቸውም ድምጻቸውም እንዳይተላለፍ የጠየቁ በሆስፒታሉ ውስጥ የሚሰሩ ነርስ ተናግረዋል።

    የግጭቱን መንስኤ በትክክል ለማወቅ አልተቻለም። አንዳንድ ወገኖች ግጭቱ በህወሀት ወታደራዊ ባለስልጣናት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የተነሳ ነው ሲሉ ሌሎች ወገኖች ደግሞ በህወሀት ደጋፊ ወታደሮችና በተቀረው ሰራዊት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ነው ይላሉ። ኢሳት የግጭቱን ትክክለኛ ምንጭ ለማወቅ ጥረት እያደረገ ነው።

    ማንዳ ከቡሬ ግንባር 21 ኪሎሜትር የሚርቅ ሲሆን፣ ግጭቱ በትክክል የተነሰባት ቦታ አሊ ፉኑ ዳባ እየተባለ በሚጠራው የጎሳ መሪ ስም በተሰየመ አሊ ፉኒ አካባቢ ነው። ግጭቱ በዚሁ ስፍራ ይጀመር እንጅ ወደ አራት አጎራባች አካባቢዎች ተሰራጭቶ እንደነበር ምንጮች አመልከተዋል።

    ከትናንት በስቲያ እና ትናንት ውጥረቱ እንደነበር ለማወቅ የተቻለ ሲሆን፣ ምናልባትም ግጭቱ እንደገና ሊያገረሽ ይችላል በሚል ስጋት የአካባቢው ሰዎች ቀያቸውን እየለቀቁ ነው።

    የቡሬ ግንባር ዋና እዝ መቀሌ የሚገኝ ሲሆን፣ በሰሜን እዝ አዛዥ ጄነራል ሳእረ መኮንን እንደሚመራ ይታወቃል።

    ቡሬ ግንባር የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከባድመ ቀጥሎ ሀይሉን በብዛት ያሰማራበት ቦታ መሆኑ ይታወቃል። ኢሳት በቅርቡ በሰሜን ግንባር የተመደበን አንድ የመከላከያ ሰራዊት አባል በማናገር በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን ችግር መዘገቡ ይታወሳል።

    በሌላ ዜና ደግሞ በአካባቢው ለሚንቀሳቀሰው የአፋር ጋድሌ ሚሊሺያ ሀይል ወጣቶችን ትመለምላላችሁ የተባሉ የሚሊሺያው ወታዳራዊ አዛዥ የሆኑት የኮሎኔል ሙሀመድ አህመድ 4 የቅርብ ዘመዶች ተይዘው ታስረዋል። በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት መንገሱንና መንግስትም ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ በርካታ ወታደሮችን ማስፈሩን መዘገባችን ይታወሳል።

    ESAT Tikuret Dr Birhanu Nega December 2012

    Thursday, December 27, 2012

    የስነምግባርና የስነዜጋ ትምህርት አስተማሪዎች የኢህአዴግ አባል እንዲሆኑ ጫና እየደረሰባቸው ነው


    መምህራኑ ለኢሳት እንደገለጡት፣ የስነ ምግባርና የስነ ዜጋ መምህራን ከታህሳስ12 እስከ 15 ” የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግሥት የበለፀገች ዴሞከራሲያዊት አገር ለመገንባት ያለው ፋይዳና ሕገ-መንግሥቱን ለትውልድ የማስረፅ አስፈላጊነት” በሚል ርዕስ በአዳማ፣ በሃዋሳ፣ በባህር ዳርና በጅማ ከተሞች ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን ተናግረው፣ ስልጠናው በዋናነት በአገሪቱ ዲሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብቶች አያያዝና የህግ የበላይነት ላይ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ቢጠበቅም፣ በስልጠናው ላይ የታየው ግን መምህራን የኢህአዴግ አባላት እንዲሆኑ መገፋፋትና ማስፈራራት ነው ብለዋል።
    መምህሩ የፈለገውን የፖለቲካ ድርጅት የመከተል መብቱ በህገመንግስት የተረጋጋጠለት ቢሆንም፣ ህገመንግስቱን ማስከበር የሚችለውና ህገመንግስቱ እንዲከበር ፍላጎት ያለው ብቸኛ ድርጅት ኢህአዴግ መሆኑ መገለጹና መምህራንም ህገመንግስቱን የማክበርና የማስከበር ሃለፊነት እንዳለባቸው መገለጹን በስልጠናው የተካፈሉ መምህራን ተናግረዋል።
    አዲሱ የመምህራን የሙያ ብቃት ማረጋጋጫ ከያዛቸው መስፈርቶች መካከል አንዱ “ልዩ ልዩ አገልግሎት” የሚል መሆኑን ያስታወሱት መምህራን፣ ልዩ  አገልግሎት የሚለው ለኢህአዴግ ታማኝነትን መግለጽ ነው ብለዋል።
    ተማሪዎች የሲቪክ መምህራኖቻቸውን ከህገመንግስትና ከዲሞክራሲ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን እንደሚጠይቁዋቸው የገለጹት መምህራን፣ ሆኖም መምህራን ከስራ መባረርን ወይም የደረጃ እድገት መከልከልን በመፍራት ተማሪዎች እንዲህ አይነት ጥያቄዎችን እንዳያነሱ እንደሚከለክሉ ተናግረዋል።

