Wednesday, October 24, 2012

ከኦሮሞ ህዝብ ጀርባ...((ከተመስገን ደሳለኝ)


እንደ መግቢያ 
1975 ዓ.ም.፡፡ በመሀል ሀገር የነበረው የፖለቲካ ግለት ከብዙ ደም መፋሰስ በኋላ ወደ ጠረፍ እና የገጠር
ከተሞች አፈገፈገ፡፡ በ‹‹ምርጥ መኮንኖች›› የተመሰረተው መንግስትም አንፃራዊ ሰላም ያገኘ መሰለ፡፡ አስቀድሞ
‹‹ወታደራዊ ክንፍ›› አቋቁሞ የነበረው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) በሀገሪቱ ዋና ዋና
ከተሞች ለማቀጣጠል ሞክሮት የነበረው አብዮት ከፍተኛ ዋጋ አስከፍሎት ከሸፈ፡፡ ለክፉ ቀን ‹‹አማራጬ›› 
ያለው ወታደራዊ ክንፉም ቢሆን ለሶስት በመከፈሉ በእጅጉ ተዳከመ (ትግል በቃን ብለው ወደ ምዕራብ ሀገራት
ለመሰደድ በወሰኑ፣ ኢህአፓን ይዘን እስከመጨረሻው እንፋለማለን ባሉና ‹‹ኢህአፓ ዴሞክራት አይደለም›› 
በሚል ተገንጥለው ‹‹ኢህዴን›› የተባለ አዲስ ድርጅት በመሰረቱ) ከዚህ በተቃራኒው በመገንጠል እና በብሄር
ጥያቄ ዙሪያ የተሰባሰቡት ሻዕቢያ፣ ህወሓት እና በሽብርተኝነት የተፈረጀው ኦነግ የተሻለ ድርጅታዊ አቅም
መፍጠር ቻሉ፡፡
…በሁለት ወጣት ታጋዮች የሚመራ ከህወሓት የጦር ሰፈር (ደደቢት) የተነሳ አንድ ልኡክ ከኢትዮጵያ መንግስት የመረጃ ሰራተኞች እናየገጠር ካድሬዎች አይን ተሸሽጎ በከፍተኛ ጥንቃቄ ጉዞ ጀምሯል፡፡ መድረሻ ነጥቡ ‹‹ደባዜን›› የተሰኘች ከተማ ነች፡፡ ልኡኩ ከብዙ ቀናትበኋላ የኦሮሚያ ገጠር ከተማ በሆነችው ደባዜን ደረሰ፡፡ በወቅቱ ደባዜን የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር /ኦነግ/ ወታደራዊ ቤዝ ስትሆን ትግረኛተናጋሪ ታጋዮቹ ወደ አካባቢው የመጡት በድርጅታቸው ህወሓት እና ኦነግ መካከል በተፈረመ ስምምነት መሰረት ነው፤ የስምምነቱ ይዘት‹‹የህወሓት ታጋዮች ለኦነግ ታጋዮች ወታደራዊ ስልጠና እንዲሰጡ፣ ካድሬዎችን እንዲያነቁ እና ሁለቱ ድርጅቶች በትጥቅ ትግሉም ሆነከትጥቅ ትግሉ በኋላ በጋራ እንዲሰሩ›› የሚል ነው፡፡ ሆኖም በሁለት የህወሓት አመራር አባል የተመራው ልዑክ ደባዜን ከደረሰ በኋላከኦነግ የጠበቀው አቀባበል የስምምነቱ ተቃራኒ ሆነ፡፡

ኦነግ በግልፅ ከህወሓት የተላኩትን ‹‹መርሲነሪዎች›› (ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች) ሲል አውግዞ ከወታደራዊ ሰፈሩ በፍጥነት እንዲወጡ አደረገ፡፡ በሁለቱ የአመራር አባላት የተመራው ቡድንም ወደ ትግራይ ተመለሰ፡፡ የቡድኑ መሪዎችም መላው የህወሓት የአመራር አባላትበተገኙበት ሪፖርታቻውን አቀረቡ፡፡ ሁለቱ የአመራር አባላት ክንፈ ገ/መድህን እና ሙሉጌታ ጫልቱ ነበሩ፡፡ ከዚህ ሪፖርት በኋላምህወሓት ከኦነግ ጋር ለመስራት የነበረው ተስፋ መከነ፡፡

የኦሮሞን ድርጅት ፍለጋ

Tuesday, October 23, 2012

Ethiopia sacks the president of Somali Region


The Ethiopian federal government has sacked the president of the Somali regional state according to reports in the regional administrative capital Jigjiga.

