Saturday, January 26, 2013

ESAT Daliy News Amsterdam Jan 26 2013 Ethiopia

Open letter to Confederation of African Football (CAF)

by Kiflu Hussain

I don’t know whether CAF has a regulation that prohibits making a political statement during African Cup of Nations

Confederation of African Football (CAF)(AFCON) football matches. I know it’s not allowed making a political statement in Olympics.A case in point; in 2012 a South Korean football player who made such a statement against Japan over a border dispute by revealing a symbol he hid under his official shirt after scoring a goal was banned from the medal ceremony.
Why did I bring this up? Because of a disturbing unconfirmed report that the Ethiopian regime via the Embassy in South Africa are putting pressure on Ethiopian footballers to wear a shirt that carries the late Ethiopian dictator Meles Zenawi’s picture under the national shirt so that they show it off after scoring a goal in the upcoming match with Burkina Faso.
If that’s the case, CAF and all concerned should know that the deceased was a criminal against humanity, a traitor who traded off Ethiopia’s vital interests and a warmonger who brought division, suffering and destruction in the Horn of Africa. Showing off the deceased’s picture in the stadium will surely destroy the spirit of the popular sport that is supposed to promote and strengthen African brother and sisterhood.Therefore, CAF should nip this shameless bid of the cadres of the Ethiopian regime in the bud. Cadres have no place in sports fields.
An Ethiopian social & political commentator exiled in Uganda

Email: kiflukam@yahoo.com

Wednesday, January 23, 2013

በጥምቀት በዓል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሲሸጡ የነበሩ ሰዎች ታሰሩ


ብዙውን ጊዜ በጥምቀት በዓል ጊዜ የሚጠቀሰውንና ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በላከው መልእክቱ ምዕራፍ 4 ቁጥር 5 ላይ ያሰፈረውን ፦“አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ጥምቀት” የሚል  የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የተፃፈበት ቆብ  የጥምቀት ዕለት ለሰንበት ት/ቤታቸው ገቢ ማስገኛነት በመሸጥ ላይ የነበሩ ወጣቶች በፖሊስ ታፍሰው ታሰሩ።
እንደ ደጀ ሰላም ዘገባ፤ ጥር 11/2005 ዓ.ም ታቦተ ሕጉን ተከትለው በሞቀና በደመቀ ሃይማኖታዊ መንፈስ በማክበር ላይ እያሉ በፖሊስ የታሠሩት ስድስት ወጣቶች ሲሆኑ ፤ጥቅሱ የተጻፈበትን ቆብ ይሸጡ የነበሩት  ለብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ገቢ ለማስገኘት  እንደሆነ ተገልጿል።
ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር  በአንድ ወቅት ወጣቶችን ሰብስበው ስለሀይማኖቶች ባደረጉት ገለፃ ፦ ተመሳሳይ ጥቅስ የተፃፈበትን ቲሸርት የለበሱ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችን ፦<<አንዲት ሀይማኖት የሚሉ አክራሪዎች>>በማለት እንደዘለፏቸው ይታወሳል።አንድ ኣማኝ ለሚያምንበት ነገር ምክንያቶቹን እንደሚያቀርብ ሁሉ ክርስቲያኖችም ስለ እምነታቸው በመጽሐፍ ቅዱሳቸው የተፃፈውን ጠቅሰው ለራሳቸው ትምህርትና ጥቅም ማዋላቸው እንዴት ከ አክራሪነት ጋር እንደተያያዘ ግልጽ አይደለም ያሉት የሀይሞኖቱ አባቶች፤ “አክራሪነት ማለት የራሱን እምነት በሌሎች ላይ በሀይልና በተጽዕኖ ለመጫን መሞከር ነው።መንግስት እያደረገ ያለው ግን የራሳችሁን እምነት አትከተሉ ይመስላል።ሰዎቹ የቀራቸው ነገር ጥቅሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መሰረዝ አለበት የሚል አዋጅ ማውጣት ብቻ ነው>>ብለዋል።
ያለ በቂ ዕውቀት የሃይማኖት አክራሪነትን እዋጋለኹ  ብሎ የተነሳው መንግስት ‘አንዲት ሃይማኖት…አንዲት ጥምቀት’ የምትለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅስ ለራሳቸው መማሪያ የሚያውሉትን ክርስቲያኖችን በሙሉ በማሳደድ ላይ ይገኛል ብሏል-ደጀ ሰላም።የመጽሐፍ ቅዱስን ኃይለ- ቃል እና የቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረተ እምነት የሆነውን ቃለ እግዚአብሔርን መናገር፣ ማስተማርም ሆነ በጽሑፍ መያዝ ፤ሌሎች እምነቶችን እንደመዋጋት ተደርጎ እንደሚቆጠር በመናገር በፖሊሶቹ አማካይነት ጥብቅ ማዋከብና እንግልት የሚፈጽመው መንግሥት እነዚህን ስድስት ልጆች ያሰረውም በዚሁ ምክንያት መሆኑን በወቅቱ በቦታው የነበሩ እማኞች ተናግረዋል።ድረ-ገጹ አክሎም ኢትዮጵያ ውስጥ ከነበሩ ቀደምት መንግሥታት ሁሉ በባሰና በከፋ መንገድ በቤተ ክርስቲያኒቱ የውስጥ ጉዳይ ረዥም እጁን አስገብቶ የሚያምሰው  ይህ መንግስት ፣  በቅርቡ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤያት ላይ ሳይቀር ባለ ሥልጣኖቹን በመላክ የሲኖዶሱ ተሰብሳቢ ለመሆን በመሞከር ላይ ይገኛልም ብሏል።መንግሥት በአገሪቱ ቀደምት እምነቶች ላይ ያለውን አቋም ለካድሬዎቹ በተከታታይ ሥልጠና በመስጠት የሚያስጠናበት ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል።ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ድረስ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና በሌሎች ኃላፊዎች ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና እስልምና ላይ ያነጣጠረ እንደሆነም ደጀ-ሰላም አስፍሯል።መንግሥት በነባር አገራዊ ቤተ እምነቶች ላይ እያስፋፋ የመጣው ጣልቃ ገብነት ድንበሩን አልፎ የእስልምና መሪዎችን በማሰር እና  የቤተ ክርስቲያናችን ሲኖዶስ በመዘወር መገለጡ ይታወቃል ብሏልም።መንግሥት ለባለሥልጣኖቹ የሚሰጠውን ሥልጠና ለማወቅ ለሚፈልጉ  ሁሉ ወደፊት እንዳስፈላጊነቱ ሙሉ ዶኩመንቱን ለማቅረብ እንደሚሞክር ድረ-ገጹ ገልጿል።

