Tuesday, January 15, 2013

የኢትዮጵያ ፍ/ቤቶት ከአሸባሪ ቡድን ጋር በመተባበር የሽብር ጥቃት ለመሰንዘር አቅደው ነበር ባላቸው 10 ሰዎች ላይ ከ3 አመት እስከ 20 ዓመት የሚደርስየእስር ቅጣት ወሰነ


የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ባስቻለው ችሎት የእስር ቅጣት ከወሰነባቸው ውስጥኬኒያዊው ሀሰን ጃርሶ እንደሚገኙበት የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል::
ከፍተኛው ፍ/ቤት ዳኛ ባህሩ ዳርቻ በኬኒያው ጃርሶ ላይ የ17 ዓመት የ እስርፍርድ ወስነውበታል::በዚህ ከአሸባሪነት ተግባር ጋር በተያያዘ ክስ በቅድሚያ የተካተቱት 11 ሰዎችእንደነበሩ ሲታወቅ አንደኛው በነጻ ተሰናብቷል ስድስቱ ደግሞ በሌሉበትተወስኖባቸዋል::የኢትዮጵያ የስለላ ድርጅት በዚህ ወር መጀመሪያ አልሸባብ ከተባለውየሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን 15 ሰዎች መያዙንማስታወቁን ይህ የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል::
በምስራቅ አፍሪካ ሃገሮች የታጣቂዎች እንቅስቃሴ እየጎላ በመምጣበት ጊዜ ነውይህ የፍ/ቤት ውሳኔ የተላለፈው ያለው ዘገባ ኢትዮጵያ ሰራዊቱን በ2011 ወደሱማሊያ ዳግም መዝመቶንም አስታውሷል::

No comments:

Post a Comment