Tuesday, November 13, 2012

በደራ ወረዳ አንዲት ሴት የባሉዋን ብልት በአደባባይ በገመድ እንድትጎትትና እንድትስም ተደረገ


ኢሳት ዜና:-በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ በገብሮ ቀበሌ የወረዳው የአስተዳደርና ፍትህ ሀላፊ የቅርብ ዘመድ የሆነ አቶ አየለ የተባለ ከሌሎች ሁለት ግብረ አበር ፖሊሶች ጋር በመሆን በቀበሌው የሚኖርን አንድን ግለሰብ መሳሪያ ደብቀሀል በሚል ሰበብ ግለሰቡንና ባለቤታቸውን ልብሳቸውን በማስወለቅ እርቃናቸውን እንዲታሰሩ አድርገዋል።
 የሚሊሺያ ዘርፍ ሀላፊውና ፖሊሶች በመቀጠልም ባልየው ብልቱ በገመድ እንዲታሰር ካስደረጉ በሁዋላ ህዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ እርቃኑዋን የሆነቸው ባለቤቱ ብልቱን በገመድ እንድትስብ እንዲሁም ብልቱን እንድትስም አስደርገዋል። በእርግጫ በመመታቱዋም የስድስት ወር ልጅ አስወርዳለች። በድርጊቱ አልሳቃችሁም የተባሉትም ተደብድበዋል።
ድርጊቱ ይፋ የሆነው አቶ ይመሩ በተባሉ የቀበሌው የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊ ሲሆን፣ ድርጊቱንም ይፋ ያደረጉት የዞኑና የወረዳው ባለስልጣናት በተሰበሰቡበት ወቅት ነው።
 ኢሳት ጥቆማው እንደደረሰው በስብሰባው ላይ የተሳተፉትን  አንድ የወረዳው ባለስልጣንን አነጋግሯል፡፤ ባለስልጣኑ ስማቸው እንዳይጠቀስባቸው በመግለጽ ስለ ተፈጸመው ድርጊት በዝርዝር አስረድተዋል።
የፖሊስ ምርመራ ክፍል የሀኪም ማስረጃዋን ለመቅደድ መሞከሩንና ድርጊቱም በተራው የኢህአዴግ አባላት ውስጥ ቁጣ መፍጠሩንም ባለስልጣኑ ተናግረዋል ።
ይህ ግለሰብ ባሂት በሚባለው ቀበሌ ደግሞ አንድን ግለሰብ በችቦ ማቃጣሉን ባለስልጣኑ ተናግረዋል::
የወረዳው የፍትህና አስተዳዳር ሀላፊ ከድርጊቱ ጀርባ እጁ እንዳለበትም ባለስልጣኑ ተናግረዋል::
 ግለሰቡ  በማዳበሪያ እና በሌሎችም ምክንያቶች እያሳበበ አባዎራዎችን ወደ እስር ቤት በመወርወር  እርሱና ጓደኞቹ ሚስቶቻቸውን እንደሚደፍሩም ታውቋል።

No comments:

Post a Comment