Tuesday, December 18, 2012

ኢሳት በናይል ሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያሰራጨው ስርጭቱ ቢቋረጥም፣ ስርጭቱን በአሞስ ሳተላይት እያስተላለፈ ነው


-ኢሳት ላለፉት ሶስት ወራት ስርጭቱን በ ናይልሳት ሲያሰራጭ ከቆየ በሁዋላ የኢትዮጵያ መንግስት ስርጭቱን ከማፈን አልፎ ባደረገው ከፍተኛ የሎቢንግ ዘመቻ የኢሳት ስርጭት እንዲቋረጥ አድርጓል።
በመላው አገሪቱ ኢሳት ቁጥር አንድ ተመራጭ የቴሌቪዥን ጣቢያ በመሆን የሰፊውን ህዝብ የመረጃ ጥማት ለማርካት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ለገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ራስ ምታት ሆኖበት እንደነበር ኢሳት የኢትዮጵያ  ወኪል ገልጿል።
ምንም እንኳ ኢሳት የናይል ሳት ስርጭቱ ቢቋረጥም፣ በአሞስ 5 የሚያካሂደው ስርጭቱ አሁንም እንደቀጠለ ነው።
ኢሳት በቅርቡ ተጨማሪ ቻናል ለማስተዋወቅ በዝግጅት ላይ ነው።
ኢሳት በናይል ሳት የሚያሰራጨው የራዲዮ ዝግጅቱ፣ አዲስ የጀመረው በአረብሳት የ ሚያስተላልፈው ራዲዮ አሁንም እንደቀጠለ ነው።
ኢሳት  Amos 5 KU  17 Degrees East  Downlink: 10961.200 V  Symbol Rate 2.200  FEC: 1/2 እንደሚተላለፍ ለማስታወስ እንወዳለን።

No comments:

Post a Comment