    በሎሚ ዲሳ ወረዳ የፖሊስ አባላት ከህዝብ ጎን በመቆማቸው ስብሰባ እንዳይካፈሉ ታገዱ


    በደቡብ ክልል በዳውሮ ዞን በገሳ ከተማ በተጠራው የመንግስት ሰራተኞች ስብሰባ ላይ የሎማ ዲሳ ህዝብን አዲስ የወረዳ ጥያቄን በመደገፍ ንግግር የዳረጉት የሀምሳ አለቃ ሽታየ ከታሰሩ በሁዋላ፣ ሌሎች የወረዳው ፖሊሶች ዛሬ በተጠራው ስብሰባ ላይ እንዳይካፈሉ ታግደዋል።
    የዞኑ ባለስልጣናት ለዲሳ ህዝብ ወረዳ አያስፈልገውም በማለት መናገራቸውን ተከትሎ አምሳ አለቃው ” ወረዳ ለህዝብ ባያስፈልግ ኖሮ ያኔ ለሲዳማ 9 ለወላይታ 5 እና ለሌሎችም ሁሉ እንደየአቅማቸው ሲታደል ለምን ይቀር አላሉም? ወረዳ ለህዝብ አያስፈልግም የሚለውን እኛ መናገር አንችልም ህዝቡ ይገለናል፣ ከፈለጋችሁ ራሳችሁ ሂዱና አሳምኑ” በማለት መመለሳቸው መዘገቡ  ይታወቃል።
    የዞኑ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ሀላፊ አቶ ተስፋየ መጊሶ ” ይህ የጥገኞች  አስተሳሰብ ነው” በማለት መመለሳቸውን ተከትሎ አምሳለቃው፣ ” እኔ ጥገኛ አይደለሁም የመናገር ነጻነት ያለ መስሎኝ ነው ስለዚህ ጥገኛ ስብሰባ ምን ያደርግለታል፡” በማለት አዳራሹን ለቀው ወጥተዋል። ሌሎች ተሰብሳቢዎችም እርሳቸውን ጥለው መውጣታቸው ይታወሳል።
    በአምሳለቃው ንግግር ያልተደሰቱት ባለስልጣናቱ በዛሬው እለት የወረዳው የፖሊስ አባላት ወደ ስብሰባ እንዳይገቡ ተከልክለዋል።
    በዛሬው አለት የተገኙት ተሰብሳቢዎች የሎማ ዲሳ ህዝብ የወረዳ ጥያቄ መፍትሄ ካላገኘ እንዳይስማሙበት በአንድ ድምጽ መግለጻቸው ታውቋል።
    ጉዳዩን በማስመልከት ጥያቄ ያቀረብንላቸው በስዊድን አገር የሚኖሩት የአካባቢው ተወላጅ መምህር ፍስሃ ተስፋዬ መንግስት ህዝቡን እርስ በርስ ለማጋጨት እየሞከረ ነው በማለት ወቅሰዋል።

      በኦሮሚያ ዳኞች በብዛት እየለቀቁ ነው


      በክልሉ የሚገኙ ዳኞች ከፖለቲካ ተጽእኖ ነጻ በሆነ መንገድ ለመስራት አልቻልንም በሚል ነው ስራቸውን የሚለቁት። አምና ከ100 በላይ ዳኞች ስራቸውን የለቀቁ ሲሆን በያዝነው አመት ደግሞ ቁጥሩ በእጥፍ ጨምሯል።
      ከአንድ ወር በፊት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ታደለ ነጊሾና አቶ ሰይድ ጁንዲን   ስልጣናቸውን ህጋዊ ባልሆነ መንገድ እንዲለቁ ከተደረጉ በሁዋላ፣ ችግሩ መባባሱ ተገልጾአል።
      ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች አሁን ባለው የፌደራል ስርአትና በክልሉ መንግስት ላይ አመኔታ ስለሌላቸው ከስልጣን እንዲለቁ መደረጋቸውን ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ዳኞች ለኢሳት ተናግረዋል።
      የኦሮሚያ ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር140/99 ፕሬዚዳንቱና ምክትሉ ከስልጣን የሚወርዱት በፈቃድ፣ በህመም ፣ በጡረታ ወይም ቅሬታ ካለ ቅሬታው ለምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ቀርቦ አስፈላጊው ማጣራት ከተደረገ በሁዋላ መሆኑን ቢደነግግም፣ አቶ ታደለና አቶ ሰይድ እንዲወርዱ የተደረገበት አካሄድ ግን ከዚህ የተለየ ነው ብለዋል።
      ከሶስት ሳምንት በፊት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙት አቶ ሙዜማም በኦህዴድ አመራር አባልነታቸው የሚታወቁና ገዢውን ፓርቲ ደግፈው በመገናኛ ብዙሀን ሲከራከሩ የነበሩ ናቸው።
      ከዚህ ቀደም  በዳኞች ላይ ይፈጸሙ የነበሩት የመብት ጥሰቶች አሁንም ተጠናክረው በመቀጠላቸው ዳኞች ተቃውሞአቸውን ለማሳየት ስራቸውን በገፍ እየለቀቁ ነው።
      የአዲሱ  ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሹመት ” ህዝብን መናቅ፣ ህዝብ ምን ይመጣል?” በሚል የተደረገ መሆኑን አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ተናግረዋል። “ትናንት ድርጅቴ ኢህአዴግ እንዲህ አድርጎአል እያሉ በሚዲያ ሲናገሩ የነበሩ ሰው ዛሬ ፍትሀዊ ዳኝነት ይሰጣሉ ብሎ ማሰብ አይቻልም” ያሉት ዳኛው፣ ዳኞች ሃላፊነታቸውን እየለቀቁ ከመሄድ ውጭ ሌላ አማራጭ የላቸውም ብለዋል።
      ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ስልጣናቸውን እንዲለቁ የተደረጉት ፕሬዚዳንቱ ፣ የተረከቡትን እቃ አላስረክብም በማለታቸው በደህንንቶች ክትትል ስር እንደነበሩ ለማወቅ ተችሎአል።
      በክልሉ የሚታየው ጎሰኝነት እየጨመረ መሆዱም ዳኞች ስልጣናቸውን እንዲለቁ ተጨማሪ ምክንያት መሆኑም ታውቋል።