ፓሊሶች በአራት ኪሎ የሚገኙ ቤቶችን በእሳት አቃጠሉ


ለረጅም አመታት በአራት ኪሎ አካባቢ የኖሩ  ሰዎች ቦታው ለሼራተን ሆቴል ማስፋፊያ ይፈለጋል በሚል ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ሲነገራቸው እንደቆየ የተናገሩት አይን እማኞች፣ ነዋሪዎቹ በበኩላቸው መንግስት ተተኪ ቤት እስካልሰጣቸው ድረስ አካባቢውን ለቀው እንደማይሄዱ ሲከራከሩ ቆይተዋል። ዛሬ ጧት ወደ አካባቢው ያቀኑት ፖሊሶች ነዋሪዎቹ እቃዎቻቸውን ሳያወጡ በቤታቸው ላይ እሳት በመልቀቅ ቤታቸውን አቃጥለውባቸዋል። ነዋሪዎቹ በጩሀት ወደ ፓርላማ በመሄድ አቤት ቢሉም ሶስት ሰዎችን በመወከል ችግራቸውን እንዲያቀረቡ ተነግሮአቸዋል። ፖሊሶች ወደ አካባቢው በመድረስ ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩ ነዋሪዎችን አባረዋቸዋል።
አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የአይን ምስክር ለኢሳት እንደገለጡት፣ ተማሪዎች ደብተራቸውን እንኳን ሳያወጡ ቤታቸው እንደተቃጠለባቸው፣ ብዙዎችም በከፋ ችግር ላይ መውደቃቸውን ገልጸዋል።
በኢትጵያ ውስጥ በልማት ስም እየተበራከተ የመጣውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አለማቀፍ ሰብአዊ መብት ተማጓች ድርጅቶች ችላ እንዳሉት ተመልክቷል። በአላማጣ ላለፉት አንድ ወራት የከተማው ህዝብ በልዩ ፖሊሶች ሲዋከብ እንደነበርመዘገባችን ይታወሳል። በአዲስ አበባ ላፍቶ ክፍለከተማ ቤታቸው የፈረሰባቸው በርካታ ነዋሪዎች አሁንም በከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

    ፓሊሶች በአራት ኪሎ የሚገኙ ቤቶችን በእሳት አቃጠሉ


    ለረጅም አመታት በአራት ኪሎ አካባቢ የኖሩ  ሰዎች ቦታው ለሼራተን ሆቴል ማስፋፊያ ይፈለጋል በሚል ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ሲነገራቸው እንደቆየ የተናገሩት አይን እማኞች፣ ነዋሪዎቹ በበኩላቸው መንግስት ተተኪ ቤት እስካልሰጣቸው ድረስ አካባቢውን ለቀው እንደማይሄዱ ሲከራከሩ ቆይተዋል። ዛሬ ጧት ወደ አካባቢው ያቀኑት ፖሊሶች ነዋሪዎቹ እቃዎቻቸውን ሳያወጡ በቤታቸው ላይ እሳት በመልቀቅ ቤታቸውን አቃጥለውባቸዋል። ነዋሪዎቹ በጩሀት ወደ ፓርላማ በመሄድ አቤት ቢሉም ሶስት ሰዎችን በመወከል ችግራቸውን እንዲያቀረቡ ተነግሮአቸዋል። ፖሊሶች ወደ አካባቢው በመድረስ ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩ ነዋሪዎችን አባረዋቸዋል።
    አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የአይን ምስክር ለኢሳት እንደገለጡት፣ ተማሪዎች ደብተራቸውን እንኳን ሳያወጡ ቤታቸው እንደተቃጠለባቸው፣ ብዙዎችም በከፋ ችግር ላይ መውደቃቸውን ገልጸዋል።
    በኢትጵያ ውስጥ በልማት ስም እየተበራከተ የመጣውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አለማቀፍ ሰብአዊ መብት ተማጓች ድርጅቶች ችላ እንዳሉት ተመልክቷል። በአላማጣ ላለፉት አንድ ወራት የከተማው ህዝብ በልዩ ፖሊሶች ሲዋከብ እንደነበርመዘገባችን ይታወሳል። በአዲስ አበባ ላፍቶ ክፍለከተማ ቤታቸው የፈረሰባቸው በርካታ ነዋሪዎች አሁንም በከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

    ልማታዊው ኪስ አውላቂ (ክንፉ አሰፋ)