The ouster of Abdi Mohamud Omar comes on the heels of growing local, regional and international accusations of widespread abuses in the region.
Mr Omar has been accused of torturing, killing and the disappearance of hundreds of Somali civilians in the restive region in eastern Ethiopia.
He is said to have been using the notorious and often lawless paramilitary Liyu Police and until recently no evidence of the abuses has reached the outside world. The Liyu police operate in the same manner as Sudan’s janjaweed militia who are said to be responsible for much of Darfur’s unrest.
Swedish Television released last month video evidence smuggled out of Ethiopia documenting and revealing gruesome human disaster of staggering proportions. Many villages in the Dagahbur district were leveled to the ground during 2010 operations.

Ginbot 7 urges Ethiopians to stand with Muslim brothers and sisters

Brutal Killings Inside Mosques Will Not Deter The Resolve Of The Ethiopian Muslim Community
Ginbot 7 Press Release
In the twenty one years of the TPLF rule, the Ethiopian people and the world at large have witnessed mass killings, targeted killings, and indiscriminate killings of the young, old, women and children as young as 8 years old. In 2005, the mass killing in Ethiopia reached its climax when special security forces under the direct order from the late Prime Minister Meles Zenawi savagely killed over 200 people as the world watched quietly. When Deputy PM Haile Mariam Desalegn took the oath of office and promised to walk on the same path as his predecessor, many Ethiopians lowered their expectation of witnessing a free, just and democratic Ethiopia in their life time.
In just a little over a month in office, PM Haile Mariam Desalegn has kept his promise of staying the course of his predecessor in gunning down peaceful demonstrators on the streets of Ethiopian cities. On Sunday, October 21, 2012, Haile Mariam Desalgen mercilessly took the lives of his first four victims in a standoff that started inside a Holy Mosque in the Amhara zone. Two of his young victims were frog marched by security forces and shot execution style at the nearby police station while the other two were shot and killed inside the Mosque compound. According to reliable local sources, there are many people who are seriously wounded and the death toll may increase by two fold.
Ginbot 7, Movement for Justice, Freedom and Democracy categorically denounces the barbaric killing of innocent civilians and holds Haile Mariam Desalegn and his associates accountable for the lives lost. Ginbot 7 acknowledges that the Muslim community in Ethiopia has been waging a legitimate struggle in Ethiopia for the past 11 months. The demands are simple and crystal clear – they have asked the regime for freedom of worship and for the right to elect their religious leaders in their own way and place of their own choosing. These rights are protected by the Ethiopian constitution which the regime is obligated to respect.
Ginbot 7 urges Ethiopians inside and outside of Ethiopia to stand together with our Muslim brothers and sisters in this difficult time. Ethiopians of Muslim and Christian faith must stand together as a community to continue the struggle for freedom, justice, democracy and equality understanding and believing that we live in the context of each other, and acknowledging that the source of our freedom is our collective struggle.
We ask that donor nations and international organizations get their act together and start holding the brutal regime in Ethiopia accountable for its heinous crimes and its wanton disregard for the sanctity of life. All civilized nations should strongly condemn this act of terror against the Muslim community in their place of worship.
In Solidarity!

Mass civilian detention reported in Degahbour


Ethiopian troops are reported to have illegally detained unknown number of Ogaden civilians in Degabour for the last 48
Mass civilian detention reported in Ethiopia
 hours. It is reported that these civilians have been taken to the military garrisons in and around Degahbour.