      ያለው አማራጭ ሕገ-መንግስቱን ማሻሻል ብቻ ነው ሲሉ አንጋፋው የሕውሀት ታጋይ አቶ ስብሐት ነጋ ገለጹ


      አቶ ስብሐት ነጋ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ከተማ ለንባብ ለበቃው ሰንደቅ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ የመለስ ራዕይ የሚባለው ነገር ትክክል እንደማይመስላቸውና ያለው የጋራ ራዕይ መሆኑን ገልጠዋል::
      ሦስት ምክትል ጠ/ሚኒስትር መሾም ያስፈለገው ክፍት የአመራር ቦታ ስለነበር እንደሆነ ያወሱት አቶ ስብሐት ነጋ: መደረግ የነበረበት ነገር መከናወኑን አስረድተዋል::
      ይህ እርምጃ ሕገ-መንግስቱን ይጥሳል በሚል የሚነሳውን ተቃውሞ በተመለከተ እኔ የማውቀው ነገር የለም ያሉት አቶ ስብሐት ነጋ ሕገ-መንግስቱ ከተጣሰም ያለው አማራጭ ሕገ-መንግስቱን ማሻሻል ወይንም ሌላ አማራጭ መፈለግ እንጂ አዲሱ አደረጃጀት መቀጠል አለበት ብለዋል::
      ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕውሀት)ን ከ1971 እስከ1981 በመሪነት ያገለገሉትና አሁን ይፋዊ የሆነ የፓርቲ አመራር ስፍራ የሌላቸው አቶ ስብሐት ነጋ በሐገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ተጽዕኗቸው የጎላ መሆኑ እየተገለጸ ይገኛል:: በተለይ የአቶ በረከት ሥምዖን ሚና ከቀነሰ ወዲህ ይበልጥ እያንሰራሩ መሆናቸው የተገለጸው አቶ ስብሐት ነጋ በዚህ ረገድ ለተነሳባቸው ጥያቄ እኔ ተራ አባል ነኝ ያለ ሃላፊነቴ ምንም የምሰራው ነገር ያለም ብለዋል::
      እኔ ሥርዓት ከጣስኩ ከግንቦት 7: ኦብነግ እና ኦነግ በምን እለያለሁ:: በማለት ጠይቀው ምንም ሚና የለኝም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል::
      የአቶ መለስ ራዕይ በሚል የሚነሳውን በተመለከተም “በግለሰብ ብቻ የተቀመጠ ራዕይ ሳይሆን የሁላችንም ዕሴት የሆነ የጋራ ራዕይ ነው” በሚል ምላሽ ሰጥተዋል:: ሆኖም አቶ መለስ ወሳኝ ሰው እንደነበሩ በቃለ ምልልሱ አንስተዋል::
      በድርጅቱ ውስጥ ክፍፍል ስለመፈጠሩ ለተነሳባቸው ጥያቄ “እስከአሁን በኢሕአዲግ ውስጥ ይሁን በአባል ድርጅቶቹ መከፋፈል የሚባል ነገር  ገጥሞ አያውቅም:: በዚህ ሂደት በተለያዩ መለኪያዎች ለኢሕአዲግ ብቁ ያልሆኑ ሰዎች ተባረዋል ወይንም በራሳቸው ለቀው ወደ ሚመጥናቸው ድርጅት ሔደው ይወድቃሉ” ያሉት አቶ ስብሐት ነጋ “አሁን በኢሕአዲግ ውስጥ የሚታይ የሚሰማ የፖለቲካ ጥያቄ ያለ አይመስለኝም ብለዋል:: ካለም እንዳለፈው ጸጋ ነው:: በአፈጻጸም ዙሪያም ጥያቄዎች ሊኖሩ ይችላሉ” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል::

      በደቡብ ክልል የዳውሮ ወረዳ ዞን ም/ቤት አባላት ዛሬ ከጠሩት ስብሰባ 1500 ሰራተኞች ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸው ተገለጠ


      የኢሳት ምንጮች  ከዞኑ እንዳመለከቱት የክቢኒ አባላቱ የምረጡን ስብሰባ አድርገው በነበረ ጊዜ ህዝቡ የኔሰው ገብሬ የተሰዋበትን የሎሜ ከተማ ዋና ከተማ ዋካ ትሁን ጥያቄ ሳይመለስ ስለምርጫ  አናወራም ብለው ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸው ተመልክቶል::
      የዳውሮ ዞን ዋና ከተማ በየኔ ሰው ገብሬና በህዝቡ ዘንድ ዋካ መሆን ይገባታል የሚል የነበረ ሲሆን የዞኑ የዴህዴን አመራር አባላት ዋካ መጤ ነዋሪ የመጣባት ከተማ በመሆኖ አይቻልም ሲሉ መቆየታቸው ተገልጦል::
      ዛሬ በሎሜ ወረዳ የዞኑ የካቢኔ አባላት ሰራተኞችን ሰብስበው በቅርቡ በሚደረገው የወረዳ ምርጫ ደኢህዴን ኢህአዴግን ምረጡን ለመስበክ ሰራተኞችን ሰብስበው የነበረ ቢሆንም የዋካ ዋና ከተማነት ካልጸደቀ ከናንተ ጋር አንወያይም ሲል ነው 1500 ሰራተኛ ስብሰባውን ረግጠው የወጡት::
      ምንጮቻችን ከሎሜ ወረዳ ባደረሱን ዘገባ መሰረት የዞኑ የካቢኔ አባላት መከፋፈላቸውንም ለማወቅ ተችሎል::

      Wednesday, December 26, 2012

      በ ኢትዮጵያውያ ከ11 ሚሊዮን በላይ ተረጅዎች አሉ


      አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው 4 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንና በአለም ባንክና በአውሮፓ ህብረት ድጋፍ በምግብ ለስራ ታቅፈው የሚረዱ 7 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን መኖራቸው ታውቋል።
      መንግስት ሴፍቲኔት እያለ በሚጠራው መርሀግብር የታቀፉ ኢትዮጵያውያን ምእራባዊያን ለጋሾች እርዳታቸውን ቢያዘገዩ ወይም ቢያቋርጡ ወደ አስቸኳይ ተረጅነት የሚወርዱ ናቸው።
      በአገሪቱ ውስጥ በሚታየው የምግብ እጥረት የተነሳ በሴፍቲኔት የሚታቀፉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱም ታውቋል። ምንም እንኳ የኢትዮጵያ መንግስት ተከታታይ የኢኮኖሚ እድገት እንዳስመዘገበ ቢገልጽም፣ ከ15 ኢትዮጵያውያን አንዱ ከውጭ በሚሰፈር እርዳታ የሚኖር መሆኑን መረጃዎች አመለክተዋል።