    ማስታወሻ፡  ባለፉት ጊዚያት በጫጫርኳቸው አጫጭር ጽሁፎቼ፤ ገንቢ ትችቶች ለላካችሁልኝ አንባብያን ሁሉ ምስጋናዬ የላቀ ነው። በአንጻሩ አፍራሽ ትችቶች በስማችሁ ጽፋችሁ የላካችሁልኝ ወገኖችንም አደንቃለሁ። ነገር ግን በብእር ስም ራሳችሁን በመደበቅ፤ ነውር እና አሳፋሪ የሆነ የፈጠራ ስራ ለምትሰሩ ደግሞ፡ ልቦና ይስጣችሁ ከማለት ውጭ የምለው የለም። ሰውን ዘልፎ ለመጻፍ እንቅልፋቸውን የሚያጡ ሰዎችን ፈረንጆቹ ‘ባለ ትንሽ ጭንቅላቶች’ ይሏቸዋል። ችግሩ ከአስተዳደግ ጉድለት፣ ከአስተሳሰብ ድህነት እና በራስ ካለመተማመን የሚመጣ የስነልቦና በሽታ ነው።
    ክንፉ አሰፋ
    የ ‘ህዳሴው ቦንድ’ ግዢ ግርግር ሞቅ ብሎ በነበረበት ሰሞን ይነገር የነበረ አነድ ቀልድ አለ። የ‘ማረሚያ’ ቤት ፖሊሶች እና ታጋዮች 500 ብር በሰረቀ ሌባ ላይ ውይይት ያደርሉ። ተከሳሹ ብሩን ያላግባብ ይስረቅ እንጂ በገንዘቡ የህዳሴውን ቦንድ መግዛቱ ነው ጉዳዩን ለውይይት የዳረገው።  ይህ ሌባ መታሰር የለበትም የሚሉት ታጋዮች፡ ለፖሊሶቹ ያቀረቡት መከራከሪያ ነጥብ ልማታዊ ሃሳብ ነበር። እንዲህ ነበር ያሉት፡ ‘ይህ ልማታዊ ኪስ አውላቂ ነው። እንዲያውም እንደዚህ አይነቶቹን ሌቦች የበለጠ እንዲሰሩ ማበረታታት ነው ያለብን።…’  ሁሉም በዚህ ሃሳብ ተስማሙና ሌባውን በያዘው ልማታዊ ተግባር የበለጠ እንዲሰራበት መክረው ለቀቁት።
    ይህ እነግዲህ ቀልድ ነው። ቀልድ ደግሞ በመጠኑም ቢሆን የእውነታ ነጸብራቅ እነጂ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ክስተት አይደለም። ‘ልማታዊ’ የሚለው ቃል ትርጉሙ ተዛብቶ ምን ያህል እየተቀለደበት መሆኑን ከዚህ ቀልድ ግንዛቤ እንወስዳለን። በዚህ ላይ ወደሗላ እመለስበታለሁ።
    ቀልዱን በቀልድ እንለፈውና አንድ ምሽት በኢ.ቲ.ቪ. ያየሁትን እውነታ ላውጋችሁ። ኢ.ቲ.ቪ. በሚያዘጋጀው የትምህርት ቤቶች ጥያቄና መልስ ውድድር ላይ ‘ቦንድ ማለት ምን ማለት ነው?’ የሚል የ500 ብር ጥያቄ ቀርቦ ነበር። ከተወዳዳሪዎቹ አንዱ መልስ ሰጠ። እነዲህ ሲል፣ “ቦንድ ማለት፡ መንግስት በህዝብ እጅ ያለውን ጥሬ ገንዘብ ለአንድ አላማ ወደ ባንክ እንዲገባ ለማድረግ የሚጠቀመበት ዘዴ ነው።”
    “ጥያቄው በትክክል ተመልሷል!” የሚል መልስ ነበር ህዘብ ከጠያቂ ጋዜጠኛው ይጠብቅ የነበረው። ጠያቂው ግን ተወዳዳሪው ትክክል እንዳልመለሰ ተናግሮ፡ ጥያቄውን ተመልካቾች  እንዲመልሱለት ጋበዘ። አነዱ ‘ልማታዊ’ ተመልካች ከመሃል ተነስቶ “ትክክል” የተባለለትን መልስ ሰጠ። መልሱ ይህ ነበር፣  “ቦንድ ማለት ወለዱ ከግብር ነጻ የሆነ የቁጠባ ዘዴ ነው። ”
    በዚህ ልማታዊ ጋዜጠኛ የተሳሳተ የቦንድ ትርጉም ተወዳዳሪ ተማሪው ብቻ ሳይሆን፤ የቴሌቭዥኑ ታዳሚዎችና ተመልካቾችም በሙሉ ቀልጠዋል። ይህ ጥያቄ በትምህርት ቤት ፈተና ላይ ቢመጣ ተመሳሳይ ‘ልማታዊ’ መልስ ያልሰጡ ተማሪዎች አያልፉም ማለት ነው።

    Tuesday, January 22, 2013

    የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞችን እያበረረ በኢህአዴግ አባላት እየሞላ ነው