The detained civilians include the youth, the old, women and even some children Eyewitnesses believe that the detained civilians number more than a hundred.
Ethiopian army and its associated militia have been very active lately in forcefully displacing many civilians in rural area. As result, a heavily armed Duufaan Unit of the Ogaden National Liberation Army (ONLA) conducted a coordinated military operations in response to increased harassment and war crimes being committed by the Ethiopian Army in the region of Degahbour.
The heaviest operations occurred near the vicinity of Waceys-Godle where the Ethiopian Army planned and its associated militia were planing to attack civilians living iin the village of Waceys-Godle. The ONLA received intelligence of the marauding Ethiopia troops and laid ambush near Degahbour, inflicting heavy casualties on the enemy. In this operation ONLA has destroyed three Urals full of soldiers.
Reports indicate that the Ethiopian army waged a counter attack and sent reinforcement this morning around 7:00 AM local time. the ONLA ambushed Ethiopian reinforcements. It is reported that 38 Ethiopian army were killed, and two military transport vehicle of the type known as Urals were destroyed.
There are ongoing reports of sustained major military battles between the ONLA and the Ethiopian army throughout Ogaden. It appears that the Ethiopian army and its associated  militia went on the offensive, but are now on the defensive.

Monday, October 22, 2012

ኃይለማርያም ከመድረሱ፤ የንፁሃንን ሕይወት መቀንጠሱ!


ኃይለማርያም ደሣለኝ ምስለኔ ነው። ዋናው ባለሥልጣን ገና በውል አልታወቀም። ለሽያጭ ገበያ እንደወጣ ፈረስ ተስፈኛ ገዢዎች ኃይለማርያምን ለሙከራ እየጋለቡት ነው። በእርግጠኝነት የሚታወቀው ኃይለማርያም ደሣለኝ ምስለኔ እንጂ ዋናው ባለሥልጣን አለመሆኑ ብቻ ነው። እሱም ይህን ተቀብሎታል። የኃይለማርያም አዲስ ጌታ ነጥሮ ባለመውጣቱ ከቀድሞ ጌታው የተረከባቸውን ሹማምንት ይዞ ይቀጥል ወይም ጥቂት ለውጦችን ያድርግ ለጊዜው በውል የሚታወቅ ነገር የለም። ምን ያህል ሥልጣን በእጁ እንዳለም እንኳንስ ሌላው ሰው እሱም አያውቀውም። የመኖሪያ ቤትም ስላልተለቀቀለት ገና ወደ ቤተመንግሥት አልገባም።

እንዲህ ብዙ ነገሮች ገና ያልለየላቸው ቢሆንም ኃይለማርያም የቀድሞ ጌታው የመለስ ዚናዊን “ሌጋሲ” ለማስፈፀም ሲል ከአሁኑ ኢትዮጵያዊያንን መግደል ጀምሯል።
ለካስ ኢትዮጵያዊያንን በግፍ መጨፍጨፍ ነበር ኃይለማርያም ደሣለኝ ገና ከጠዋቱ ደጋግሞ “የኔ ሥራ የታላቁ መሪያችንን ሌጋሲ ማስቀጠል ነው” ሲል የነበረው!! እንዳለውም “የመሪውን ሊጋሲ” የሚያስቀጥል መሆኑን ከጅምሩ አሳየን።
የኃይለማርያም ደሣለኝ የምስለኔ አገዛዝ የመጀመሪያ ሰለባዎች ሙስሊም ምዕመናን ሆኑ። ቀኑም እሁድ ጥቅምት 11 ቀን 2005 ዓ.ም. ነበር። በደቡብ ወሎ በምትገኘው ገርባ ከተማ የሚገኙ ሙስሊም ምዕመናን በሣምንታት በፊት በተካሄደው የውሸት ምርጫ ባለመሳተፋቸው ሰበብ ተፈልጎ የጥይት ዝናብ ወረደባቸው። ምዕመናኑ በመስጊዳቸው ለመጠለል ሞከሩ፤ ግን አልቻሉም። የፓሊስ ልብስ የለበሱ የጦር ሠራዊት አባላት ምዕመናኑን በጭስ አፍነው በጥይት ቆሏቸው። እስካሁን ከአራት ያላነሱ ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው ተረጋግጧል። የሟቾች ብዛት ከዚህም በላይ እንደሚሆን ይገመታል። ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል። ጥቂቶቹ ደሴ ሆስፒታል ተወስደው የህክምና ርዳታ ያገኙ ቢሆኑም ብዙዎች ግን ይህንን እድል አላገኙም።
የኃይለማርያም የምስለኔ አገዛዝ አንድ ፓሊስ ተገድሎብኛል ቢልም እውነት ይሁን አይሁን እስካሁን ማረጋገጥ አልተቻለም። የቀድሞ ጌታው መለስ ዜናዊ ሰው በገደለ ቁጥር “ፓሊስ ተገድሎብኛል” ይል እንደነበረው ኃይለማርያምም ተመሳሳይ ውሸት መፈብረክ “የሌጋሲው” አካል አድርጎት ሊሆን ይችላል፤ ለጊዜው እርግጠኛው አልታወቀም።
በእርግጠኝነት የሚታወቀው ነገር በጥቅምት 11 ቀን 2005 ዓ.ም. በገርባ ከተማ ከአንድ መቶ በላይ በሆኑ ንጹሃን ዜጎች ላይ የሕይወት መጥፋት ወይም የአካል ጉዳት ያስከተለ ግፍ መፈጸሙ ነው።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው ጭፍጨፋ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ይገልፃል፤ ለሟቾቹ ገነትን ለቤተሰቦቻቸው ደግሞ መጽናናትን ይመኛል። ግንቦት 7 እነዚህ ውድ ኢትዮጵያዊያን ለመብቶቻቸው መከበር ሲሉ ከፍተኛውን የሕይወት መስዋትነት የከፈሉ ሰማዕታት አድርጎ ይመለከታል።