      መምህራን ተማሪዎችን ፈርመው እንዲረከቡ የሚያደርግ መመሪያ ተዘጋጀ


      ኢሳት ዜና:-ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎች መጨመራቸውን ተከትሎ ፣ በአማራ ክልል የሚያስተምሩ መምህራን ተማሪዎችን በሰሚስተሩ መጀመሪያ ላይ ቆጥረው ተረክበው፣ በሰሚስተሩ መጨረሻ ላይ ቆጥረው እንዲያስረክቡ የሚያደርግ መመሪያ ወጥቶ ለውይይት ቢቀርብም፣ መምህራን ግን አጥብቀው ተቃውመውታል።
      በአንድ የትምህርት ዘመን ውስጥ መምህሩ ቆጥሮ ከተረከባቸው ተማሪዎች መካከል ከ2 ተኩል በመቶ በላይ ተማሪዎች ቢያቋርጡ፣ መምህሩ በጥፋተኝነት የሚመዘገብ ሲሆን፣ አስፈላጊውን እድገትም አያገኝም።
      በክልሉ የሚማሩ ተማሪዎች በብዛት ወደ አረብ አገራት በስደት መልክ እንደሚሄዱ መዘገባችንን ተከትሎ እንዲህ አይነት መመሪያ መተላላፉ ታውቋል።
      መንግስት በየጊዜው የሚያወጣቸው መመሪያዎች መምህራን ተስፋ እንዲቆርጡ እያደረጋቸው መሆኑን መምህሩ ተናግረዋል።

      Monday, December 24, 2012

      በህውሀት የብቸኝነት እዝ የሚመራው የኢትዮጵያ ሰራዊት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ከሚደረጉ ህዝባዊ ትግሎች ጎን እንዲሰለፍ ጥሪ ቀረበ


      ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ የትግል አቅጣጫውንና የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና የደህንነት ሀይሎች ለመንግስት ህዝብን የመጨቆኛ መሳሪያ መሆናቸውን አቁመው ከህዝብ ጎን እንዲቆሙ ጥሪውን አስተላልፎል::ታህሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

      ህውሀት ኢህአዴግ በህዝባችን ላይ የሚያደርሰው በደልና ግፍ ሊያበቃ ይገባል ያለው የሸንጎ መግለጫ በእስር ላይ ያሉት የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ባስቸኮይ እንዲፈቱም መንግስትን አሳስቦል::
      አፋኝ የሆኑ የሚዲያና የሽብርተኝነት ህጎች በሙሉ እንዲሰረዙ ያሳሰበው የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ የመንግስት ሚዲያዎች ለምርጫ ግዜ ብቻ ለፕሮፓጋንዳ ሲባል የሚሰጥ ሽርፍራፊ ሰአት ቆሞ በመደበኛነት የተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚሳተፉበት እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል\::
      የዲፕሎማቲክ የበላይነት በአንድ ወይም በሁለት ድርጅት ትግል እንደማይገኝ ያመለከተው የሸንጎ መግለጫ ለዘለቄታ ዲፕሎማሲያዊ የበላይነት ለመብቃት ጠቃሚ ስትራቴጂዎችን በመቀየስ ከሌሎች ሀይሎች ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አመልክቶል::

      የግንቦት7 ህዝባዊ ሐይል ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ




      ኢሳት ዜና:-የድርጅቱ ቃል አቀባይ ታጋይ ዜና ጉታ ለኢሳት እንደገለጠው ከትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ወይም ደሚት፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ ፍትህና እኩልነት ግንባር፣ ከጋምቤላ ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፣ ከቤንሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ እንዲሁም የአማራ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ከተባሉት ድርጅቶች ጋር በጥምረት ለመስራት አስፈላጊው ዝግጅት አጠናቋል።ታህሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
      ታጋይ ዜና ጉታ ህዝባዊ ሀይሉ በዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ከሚመራው የግንቦት7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ጋር ግንኙነት እንዳለው ጥያቄ ቢቀርብለትም አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።