    በአየር መንገዱ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጹት በኢህአዴግ አባሉ ስራ አስኪያጅ በአቶ ተወልደ ገብረማርያም ፣ በተጠባባቂው ስራ አስኪያጅ በአቶ ኢሳያስ ወልደማርያም እና በኦዲተሩ በአቶ ዋሱ ዘለለው አነሳሽነት ነባር ሰራተኞች ከስራ እየተቀነሱ  በኢህአዴግ የወጣት ፎረም አባላት እየተተኩ ነው። በቅርቡ 36 የትኬት ሽያጭ ሰራተኞች እና 14 ኤጀንቶች ከስራ ተባረው በፎረሙ አባላት ተተክተዋል።  ከእነዚህም መካከል 5 የትኬት ሰራተኞች እና 14 በተለያዩ ሀላፊነት ላይ ያሉ የድርጅቱ ሰራተኞች በሰበብ አስባቡ ወደ እስር ቤት እንዲላኩ መደረጉን የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።
    ከተባረሩት ሰራተኞች መካከል ኢማም ያሲን፣ ሳሙኤል እንዳለ፣ ቤተልሄም ጌታቸው፣ ኤደን በየነ፣ የአመቱ ምርጥ የትኬት ሽያጭ ኤጀንት ተብሎ የተሸለመው ይርጋለም ታደሰ፣ ቤተልሄም ተፈራ፣ ኤደን ካሳየ፣ ቤዛዊት ኤፍሬም፣ አንተንሳይ አማረ፣ ሰለሞን በቀለ ይገኙበታል።
    ከታሰሩት ሰራተኞች መካከል ደግሞ ሳሙኤል እንዳለ፣ አማኑኤል ጸጋው፣ ብርሀኑ ሰለሞን፣ እኑ ገብረእግዚአብሄር፣ አይዳ ዘልኡል፣ እና በረከት ግርማ የሚገኙበት ሲሆን፣ በረከት ግርማ ስራውን ለቆ በቱርክ አየር መንገድ ውስጥ ተቀጥሮ በማገልገል ላይ ሳለ የፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር አውለውታል።
    ከስራ ከታገዱት መካከል ትንግርት ደምሴ፣ ዳንኤል ገበየሁ፣ ሀይማኖት ንጉሴ፣ ሳምራዊት ገረመው፣ ሜላት አስራት፣ አማኑኤል በልስቲ፣ አማኑኤል ነጋሽ፣ ክንፈ ሚካኤል ሽጉጤ፣ አንዱአለም ግርማ ይገኙበታል።
    ከተባረሩት፣ ከታገዱትና ከታሰሩት መካከል ከ10 እሰከ 30 አመታት የሰሩ ነባር አየር መንገዱ ሰራተኞች የሚገኙበት ሲሆን፣ የተባረሩበት ወይም የታገዱበት ምክንያትም የኢህአዴግ አባል እንዲሆኑ ተጠይቀው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው መሆኑን ሰራተኞች ይገልጻሉ።
    አቶ ተወልደ ገብረማርያም የኢትዮጵያን አየር መንገድ በስራ አስኪያጅነት  ለመምራት ስልጣኑን ከተረከቡ በሁዋላ፣ በተለያዩ መንገዶች የኢህአዴግ የወጣት አደረጃጀት አባላት በድርጅቱ ውስጥ በስፋት እንዲቀጠሩ አድርገዋል።
    እቃዎችን በማውረድና በመስቀል ስራ ላይ የስሩ የነበሩ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ተባረው በኢህአዴግ ወጣት ፎረም አባላት እንዲተኩ ማድረጋቸውን ከወር በፊት መዘገባችን ይታወሳል። 

    Monday, January 21, 2013

    ልዩ ሀይል በአላጣማ መግባቱን ተከትሎ በከተማው ያለው ውጥረት አይሏል


    የኢሳት የአላማጣ ምንጮች እንደተናገሩት በዛሬው እለት በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 12 ሰአት አካባቢ ከመቀሌ የተነሱ በ3 መኪኖች የተጫኑ ልዩ የፌደራል ፖሊስ አባላት አላማጣ በመግባት ህዝቡን እያሸበሩት ነው።
    በከተማዋ ጋርቬ እየተባለ በሚጠራው  አካባቢ የሚገኙ 200 የሚጠጉ የቤት ባለንብረቶች ንብረቶቻቸውን ነገ ማክሰኞ የማያወጡ ከሆነ ፣ ቤቶቻቸው በዶዘሮች እንደሚፈርሱ ንብረቶቻቸውም እንደሚወረሱ እንደተነገራቸው ታውቋል። ልዩ የፖሊስ ሀይላትም ተቃውሞ ሊያነሱ ይችላሉ ብለው የሚጠሩዋቸውን አካባቢዎች እያሰሱ ሲያስጠነቀቅ አምሽተዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ይፈርሳሉ ተብለው የተመዘገቡት ቤቶች 2 ሺ ናቸው።
    “ከፍተኛ ውጥረት አለ፣ ልዩ ሀይሎች ህዝቡን እያሸበሩት ነው፣ በነገው እለት ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል፣ በከተማዋ ሁለት ሶስት ሆኖ ማውራት አይቻልም”  በማለት አንድ ነዋሪ ተናግረዋል።
    ባለፈው ጥር መግቢያ ላይ በከተማዋ ከፍተኛ ተቃውሞ ተነስቶ እንደነበር ይታወሳል። በወቅቱ ተይዘው የታሰሩ የከተማ ታዋቂ ሰዎች እስካሁን አለመፈታታቸው ታውቋል።
    ይህ በእንዲህ እንዳለ በክብሮም አሰፋ ሞላ የተጻፈው “የራያ ህዝብ ባህልና ታሪክ ” መጽሀፍ እንዳይሸጥ ተከልክሎአል። መፅሀፉ ለምን እንዳይሸጥ እንደተከለከለ ለማወቅ ያደረግነው ሙከራ ባይሳካም አንዳንድ ወገኖች እንደጠቆሙት መጽሀፉ ህወሀት ስለራያ ህዝብ ማንነትና ታሪክ ከሚሰጠው ትንተና ጋር የሚቃረኑ ትንታኔዎችን ይዟል።