በረከት ስምዖን በኤርትራ ፓልቶክ ክፍል (ተስፋዬ ገብረአብ)

የኤርትራውያን የአረብኛ ፓልቶክ ክፍል በረከት ስምኦንን እንግዳ አድርጎ ጋብዞ ነበር። ጥያቄዎች ይቀርቡ የነበሩት በአረብኛ ቢሆንም፣ የትግርኛ ትርጉም ስለነበረው ሙሉውን ተከታትዬው ነበር። ውይይቱ ሲጨመቅ በሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎች ዙሪያ ያተኮረ ነበር ማለት ይቻላል።

የመጀመሪያው፣ “የኢትዮ - ኤርትራ ድንበር ለምን አይካለልም? ችግራችሁ ምንድነው?” የሚል ነበር። በረከት የተለመደውን ምላሽ ሰጥቶአል።

“ርግጥ ነው ወደ ፍርድ ቤት እንሂድ ያልነው እኛ ነን። ፍርድ ቤትም ሄደን ተሸንፈናል። ምንም እንኳ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ስህተት ነው ብለን ብናምንም፣ ውሳኔውን ከማክበር ውጭ አማራጭ የለንም። ችግሩ ያለው አፈፃፀሙ ላይ ነው። እንነጋገር ብለን ጠየቅን። የኤርትራ መንግስት ግን ፈቃደኛ ሳይሆን ቀረ። መነጋገር የሚያስፈልገን ጉዳዩ በቀጥታ ህዝብን የሚነካ በመሆኑ ነው። አንድን ቤት ለሁለት የሚከፍል ሁኔታ ጭምር አለ። ሌላው ጉዳይ ድንበሩን ማካለል ብቻ ሳይሆን፣ በሁለቱ አገራት መካከል ዘላቂ ሰላም የሚመጣበት ሁኔታ ላይ መነጋገር እንፈልጋለን። የንግድ ግንኙነት አለ። የህዝብ ግንኙነት ጉዳይም አለ። ህግደፍ ይህን ለመፍታት ፍላጎት የለውም። ከዚህ ባሻገር የኢትዮጵያ ያልሆነ መሬት ወደኛ እንዲመጣ ፍላጎት የለንም። ባድመ ላይም የተለየ ፍላጎት የለንም። የኛ ሆኖ ሳለ በህግ የተወሰነብንንም ቢሆን የመስጠት ችግር የለብንም። ጥያቄያችን ‘እንነጋገር’ የሚል ነው” ሲል መልስ ሰጥቶአል።

ሁለተኛው መሰረታዊ ጥያቄ፣

“እኛ ኤርትራውያን የታገልነው ለኤርትራ ነፃነት ነው። የሃይማኖት፣ የቋንቋ እና የብሄር ችግር የለብንም። የኢትዮጵያ ሁኔታ እና የኛ ተመሳሳይ አይደለም። ኢትዮጵያ ላይ የኦሮሞ እና የኦጋዴን ጥያቄዎች አሉባችሁ። ‘እስከመገንጠል’ የሚለው አንቀጽ ለናንተ ያስፈልግ እንደሁ አናውቅም። የኤርትራን አንድነት ችግር ላይ የሚከተውን የመገንጠል እና በብሄር የመደራጀት ነገር ወደኛም የምትገፉብን ለምንድነው? ኤርትራውያንን ለምን በጎሳ ለማደራጀት ትሞክራላችሁ? መገንጠልን እንደግፋለን ትላላችሁ። ኦጋዴኖች መገንጠልን ሲጠይቁ ግን አልፈቀዳችሁም። ለራሳችሁ ያላመናችሁበትን ወደ ኤርትራ ትገፉታላችሁ…”

የስምኦን ልጅ በረከት፣ ይህችን ጥያቄ ለመመለስ በጣም ብዙ ደከመ፣

“…የኤርትራ ህብረተሰብ ውስጥ ጥያቄው አለ” ሲል ጀመረ፣ “…እኛ ያመጣነው አይደለም። ተደራጅተው የመጡትን ግን እውቅና ሰጥተናል። በትግርኛ እና በትግረ፣ በአፋር እና በትግርኛ መካከል ቅራኔ አለ። የብሄር ጭቆና አለ። ይህ የማይካድ ነው። እርግጥ ነው፣ ትግሉ የተካሄደው ኤርትራ በሚለው ስሜት ነው። ኤርትራ ነፃነቷን ካገኘች በሁዋላ ግን ትግሉ ወደ ውስጥ ዞሮአል። ይህ የውስጥ ትግል ኤርትራን ይፈረካክሳታል ወይም ደግሞ አንድነታን ያረጋግጥላታል። ውስጣዊ ትግሉ ገና አልተፈታም። የኢትዮጵያን ሞዴል ውሰዱ አላልናችሁም። በቋንቋ እና በሃይማኖት ተበድለናል’ ብለው ወደኛ የሚመጡትን ግን እናግዛለን። የመገንጠልን መብት እንደግፋለን። እውነት ነው። እናበረታታለን ማለት ግን አይደለም። ኦጋዴን ላይ መገንጠልን የጠየቀው አንድ ፓርቲ ብቻ ነው። ህዝቡ እስካሁን የመገንጠል ዝንባሌ አላሳየም። ኤርትራ ተገንጥላለች። ልክ እንደ ኤርትራ አንድ ላይ መኖር ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ከተደረሰ ሌሎችም ሊገነጠሉ ይችላሉ። ‘ኤርትራውያን አንድ ነን። ልዩነት የለንም፣ አንድ አገር - አንድ ልብ’ የሚለው ዘፈን ግን የሻእቢያ መንገድ ነው።”

በዚህ የበረከት ንግግር ኤርትራውያን መቆጣታቸውን ተከታትዬአለሁ።

በመጨረሻ፣ “በረከት ስምኦን አንተ ትውልድህ ከኤርትራ ነው። ለመሆኑ በኢትዮጵያ የመንግስት ከፍተኛ ስልጣን ላይ በመቀመጥህ የደረሰብህን ችግር ልትነግረን ትችላለህ?” የሚል ጥያቄ ለበረከት ቀርቦለት ነበር። ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀረ። የታዳሚዎችን የቁጣ ስሜት የተገነዘበው በረከት፣ ውይይቱን ለማቋረጥ ተገደደ። በርካታ ጋዜጠኞች ጥያቄ ለመጠየቅ እጅ አውጥተው የነበረ ቢሆንም በረከት አስቸኳይ ስራ እንዳለው ገልፆ መካከሉ ላይ ተሰናብቶአል።
ተስፋዬ ገ/አብ

ESAT Ethiopian News Weekly October 21, 2012