      ESAT EthiopiaTikuret Fez ralizm Tamagn Beyene Part 2

      ሰበር ዜና – ማኅበረ ቅዱሳን ራሱንና የአባላቱን አቋም በመፃረር በፓትርያሪክ ምርጫው ለመሳተፍ ወሰነ


      ሐራ ዘተዋሕዶ

      • ማኅበሩ ዲ/ን ዓባይነህ ካሴ ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የሰጡትን አስተያየት አስተባብሏል
      • የማኅበሩ ምክትል ሰብሳቢ ከመንግሥት ለተመደቡት ባለሥልጣን እገዛ ትሰጣለች
      • ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በማኅበሩ ጥቂት አመራሮች አቋም ግራ ተጋብተዋል
      • የማኅበሩ የሰሜን አሜሪካ ማእከል ሰብሳቢ የአቋም ለውጡን በመቃወም ‹‹ውሳኔው አያስማማንም፤ የማስቀድመው ዕርቀ ሰላሙን ነው›› ብለዋል፡፡
      ‹‹ቤተ ክርስቲያናችንን ወደ አንድነት የሚያመጣ ዕርቀ ሰላም መፈጸም ከሃይማኖታዊ ሥነ ምግባር አንጻር፣ ለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ከማሰብ አንጻር፣ መንጋውን ከማነጽና ሐዋርያዊ
      Uganda, Kampala Ethiopian Orthodox Church
      Uganda, Kampala Ethiopian Orthodox Church
      አገልግሎትን ከማቅናት አንጻር ለአባቶቻችን ግዴታ ይኾንባቸዋል፡፡ የሚፈለገው ዕርቀ ሰላም እውን እንዲሆንም ለእግዚአብሔር ፈቃድ፣ ለእውነት፣ ለኅሊና ምስክርነት መገዛት አግባብ ይሆናል›› – ይህ መልእክት በሐመር መጽሔት፣ 20 ዓመት ቁጥር 8፣ ታኅሣሥ 2005 ዓ.ም በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የወጣ፣ በድረ ገጹም የተደገመ የማኅበረ ቅዱሳን አቋም ነው፡፡ ይህ የማኅበረ ቅዱሳን መልእክት‹‹ከምርጫው ይልቅ ዕርቀ ሰላሙ ይቅደም››ከሚለውና ማኅበሩ የበለጠ ከሚታወቅበት አቋሙ የመነጨ ነው፡፡
      ማኅበረ ቅዱሳን በመልእክቱ ዕርቅ÷ ‹‹በቤተ መቅደሱ ዕለት ዕለት መሥዋዕት ለሚያቀርቡ፣ ብዙዎችን በጸጋ እግዚአብሔር ባዕለጸጋ ለሚያደርጉ፣ ምስጢራትንም ሁሉ ለሚፈጽሙ፣ የሃይማኖትና የሥነ ምግባር ምልክት ለሆኑ ከሁለቱም ወገን ያሉ ብፁዐን አባቶች የሚያስተምሩት ብቻ ሳይሆን ዘወትር እንዲኖሩት የሚጠበቅ ክርስቲያናዊ ሕይወት›› መኾኑን መክሮ ነበር፡፡ መምከር ብቻ ሳይሆን÷ ቤተ ክርስቲያን ለኻያ ዓመታት ያሳለፈቻቸው አሳዘኝ ኹኔታዎች እንዳይቀጥሉ ዛሬ ላይ መደረግ የሚገባው ሁሉ መደረግ ይኖርበታል ብሎ እንደሚያምን፣ ለዚህም እንደሚሠራ አቋሙን አስታውቆ ነበር፡፡
      ዛሬ፣ ታኅሣሥ 12 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀትር በኋላ ከመንበረ ፓትርያሪኩ የተሰማው ዜና ግን ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ጉዳይ ማድረግ ከሚችለው አስተዋፅኦ አንጻር በውጭም በውስጥም፣ በቅርብም በሩቅም ተስፋ ለሚያደርጉት ወገኖች ሁሉ አንገት የሚያስደፋ ነው፡፡ የማኅበሩ ጥቂት አመራሮች በወሰኑት ውሳኔ ማኅበሩ ‹‹ቅድሚያ ለዕርቀ ሰላሙ›› ሲለው የነበረው መፈክር ‹‹ቅድሚያ ለምርጫው›› ወደሚለው ተለውጧል!!
      የማኅበሩ ሥራ አመራር ጉባኤ አባል የኾነውና በነሐሴው የማኅበሩ 10 ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በአወዛጋቢ አኳኋን የተመረጠው አቶ ባያብል ሙላቴ የአስመራጭ ኮሚቴው አባልነቱን የተቀበለ ሲኾን ዛሬ በተሰማው የማኅበሩ የአቋም ለውጥ ደግሞ የፓትርያሪክ ምርጫ ሂደቱን እንድትከታተል የማኅበሩ ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሪት ዳግማዊት ኀይሌ መመደቧ ተነግሯል፡፡ አቶ ባያብል ሙላቴ ከሲኖዶሱ በተመደቡ ሰባት ሊቃነ ጳጳሳት አማካይነት ተቋቁሞ ያለበቂ ትችትና ውይይት በቀጥታ በጸደቀው 13 አባላት ባሉት አስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ አንዱ አባል መኾ ናቸው ቢታወቅም ማኅበሩን ይወክላሉ በሚል የተመረጡበት መንገድ ግን ለብዙዎች ግልጽ አይደለም፡፡
      የምክትል ሰብሳቢዋ ወ/ሪት ዳግማዊት የዛሬው ምደባ የአቶ ባያብል በአስመራጭ ኮሚቴ መካተት በማኅበሩ ላይ የፈጠረው አጣብቂኝ አስተዋፅኦ ሊያደርግ እንደሚችል የሚስማሙ ተቺዎች÷ ከመንግሥት ከፍተኛ አካላት ጋራ በዕርቀ ሰላሙና በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ መርቆሬዎስ አመላለስ መካከል ስለመለየት እንዲሁም ስለ ተተኪ ፓትርያሪክ ምርጫ በተደጋጋሚ የተደረገው ውይይት ቀጥተኛ ጫና ሳያሳድር እንዳልቀረ ይናገራሉ፡፡ ዕርቀ ሰላሙ ዕንቅፋት የሚፈጥሩ ቀኖናዊ ጉዳዮችን ከግምት በማስገባት፣ ተቀባይነት የሌላቸውን ቅደመ ኹኔታዎች በማስወገድ መፈጸም እንደሚገባው የሚገልጸው ማኅበሩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበር ይመለሱ የሚለውን በመቃወም የስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ መፈጸም ይኖርበታል ብሎ እንደሚያምን ተመልክቷል፡፡
