Saturday, December 8, 2012

በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ የንብረት ውርስ ላይ ትእዛዝ ተሰጠ


ከፍተኛው ፍርድ ቤት በ1ኛ ተከሳሽ በአቶ አንዷለም አራጌ ባለቤት ስም የተመዘገበው የቤት መኪና ፤ በ7ኛ ተከሳሽ አቶ እስክንድር ነጋ ስም የተመዘገበ 1 ቤትና ከእናታቸው በውርስ ያገኙት ተዳምሮ 2 መኖሪያ ቤቶች እና በባለቤታቸው ስም የተመዘገበ 1 የቤት መኪና ፤ እንዲሁም በሌሉበት በተከሰሱት በ16ኛ ተከሳሽ በአቶ አበበ በለው ባለቤት ስም ፥ የተመዘገበ መኖሪያ ቤት ላይ የቀረበውን የውርስ አቤቱታ ያደመጠ ሲሆን አቶ አንዱአለም ባለቤት በጠበቃቸው አማካኝነት መኪናዋ ልጆችን ትምህርት ቤት የምታመላልስ መሆኗን ጠቅሰዋል።  የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ወ/ሮ ሰርካለም ፋሲል ችሎት ቀርበው እንዳማይከራከሩ በችሎቱ ላይ ተገልጿል።
የ አቶ አበበ በለው  ባለቤትም ችሎት ስላልቀረቡ ለታህሳስ 18 መጥሪያ ደርሷቸው ችሎት እንዲገኙ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት ለታህሳስ 18 ቀን 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙ ታውቋል

በባህርዳር ለሚከበረው 7ኛው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ዝግጅት 200 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉ ታወቀ


ኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጡት በአሉን ለማክበር የወጣው ገንዘብ እስካሁን ባለው ግርድፍ መረጃ 200 ሚሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ሂሳቡ ሲወራረድ ወጪው ከዚህም ከፍ ሊል ይችላል ተብሎአል።
በትናንትናው  ዕለትም በ20 ሚሊየን ብር የተሰራችው ህዳሴ የተሰኘች መርከብ የከተማዋ ነዋሪዎች፣እንግዶች፣ባለስልጣናት በተገኙበት ተመርቃለች፡፡ህገመንግስቱ የጸደቀበት ህዳር 29 የብሔርብሔረሰቦች በዓል ሆኖ እንዲከበር የፌዴሬሽን ም/ቤት በወሰነው መሰረት በዓሉ በፈንጠዝያና በግብዣ በየዓመቱ ሲከበር ዘንድሮ ለ7ኛ ጊዜ ነው፡፡
የበዓሉ ማጠቃለያ ከ550 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ወጥቶበት በመገንባት ላይ ባለው የባህርዳር ስታዲየም ተጠናቋል
በተለይ በዓሉን በፌሽታ ለማሳለፍ የሚወጣው ከፍተኛ ወጪ ብክነት መሆኑን አንድ ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪ ጠቁመው የብሔርብሔረሰቦች መብትና ጥቅም እንዲሁም የሕገመንግስቱ ፍሬሃሳቦች የሚከበሩት መልካም አስተዳደር፣ግልጽነትና ተጠያቂነትን በመዘርጋት በስራ እንጂ በፌሽታ ሊሆን አይችልም ብለዋል፣ ዘጋቢያችን ከባህርዳር እንደገለጠው።

አቶ ሀይለማርያም በጣና በለስ ስኳር ፕሮጀክት ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ሰራተኞቹ በድብቅ ካምፕ ውስጥ ገብተው በመገኘታቸው አጋዚዎቹ ሲያሸብሩዋው መዋላቸው ታውቋል። ሰራተኞች ፕሮጀክቱን የሚመራው ጠፍቷል፣ የሰራተኛው መብት ታፍኗል በማለት አቤቱታ ሲያቀርቡ ይሰማል።
የኢሳት ዘጋቢ ከባህርዳር እንደገለጸው ከከተማው የተሰበሰቡ ነድያን ጅንአድ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተሰብስበው በአንድ ቦታ እንዲከማቹ ከተደረገ በሁዋላ የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በልተው ይስተረፉት ተረፈ ምርት እየቀረበላቸው መሆኑን ገልጿል።
አንዲት ወጣት ለዚህ በአል የወጣው 200 ሚሊዮን ብር በከተማው የሚታየውን የስራ አጥ ወጣቶች ቁጥር በብዙ እጅ ለመቀነስ ይጠቅም ነበር ስትል አስተያየቱዋን ሰጥታለች።
ኢህአዴግ ጫካ በነበረበት ጊዜ ደርግ ህዝቡን እያስራበ ለ10ኛው አብዮት በአል ከፍተኛ ገንዘብ አወጣ በማለት ይተች ነበር።

ጠቅላይ ሚ/ር ሀይለማርያም ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ለምታደርገው የእግር ኳስ ጨዋታ ቦታ እንዲለወጥ መጠየቁን አላውቅም አሉ


አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ይህን የተናገሩት ከአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው።  ረዩተር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቃል አቀባይ የሆኑትን አቶ መላኩ አየለን በመጠቀስ  ” ለተጫዋቾች ደህንነት ሲባል እግር ኳስ ፌደሬሽኑ የጨዋታው ቦታ እንዲቀየር መጠየቁን ” ዘግቦ ነበር። ቢቢሲና አልጀዚራን የመሳሰሉ ታላላቅ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀንም ለጉዳዩ  የዜና ሽፋን መስጠታቸው ይታወቃል።
በኢትