Thursday, October 25, 2012

በአባቶች መሀከል የሚካሄደው እርቅ በቀጣዩ ወር ይቀጥላል ተባለ


ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ የተጀመረው የቀዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ባጸደቃቸው አጀንዳዎች ላይ ውይይቱን ቅጥሏል።የእርቁ ሂደት በቀጣዩ ወር እንዲቀጥለም ወስኗል።ሰኞ ዕለት የተጀመረው የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከቀረጻቸው አጀንዳዎች የፓትሪያሊክ መርጫ ህግ ማውጣት አንዱ መሆኑ ተመልክቷል፤ደጀሰላም እንደዘገበው ከፍተኛ የገንዘብ ብክለት የተመዘገበባቸው የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሰራ አስኪያጅ ንብረእድ ኤልያስ አብርሃ ከሃላፊነታቸው የመነሳታቸው ጉዳይ እያበቃለት መምጣቱን አመልክቷል። ቅዱስ ሲኖዶሱም የ አዲስ አበባ ሐገረ ሰብከት በአናት እንዲከፈል መወሰኑንም ይፋ አደርጓል።የፊታችን ህዳር በዩናይተድ እስቴት አሜሪካ በሚካሄደው የእርቅ ድርድር ላይ የሚሳተፉ ልኡካንንም ቅዱስ ሲኖዶሱ መሰየሙንም ደጀሰላም ዘግቦል። ብጹእ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብጹእ አቡነ አትናትዎስ፣ እና ብጹእ አቡነ ገሪማ ለእርቁ ሂደት የተወከሉ ሲሆን ንቡረእድ ኢሊያስ አብርሀ በጸሀፊነት ከለኡካን ቡድኑ ጋር እንዲጎዙ መወሰኑንም በዘገባው ተመልክቶል።አዲስ አበባ በሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ የሚገኙት አባታቶች በእርቀ ሰላሙ ጉዳይ ተመሳሳይ አቆም መያዛቸው ተሰምቶል። ሆኖም አቡነ ምውርቆሪዎስ በፓትሪያርክነት መንበራቸው እንዲመለሱ የሚጠይቁ በአንድ ወገን ሲኖሩ በሌላ ወገን የፓትሪያርክ አቡነ መቆሪዎስ ስም በቅዳሴ እየተጠራ ወደሀገራቸው ተመልሰው በፈቀዱት ስፍራ እንዲቀመጡ ሆኖም የቀጣዩ ፓትርያርክ ምርጫ እንዲካሄድ የሚል አቆም መንጸባረቁም ተመልክቶል።

No comments:

Post a Comment