      ይኸው የማኅበሩ አቋም በተለይም የማኅበሩ ኤዲቶሪያል ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ የኾኑት ዲ/ን ዓባይነህ ካሴ ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን የሰላም ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን ከሰጡ ወዲህ ተግዳሮት እንደገጠመው ይነገራል፡፡ ዲ/ን ዓባይነህ በማኅበሩ ያላቸውን ሓላፊነት ጠቅሰው ሲያበቁ÷ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ወደ መንበር መመለስ የተጣሰው ቀኖና የሚቃናበት አንድ አማራጭ መኾኑን ማስቀመጣቸው፣ ቅድሚያ ለዕርቀ ሰላሙ በማለት አሰምቶ የሚጮኸው በአራቱም ማእዝናት የሚገኝ ምእመን ድምፅ ሊደመጥ እንደሚገባው ማሳሰባቸው፤ ከማንም ተጽዕኖ ይመጣል ብሎ ሳይፈራ በመግባባት፣ መወያየት፣ መንቀሳቀስና መነጋገር እንደሚያስፈልገው መጠቆማቸው፤ የሁለቱ ወገኖች የሰላም ልኡካን አብረው መጸለያቸውና መቀደሳቸው ‹‹ታላቅ ርምጃ›› መኾኑን መናገራቸው የማኅበሩን የቀደመ አቋም የለወጡትን ጥቂት አመራሮች አለማስደሰቱ ተገልጧል፡፡
      ይህን በተመለከተ የማኅበሩ አራት አመራሮች በትላንትናው ዕለት ምሽት ዲ/ን ዓባይነህን ያነጋገሩ ሲኾን በዛሬው ዕለት ማምሻውን ደግሞ ዲ/ን ዓባይነህ ለቪ.ኦ.ኤ የሰጡት ቃለ ምልልስ ማኅበሩን እንደማይወክልና የግላቸው መኾኑን በድረ ገጹ አስታውቋል፡፡ ዲ/ን ዓባይነህ በሬዲዮው ቃለ ምልልሳቸው የሰጡት አስተያየት የማኅበሩ አመራሮች ከመንግሥት ከፍተኛ አካላት ባደረጉት ውይይት ካስቀመጡት አቋምና በየጊዜው ለሊቃነ ጳጳሳቱ ከሚሰጡት ማብራሪያ ጋራ ‹‹የተጋጨ ነው፤ አባቶችን የሚከፋፍል ነው›› መባሉ የማኅበሩን ጥቂት አመራሮች ዛሬ የተሰማውን ዐይነት ግልጽ ነገር ግን በታሪክ አሳዛኝ የኾነ አካሄድ ውስጥ እንዲገቡ እንዳስገደዳቸው ተተችቷል፡፡ ወዲያውም ደግሞ ‹‹ርምጃ ወስደን እናሳውቃችኋለን›› ላሏቸው እንደ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ ላሉት ሊቃነ ጳጳሳት የተግባር ምላሽ መኾኑ ተመልክቷል፡፡
      ወ/ሪት ዳግማዊት በተመደበችበት ሓላፊነት ‹‹የፓትርያሪክ ምርጫውን ሰላማዊ ለማድረግ›› በሚል ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሃይማኖት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ለተመደቡት አቶ ትእዛዙ ደሳለኝ መረጃዎች በመስጠትና ከአባቶች ጋራ በማቀራረብ እንደምትረዳ ተጠቁሟል፡፡ በተመሳሳይ አኳኋን የማኅበሩ ጽ/ቤት ሓላፊዎች የማኅበሩ የዋናው ማእከል ጽ/ቤት ልዩ ልዩ ክፍሎች÷ ማኅበሩ በምርጫው ላይ በማተኮር ለሚሠራው ሥራ እንዲዘጋጁ መመሪያና ማሳሰቢያ ሲሰጡ መዋላቸው ተዘግቧል፡፡
      ይኹንና ውሳኔው የማኅበሩ ከፍተኛ አመራር ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ ዕርቀ ሰላሙ ቅድሚያ እንዲሰጠውና በትኩረት እንዲሠራበት በሙሉ ድምፅ ሊባል በሚችል መልኩ ያሳለፈውን መመሪያ የሚፃረር መኾኑን የገለጹ ወገኖች በአቋም ለውጡ ‹‹ራሱንና ለረጅም ጊዜ በጋራ ሲሠራበት የነበረውን የአባላቱን አቋም ተፃሯል›› ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ የቀድሞው የማኅበሩ ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም÷ ዕርቅ ሳይፈጸም ምንም ዐይነት እንቀስቃሴ እንዳይደረግ አበው መነኰሳቱ ለአባቶች እንዲመክሩና ኹኔታውንም በጸሎት እንዲያስቡ የተማፀኑት በትላንትናው ዕለት ምሽት አምስት ብፁዓን አባቶች በተገኙበት በተዘጋውና ለስድስት ቀናት የቆየው 70 የገዳማት አበምኔቶች ከ61 ገዳማት በተገኙበት ዐውደ ጉባኤ እንደነበር ተወስቷል፡፡
      የማኅበሩ የሰሜን አሜሪካ ማእከል ሰብሳቢ የኾኑት ቀሲስ በላቸው ወርቁ ከዋናው ጽ/ቤት ሓላፊዎች ጋራ በስልክ አድርገውታል በተባለ ውይይት÷ ‹‹የተወሰነው ውሳኔ ፈጽሞ አያስማማንም፤ እኛ የምናስቀድመው ዕርቀ ሰላሙን ነው፤ ባለሁበት ቤተ ክርስቲያን በምሰጠው አገልግሎት ከዚህ የማኅበሩ አቋም እለያለኹ›› በሚል ተቃውሟቸውን መግለጻቸው ተገልጧል፡፡
      ለሁለት ዐሥርት ዓመታት መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ልማታዊ አገልግሎት በመፈጸም የትውልድ ግዴታውን እየተወጣ የሚገኘውን የማኅበረ ቅዱሳንን ክፉ መስማትም ማየትም አንሻም፡፡ ነገር ግን÷ ከቤተ ክርስቲያን አንድነትና ሰላም የሚቀድም ነገር ደግሞ የለም፡፡ ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት እስከቆመ ድረስ ሁሉም ከጎኑ ይቆማል፤ አሰላለፉ፣ ስልቱ ይህን ሲቃረን ደግሞ ብቻውን ይቀራል፡፡
      የቤተ ክርስቲያንን ሰላምና አንድነት እንደሚያረጋግጥ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ አገልጋዮችና ምእመናን ታምኖበት እየተደከመበት የሚገኘው ‹‹የዕርቀ ሰላም ይቅደም›› ጥያቄ ወደ አዲስ ምዕራፍ ሊሸጋገር ባለበት ዋዜማ ማኅበሩ የወሰደው አቋም ክፉኛ ያሳስበናል፡፡ ማኅበሩ በርግጥም ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ድምፁን ከፍ አድርጎ ለማሰማት ከተዘጋጀው ምእመን ጋራ ለመሰለፍ የተዘጋጁ ብዙኀን አመራሩና አባላቱ ማኅበር ከኾነ ጊዜው ከማለፉ በፊት የዛሬውን አቋሙን ያጢን፣ ይመርምር እንላለን ! ! !

      Sunday, December 23, 2012

      ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ተመሰረተ (ግንቦት 7 ዜና)



      News, Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy.www.ginbot7pf.org በሚል ድረ ገጽ ላይ የወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የሚባል ድርጅት መመስረቱ ተገለጸ ።  መግለጫውን ያወጣው የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል እንዳብራራው ታህሳስ 11 ቀን 2012 ዓም ” የወያኔን ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በትጥቅ ትግል ለማስወገድ “የግንቦት7 ሕዝባዊ ኃይል” የሚል ስያሜ የሰጠነውን፣ በሃገር ወዳድና ለህዝብ ተቆርቋሪ በሆኑ ወጣቶች፣ ምሁራንና ዜጎች የተሞላውን ድርጅት መመሥረታችን በዛሬው እለት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በይፋ እናበስራልን” ብሎአል።
      “የሕዝብ ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት፤ የዜጎች መብቶች፣ ሃገራዊ አንድነት፣ ደህንነትና ጥቅም የተከበሩባት ጠንካራና ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እውን ሆኖ የማየትን ራዕይ የሰነቀ ድርጅት መሆኑን” የገለጸው ህዝባዊ ሀይሉ፣ መንግስትን በኃይል የማስወገድ፤ ሰላማዊና ዲሞክራሲ የሥልጣን ሽግግር በሃገሪቱ እንዲኖር የማስቻል እና ከማንኛዉም የፓለቲካ ድርጅት ጋር ያልወገኑ ነፃ፣ ጠንካራና ብቃት ያላቸው ህገ-መንግሥታዊ የመከላከያ፣ የፓሊስና የደህንነት ተቋማት እንዲኖሩ አስተዋጽዖ የማድረግ ተልዕኮ” ይዞ መነሳቱን ገልጿል።
      ህዝባዊ ሀይሉ “በሃገራችን በወያኔ አምባገነናዊ እብሪት ያልታፈነ፣ ያልተዋረደና ያልተዘረፈ የሃገሪቱ ዜጋ እንደማይገኝ ገልጾ፣ ሹማምንቱ በሃብት ላይ ሃብት፤ በድሎት ላይ ድሎት ሲጨምሩ፣ የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ እጣ ፈንታ ግን መፈናቀል፣ መሰደድ፣ መንገላታት፣ መታሰር፣ መደብደብና መገደል ሆኗል” ብሎአል። “የወያኔ  የአመጽ እብሪት በሕዝባዊ አመጽ የሚተነፍስበት ሁኔታ  እስካልመጣ ድረስ፣ ወያኔ መብታቸውን ከመጠየቅ ውጭ ምንም እንከን የሌለባቸውን ንጹሃን ዜጎች ከማሰር፣ ሰቆቃ ከመፈጸም፣ ከመግደል ከማሳደድና  ከማፈናቀል” እንደማይቦዝን ህዝባዊ ሐይሉ ገልጿል።
      የግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል ” ዜጎች በሽብርተኛነት እየተከሰሱ በእድሜ ልክ እስራት ሲቀጡና ሰቆቃ ሲፈፀምባቸው የታዘባችሁ ወጣቶች፤ ለሃይማኖት እኩልነት በመታገላቸው በእስር ላይ እየማቀቁ፣ እየተገረፉና እየተሰቃዩ ያሉ የሙስሊም ምዕመናን ተወካዮች ጉዳይ የሚያሳስባችሁ ወገኖች፤ በቤተክህነትና በክርስትና ተቋማት ላይ እየተፈፀመ ያለው ደባ የሚያንገበግባችሁ ፤ ለወያኔዎችና ሸሪኮቻቸው እድገትና ምቾት ሲባል ከይዞታችሁ የተፈናቀላችሁ፤ ገቢን ሳይሆን ወገንተኛነትን መስፈረት ባደረገ መመዘኛ ከአቅም በላይ የሆነ የወያኔ ግብር፣ ታክስና መዋጮ የተማረራችሁ ነጋዴዎች፤ ማኅበራችሁ በወያኔ ፈርሶ ወይም ተጠልፎ የጋራ ድምፃችሁን የምታሰሙበት፣ ከቀጣሪያችሁ ከወያኔ  ጋር ፍትሃዊ የጉልበታችሁን ዋጋ ክፍያ መደራደሪያ ያጣችሁ ላብአደሮች፣ መምህራን፣ የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች፤ ምንም አይነት የአካዳሚ ነጻነት በሌለበት ሁኔታ ጥራቱን ያልጠበቀ ትምህርት እንድትከታተሉ የተፈረደባችሁ፣ ትምህርታችሁን ጨርሳችሁ ከየኮሌጁና ከየዩንቨርስቲው ስትመረቁ እጣችሁ ድንጋይ ማንጠፍ የሆነው ወጣት ተማሪዎች” ትግሉን ተቀላቀሉ ሲል ጥሪ አቅርቧል።
      ህዝባዊ ሀይሉ “አደገኛ በረሃዎችንና ባህሮችን በማቋረጥ ለመሰደድ ልባችሁ እየከጀለ ላሉ ወጣቶች፣ በአረብ ሃገራት ለባርነት ስራ ተሽጠው እጣቸው ተገዶ  መደፈር፣ በፈላው ወሃ መቀቀል፣ መደብደብ፣ መዋረድና ከፎቅ ላይ እየተወረሩ ክቡር ህይወትን ማጣት ለሆነው ሴቶች፣  ለሃገር አንድነትና ክብር መሰለፍ እንደ ወንጀል ተቆጥሮባቸው እንደ ባዕድ ጦር የተበተኑና የተገፉ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ በሚታየው ዘረኛነት እየተቃጠሉ፣ በሕዝብ ላይ ዝመቱ በተባሉ ቁጥር ከህሊናቸው  ጋር መዳማት የመረራችው የኢትዮጵያ ወታደሮች እና በድህነት አስገዳጅነት፣ እንዲሁም በሌሎችም ማስፈራሪያዎችና ጫናዎች የወያኔ/ኢህአዴግ ድርጅቶች አባል የሆኑ ወገኖች በሙሉ” ጥሪውን ሰምተው ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጠይቋል።
      በ http://www.ginbot7pf.org ድረገጽ ላይ የወጣው ዜና እንደሚያመለክተው ህዝባዊ ሀይሉ ራሱን በትጥቅና በሰው ሀይል አደራጅቷል።