    Sunday, January 20, 2013

    መነቀል ያለበት ስር የሰደደ የወያኔ ዘረኝነት

    የግንቦት 7 ንቅናቄ

    ዘረኛዉ የወያኔ ስርአት የኢትዮጵያን ህዝብ ለጥቂት አመታት ኢትዮጵያዊያንን ባሰረና በገደለ ቁጥር ገንዘብ የሚሰጡትን አለም አቀፍ ድርጅቶችና አርዳታ ሰጪ አገሮች ደግሞ 21 አመት ሙሉ ካታለለበት መንገድ አንዱ የፌዴራል ስርአት መስርቼ ኢትዮጵያን የእኩሎች አገር አደረኳት የሚለዉ ባዶ አባባሉ ነዉ። ይህንን ተጋልጦ እርቃኑን የቀረ አባባል የኢትዮጵያ ህዝብ ተገንዝቦ ወያኔን መታገል ከጀመረ ቆይቷል፤ ዋና ዋናዎቹ እርዳታ ለጋሾችም ቢሆኑ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነት ግድ የሌለዉ ወያኔ ወጣቶቻችንን እየገበረ ጥቅማቸዉን ስለሚያስከብርላቸዉ ነዉ እንጂ ወያኔ እንኳን እየደገፉ እርዳታ የሚሰጡት በአንድ ተርታም አብረዉ ለመቀመጥ የማይመች የእኩዮች ስብስብ እንደሆነ ካወቁ ቆይቷል።

    ህወሀት በፌዴራል ስርአቱ ዉስጥ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ምልክት ነዉ ብሎ በሚጠራዉ ፓርላማ ዉስጥ ያለዉ መቀመጫ 8 ብቻ ነዉ። እዚህ ፓርላማ ዉስጥ የትግራይን ህዝብ እወክላለሁ የሚለዉ ህወሀት ነዉ፤ ትግራይ ደግሞ ኢትዮጵያ ዉስጥ አንድ ክልል ናት። የተቀሩት 8 ክልሎች በዚህ የእኩልነት ምልክት በሆነዉ ፓርላማ ዉስጥ ያላቸዉ የመቀመጫ ብዛት 569 ነዉ። ሆኖም በወያኔ መንደር የፖለቲካ ስልጣን ምንጭ ህዝብ ሳይሆን ጠመንጃ ነዉና ወያኔ ፓርላማዉ  ዉስጥ 8 ወንበር ብቻ ይዞ 569 ወንበር ያላቸዉን የኦሮሚያን፤ የአማራን፤ የደቡብ ክልልንና የተቀሩትን አምስት ክልሎች እንደ መኪና ይነዳቸዋል። የየክልሉን መሪ ይሾማል፤ ይሽራል ወይም የማይስማማዉን የክልል ባለስልጣን ያስራል። ፓርላማዉ ዉስጥ አንድ መቶ ሰባ ስምንት፤ አንድ መቶ ሰላሳ ስምንትና አንድ መቶ ሀያ ሦስት መቀመጫ ያላቸዉ የኦሮሚያ፤ የአማራና የደቡብ ክልል ፓርቲዎች በራሳቸዉ ጉልበትም ሆነ ህልዉና ስለሌላቸዉ አንዱ ከሌላዉ የበለጠ ስልጣን ወይም ሹመት ለማግኘት አንጋጥጠዉ ወደ ላይ የሚመለከቱት ህወሀትን ነዉ።
    ለመሆኑ ወያኔ የፌዴራል ስርዐት መስርቼ የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት አረጋገጥኩ ሲል ምን ማለቱ ነዉ? እኩልነቱ የፖለቲካ ነዉ  የኤኮኖሚ? ወይስ በየአመቱ ህዳር ወር ላይ የፌዴራልዝም ቀን ሲከበር እንደምናየዉ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት የተረጋገጠዉ በዘፈን ብቻ ነዉ? የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስርዐት ከላይና ከታች የሚቆጣጠረዉና ይህንኑ የፖለቲካ ስርአት የሚደግፍ የኤኮኖሚ መዋቅር ዘርግቶ የአገራችንን ኃብት የሚቦጠብጠዉ ህወሀት ብቻ ነዉና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ተረጋገጠ የሚባለዉ አባባል ከተራ የቃላት ድርደራ ዉጭ ሌላ ምንም ትርጉም የለዉም።
    አፄ ቴዎድሮስን እንደ ልጅነት ሞዴሉ የሚመለከተዉ ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማሪያም የመጀመሪያዉን የኢትዮጰያ ዘመናዊ ወታደራዊ እንጂኔሪንግ ተቋም ሲመሰርት ስሙን “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ብሎ ነበር የሰየመዉ። ስያሜዉ የአፄ ቴዎድሮስ ስራና ስም ህያዉ ሆኖ እንዲኖር ለማድረግ የተደረገ ሙከራ እንደነበር ግልጽ ነዉ። የኢትዮጵያን የቀድሞ መሪዎች በጅምላ የሚዘልፈዉ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት ከአንዲት የአገር ዉስጥ ጋዜጠኛ ጋር ባደረገዉ ቃለ ምልልስ አፄ ቴዎድሮስ ጋፋት ላይ ያሰሩትን መድፍና መንግስቱ ኃ/ማሪያም “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ብሎ  የሰየመዉን ወታራዊ ተቋም አስመልክቶ ሁለቱንም መሪዎች ሲያንቋሽሽ ተደምጧል። የሚገርመዉ ዛሬ ወያኔ የብረታብረት እንጂኔሪንግ ኮረፓሬሺን ብሎ የሚጠራዉ ግዙፍ የሲቪልና ወታደራዊ እንዱስትሪ ተቋምና በዚህ ተቋም ዉስጥ የሚገኙ ዋና ዋና ፋብሪካዎች ደርግ  “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ብሎ የጀመራቸዉ የከባድ እንዱስትሪ ጅምሮች ናቸዉ። በ1970ዎቹ አጋማሽ ላይ “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ስራዉን ሲጀምር የፋብሪካዉ ሀላፊዎች፤ እንጂኔሮች፤ የመምሪያ ሀላፊዎችና ቴክኒሺያኖች የስራ ዕድል የሚያኙት የትምህርት ደረጃቸዉ፤ ችሎታቸዉና የሰራ ልምዳቸዉ ብቻ እየታየ ነበር፤ ወይም ትግርኛ ስለተናገረ ስራ የሚከለከል አማርኛ፤ ኦሮምኛ ወይም ሌላ ቋንቋ ስለተናገረ አድሎ የሚደረግለት ዜጋ አልነበረም። ዛሬ ወያኔ ከደርግ ስርአት ተረክቦ የብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን ብሎ በሰየመዉ እንዱስትሪ ዉስጥ አብዛኛዉን የሀላፊነት ቦታ የያዙ ሰዎች ለቦታዉ የበቁት በስራ ልምዳቸዉና ችሎታቸዉ ሳይሆን የተወለዱበት ዘርና የሚናገሩት ቋንቋ እየታየ ነዉ። ወታራዊዉ አምባገነን ደርግም ሆነ  ወያኔ ይህንን እንዱስትሪ የወደፊቱ የኢትዮጵያ ከባድ እንዱስትሪ ዘርፍ መሰረት ይሆናል የሚል ራዕይ ነበራቸዉ። ልዩነታቸዉ የእንዱስትሪዉ አስፈላጊነት ላይ ሳይሆን እንዱስትሪዉን ማን ይቆጣጠረዋል የሚለዉ ጥያቄ ላይ ነዉ። ደርግ በሱ መሪነት ለማንም ችሎታ ላለዉ ኢትዮጵያዊ የእንዱስትሪዉን በር የከፈተ ሲሆን ወያኔ ግን እንዱስትሪዉ እንዳለ በአንድ ዘር ቁጥጥር ስር እንዲገባ አድርጓል።  ደርግም ወያኔም አምባገነኖች ስለሆኑ አንዱስትሪዉን ከህዝብ ቁጥጥር ዉጭ አድርገዉታል፤ ወያኔ ግን ከአምባገነንም የጎሳ አምባገነን ስለሆነ ይህንን ትልቅ እንዱስትሪ ሙሉ በሙሉ በትግርኛ ተናጋሪዎች ቁጥጥር ስር አድርጎታል።
    ግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ባለለፉት ሦስት አመታት ይህንን ወያኔ ገነባሁ የሚለዉን የፌዴራል ስርአትና በስርአቱ ዉስጥ የተለያዪ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የሚጫወቱትን ሚና በመረጃ አስደግፎ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ አቅርቧል። የዛሬ ሁለት አመት ግንቦት ሰባት በኢትዮጵያ መላከያ ሰራዊት ዉስጥ የተዘረጋዉን የወያኔ የዘረኝነት መረብ ከሰሞኑ ደግሞ የኢትዮቴሌኮምን የዘረኝነት አደረጃጀት በመረጃ በማስደገፍ ለህዝብ ማቅረቡ ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮረፓሬሺንን የዘረኝነት አደረጃጀትና በዚህ አደረጃጀት ዉስጥ ማን ምን እንደሆነ ያጣናዉን የጥናት ዉጤት በመረጃ አስደግፎ ያቀርባል።  ግንቦት ሰባት ሃያ አራት ሰአት ሙሉ የሚከታተሉትን የወያኔ የደህንነት ሰራተኞች ከበባ ጥሶ የወያኔን ዘረኝነት የሚያጋልጡ መረጃዎችን ከራሱ ከወያኔ ጓዳ እየጎተተ አዉጥቶ ለህዝብ የሚያቀርበዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔን ዘረኝነት አያውቀዉም በሚል አስተሳሰብ አይደለም። ግንቦት ሰባት ኢትዮጵያ ዉስጥ ወያኔ የፈጠረዉ ከፍተኛ የመረጃ ጉድለት አለ ብሎ ያምናል፤ስለሆነም ህዝቡ የወያኔን ዘረኝነት ቢረዳም መጠኑን፤ስፋቱንና ጥልቀቱን በሚገባ ላያዉቅ ይችላል ብለን እናምናለን። በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በየቀኑ ደሙን እንደ መዥገር የሚመጠዉን ወያኔን የመሰለ የጀርባ ላይ አጥንት ተሸክሞ መኖር የለበትም ብለን ስለምናምን ህዝብን ለትግል ከምናዘጋጅበትና ከምናነሳሳባቸዉ መንዶች ዉስጥ አንዱ እንደዚህ ህዝብ በገዛ አገሩ “እኩል አደረግንህ” ብለዉ በሚነግሩት ከሀዲዎች ቅኝ አገዛዝ እየተገዛ መሆኑን በማሳወቅ ነዉ።
    ባለፈዉ ሳምንት የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን ዋና ዳይረክተር ብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘዉ ፓርላማ ዉስጥ ተገኝቶ የኮርፓሬሺኑን የሁለት አመት የስራ ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ኮርፓሬሺኑ የግል ባለኃብቶችን አያሳትፍም እንዳዉም እያቀጨጫቸዉ ነዉ፤ ለሙስና የተጋለጠ ነዉ፤ ደግሞም አብዛኛዉ የኮርፖሬሺኑ ሰራተኛ የመከላከያ ሰራዊት አባል ነዉና ይህ አሰራር  ሠራተኞችን ለማስተዳደር አስቸጋሪ አይሆንም ወይ የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበዉለት ነበር። የግሉን ዘርፍ መቅጨጭ በተመለከተ ኢትዮጵያ ዉስጥ ቀድሞዉንም ቢሆን “የወያኔ ዘርፍ” እንጂ የግል ዘርፍ የሚባል ነገር የለምና ጥያቄዉ መቅረብም አልነበረበትም።  ሙስናም ቢሆን የወያኔ ስርዐት ዋናዉ መገለጫ ባህሪይ ስለሆነ ወያኔ እስካልተወገደ ድረስ ሙስና  “ሙስናን እናጠፋለን” ስለተባለ ብቻ የሚጠፋ ነገር አይደለም። ግንቦት ሰባትን እጅግ በጣም ያሳዘነዉና ያስገረመዉ ነገር ያንን ወያኔ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ምልክት ነዉ ብሎ የሚናገርለትን ፓርላማ ያስጨነቀዉ (ተጨንቆ ከሆነ) የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን በአንድ አናሳ ብሔረሰብ ሙሉ ቁጥጥር ስር መዉደቁ ሳይሆን አብዛኛዉ የኮርፖሬሺኑ ሰራተኞች የመከላከያ ሰራዊት አባላት መሆናቸዉ ነዉ። በእርግጥ የአንድ ትልቅ ኮርፖሬሺን ሰራተኞች በአብዛኛዉ  የጦር ሠራዊት አባላት ሲሆኑ የአሰራርና የአስተዳደር ችግር መፈጠሩ አይቀርም፤ ሆኖም የሠራዊቱ ታማኝነት  ለህዝብ ታዛዥነቱ ደግሞ ለህገ መንግሰስቱ ብቻ ቢሆን ኖሮ ይህ ችግር በቀላሉ የሚወገድ ችግር ይሆን ነበር።

    ፍረደም ሐውስ የ 2013 ኢትዮጵያ ነጻነት የሌለባት ናት አለ

    በአለም ላይ ያሉ አገሮችን ነጻነት ( ፍሪደም) በማወዳደር ሪፖርቱን የሚያወጣው አለማቀፋዊ እውቅና ያለው ፍሪደም ሀውስ የ2013 ሪፖርቱን ይፋ ሲያደርግ እንደገለጠው  ኢትዮጵያ ነጻነት የሌለባት አገር ናት ብሎአታል።
    ፍሪደም ሐውስ የአለም አገራትን ነጻነት የሰፈነባቸው ከፊል ነጻነት ያለባቸውና ነጻነት የሌለባቸው አገራት በማለት በሶስት ከፍሎ የተመለከተ ሲሆን ፣ ነጻነት የሌለባቸው አገራት ተብለው የተፈረጁት መሰረታዊ የሆኑት የፖለቲካ መብቶች የሌሉባቸው፣ እንዲሁም የሰቪል ነጻነቶች የተነፈጉባቸው አገሮች ናቸው።
    ኢትዮጵያ ነጻነት የሌለባቸው አገሮች ተብላ የተፈረጀችው በአገሩ የፕሬስ ነጻነትን ጨምሮ ሌሎች የሰብአዊ እና ፖለቲካዊ መብቶች ባለመከበራቸው ነው።
    በአፍሪካ ውስጥ ነጻነት የሰፈነባቸው ተብለው የተጠቀሱት አገሮች  ቤኒን፣ ቦትስዋና፣ ኬፕ ቨርዴ፣ ጋና፣ ሌሶቶ፣ ማሊ፣ ሞሪሺየስ፣ ናምቢያ፣ ሳኦቶሚና ፕሪንሲፒ እና ደቡብ አፍሪካ ናቸው።
    ነጻነት ከሌለባቸው አገሮች መካከል ኢትዮጵያ፣ አንጎላ፣ ካሜሩን፣ ቻድ፣ ሁለቱ ኮንጎዎች፣ ጅቡቲ፣ ኢኳቶሪያን ጊኒ፣ ኤርትራ፣ ጋቦን፣ ጋምቢያ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ማሊ፣ ሞሪታኒያ፣ ሩዋንዳ እና ሶማሊያ ይገኙበታል።
    ከአፍሪካ ቀንድ አገሮች በከፊል ነጻነት ያለባቸው ኬንያ እና ዩጋንዳ ናቸው።
    የህወሀት/ ኢህአዴግ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊ እና ፖለቲካ መብቶች መከበራቸውን በተደጋጋሚ ቢገልጽም፣ የፍሪደም ሐውስ ሪፖርት እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ በ እኤአ 2010 ከነበራት ከፊል ነጻ ደረጃ  ወደ ነጻነት ወደ ሌለባቸው አገራት ደረጃ መውረዷን ነው።

    የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን 70 በመቶው የአመራር ቦታ በህወሀት አባለት የተያዘ ነው ተባለ


    ግንቦት7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለኢሳት በላከው ሁለተኛ ጥናቱ ላይ እንዳመለከተው በ11 መምሪያዎች የተዋቀረው በስሩ አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱስትሪዎቸን የሚያስተዳደርው የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን አስራ አንድ ትላልቅ መምሪያዎችና አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱሰትሪዎች በዋና ሀላፊነት፤ በዳይሬክተርነትና በምክትል ዳይረክትርነት የሚመሩ በ29 የከፍተኛ አመራር አባላት ነው።
    ከእነዚህ 29 ከፍተኛ አመራር አባላት ዉስጥ 69 በመቶዉ ወይም ሃያዉ የህወሀት አባላት የሆኑ ወታደራዊ መኮንኖች ናቸዉ።በዚህ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች ያላቸዉ ቦታ 31 በመቶ ወይም ከእያንዳንዳቸዉ በቅደም ተከተል ሦስትና ስድስት ሰዎች ብቻ ሲሆን ከተቀሩት አምስት ክልሎች በዚህ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ የተመደበ አንድም  ሰዉ የለም ፣ እንደጥናቱ።
    ኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ እንዱስትሪ ለመገንባት በሚደረገዉ ጥረት ዉስጥ ከፍተኛዉን ሚና ይጫወታል የሚባለዉ የብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን በሲቪልና ወታራዊ መምሪያዎች ተከፋፍሎ የተዳራጀ ሲሆን በስሩ አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱስትሪዎች እንደሚገኙ የጠቀሰው ግንቦት7፣ ከአስራ ሦስቱ እንዱስትሪዎች ዘጠኙን የሚያስተዳድሩት የህወሀት አባላት ናቸዉ። በኮርፖሬሺኑ ዉስጥ ከፍተኛ ስልጣን ከተሰጣቸዉ የህወሀት አባላት መካከል ብረጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘዉ  የብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን ዋና ዳይሬክተር ፤ ኮ/ል ተከስተ ኃ/ማሪያም  በምክትል ዋና ዳይረክተር ማዕረግ የኮርፖሬት ፕሮዳክሺን ግንባታ ሀላፊ ፤ ኮ/ል ፀጋሉ ኪሮስ በምክትል ዋና ዳይሬክተር ማዕረግ የኮርፖሬት ወታደራዊ ምርቶች ሀላፊ ፤ ኮ/ል ሙሉ ወ/ሰንበት በምክትል ዋና ዳይረክተር ማዕረግ የኮርፖሬት ፕሮጀክቶች አስተደዳደር ሀላፊ፤ሻምበል ካህሳይ ክሽን የምርመራና ልማት ዳይረክተርና  ሻምበል ገ/ስላሴ ገ/ጊዮርጊስ የአቅም ግንባታና ስልጠና ማዕከል ዳይሬክተር ይገኙበታል።
    ከትግራይ ዉጭ ከሌሎቹ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔሰቦች በብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን እንዱስትሪዎች ዉስጥ ከፍተኛ የሀላፊነት ደረጃ ባለዉ የአመራር ቦታ ላይ የመቀመጥ ዕድል ያገኙ ኢትዮጵያዉያን ቁጥር አራት ብቻ ናቸው። ኬሚካልና ሴንተቲክ እንዱስትሪ ሃለፊ መ/አ ሰለሞን ዘውዴ፣ አዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ ሃለፊ ኮ/ል ፍሰሀ ግደይ፣ ሜታልስ እንዱስትሪ ሃለፊ ሻለቃ መኮንን በላይ፣ ፓወር እንዱስትሪ ሃለፊ፣ ሻምበል አሰፋ የሀንስ፣ ሆሚቹ ኢሚዩኔሽን ኢንጂነሪንግ ሃለፊ ኮ/ል ሀድጉ በላይ፣ ህብረት ማሽን ቱል ኢንጂነሪንግ ሃለፊ፣ ሻምበል ተሰማ ግደይ፣ ቢሾፍቱ አቶሞቲቭ ሎኮሞቲቭ ሀላፊ፣ ኮ/ል ገብረመድህን ገ ስላሴ ፣ የደጀን አቪየሽን እንዱስትሪ ሀላፊ ሳለቃ ኢሉ ጸጋየ እንዲሁም የጋፋት አርማመንት እንዱስትሪ ሀላፊ ሻለቃ ግሩም ገብረመድህን የህወሀት አባላት ትጋረይ ተወላጆች መሆናቸው በጥናቱ ተመልክቷል። የኢትዮ ፕላስቲክ እንዱስትሪ ሃለፊ አቶ ጋሻው እምሩ፣ እርሻ መሳሪያዎች እንዱስትሪ ሃለፊ ኮሎኔል ደሴ ዘለቀ እና የሀይቴክ እንዱሰትሪ ሀላፊ ኮ/ል ጸጋየ አንሙት የአማራ ተወላጆች ሲሆኑ፣ ከኦሮሞ ደግሞ የፋብሪኬንና ስትራክቸራል እንዱስተሪ ሀላፊው ኮ/ል ብቂላ ብቻ ተጠቅሰዋል።
    ይህ ጥናት የተጠናዉ ከ2004 እስከ 2005 ዓም ባለዉ የአንድ አመት ግዜ ዉስጥ መሆኑን ተጠቅሷል። ግንቦት7 በቅርቡ በኢትዮቴልኮም ውስጥ ያለውን የብሄር ተዋጽኦ ይፋ ማድረጉን መዘገባችን ይታወሳል።
    የኢትዮጵያ መንግስት ሰዎቹ የሚሾሙት በዘራቸው ሳይሆን በችሎታቸው ነው በማለት ይከራከራል። መንግስት 7ኛውን የብሄር ብሄራሰቦች ቀን 200 ሚሊዮን ብር በማውጣት በባህርዳር ማክበሩ ይታወሳል።