      Wild celebrations as news of the formation of a crack guerrilla group reach South Africa!


      The Horn Times Breaking News, 21 December 2012
      by Getahune Bekele, Johannesburg
      “Tekebresh yenorshiw babatochachin dem,”
      Enat Ethiopia yedeferesh yewdem,”

      The patriotic song made famous by the incomparable Ethiopian singer Shambel Belayneh was on everyone’s lips on
      GPF, Ginbot 7 popular Force fighters on the move.
      GPF, Ginbot 7 popular Force fighters on the move…
      Saturday morning 21 December 2012, when the Horn Times visited the bustling GP street in central Johannesburg where Ethiopian refugees usually gather in large numbers.
      “President Jacob Zuma, it is time to return the favor, help our freedom fighters…” an excited Ethiopian refugee shouted at a passing police van while his friends whistle and scream “freedom! Freedom!”
      “The day 90 million Ethiopians patiently waited for has finally arrived.
      And the long walk to freedom begins now. Begging for freedom from a homicide maniac has come to a grinding halt. This is the way to go if we want to break the bondage of slavery.” Henock Alemayehu, 24, a college student in the city of Pretoria told the Horn Times, smiling ear to ear.
      As the announcement of the formation of the guerrilla group spread throughout South Africa like wildfires, GPF was also showered with congratulatory messages and some freedom loving refugees even pledged financial assistance.
      Here in South Africa, many exiles believe the announcement would trigger a mass defection from non-Tigre members of the brutal TPLF army and the regime would collapse sooner than expected.
      The Ethiopian community association in South Africa spokes person also lauded the formation of the GPF as a milestone in the struggle against the rapacious minority junta and sent out his message of congratulations to Ginbot-7 opposition party leaders.
      “The announcement of the formation of Ginbot 7 Popular Force, GPF, is like sweet melody to the ears of millions of Ethiopians. Attempting to talk peace with fascist warlords for 21 years had proved a total waste of time. It is time to talk to them with the only language they understand.” The spokesperson said.
      “Deadly inter tribal clashes; hunger and disease are still blighting our country .Arbitrary arrest, torture and extrajudicial killings are perfectly legal. While the junta receives billions of dollars in foreign aid, material poverty is driving thousands out of the country. Ethiopia is nothing but the world’s biggest open air prison. To end all this, Ethiopia doesn’t need myopic political parties, we need crack guerrilla groups and GPF is the answer. It will carry the hopes and aspirations of 90 million Ethiopians.” The spokesman added.
      Furthermore, a military analyst from Addis Ababa- Ethiopia told the Horn Times that if GPF fighters hit any area in the vast nation and hold on to a village or a town for few days, the brutally oppressed Ethiopians will rise against the junta.
      “Look, in the TPLF army one platoon has 3 ethnic Tigre commanders and one Tigre political commissar. In one squad (9 solders) there is one Tigre commander and two gujjiles who are spying and watching the performances of contracted non- Tigre solders. That is why am saying if GPF fighters score even a miner victory, these unhappy solders will turn their guns on their commanders.” He explains.
      In additional news, concerned Ethiopians in South Africa have called on Ethiopatriot website to stop demonizing respected opposition party leaders such as Dr Berhanu Nega and Andargachew Tsige.
      “Patriots doesn’t call fellow patriots ‘traitors’, we know some great Ethiopians associated with the Ethiopatriot group. Let’s not fragment ourselves. Let’s slain the evil behemoth in Aratkilo together. Let’s rally around GPF.” The Ethiopians said.

      Ethiopia 2012: Human Rights and Government Wrongs


      by Alemayehu G. Mariam,

      Another Groundhog Year

      Ethiopia 2012: Human Rights and Government Wrongs
      It was a repetition of 2007, 2006, 2005, 2004… Everyday millions of Ethiopians woke up only to find themselves trapped in a time loop where their lives replayed like a broken record. Each “new” day is the same as the one before it: Repression, intimidation, corruption, incarceration, deception, brutalization and human rights violation… They have no idea how to get out of this awful cycle of misery, agony, despair and tribulation. So, they pray and pray and pray and pray… for deliverance from Evil!
      It is December 2012. Are Ethiopians better off today than they were in 2008, 2009, 2010, 2011? 
      Does bread (teff) cost more today than it did in 2008…, a year ago? Cooking oil, produce, basic staples, beef, poultry, housing, water, electricity, household fuel, gasoline…?
      Are there more poor people in Ethiopia today than there were in 2008? More hunger, homelessness, unemployment, less health care, fewer educational opportunities for young people?
      Is there more corruption and secrecy and less transparency and accountability in December 2012 than in December 2008?
      Are elections more free and fair in 2012 than in 2008?
      Are there more political prisoners today than in 2008?
      Is there less press freedom and are more journalists in prison today than in 2008?
      Is Ethiopia more dependent on international handouts for its daily bread today than it was in 2008?
      Is there more environmental pollution, habitat destruction, forced human displacement and land grabbing in Ethiopia today than 2008?
      Is Ethiopia today still at the very bottom of the U.N. Human Development Index?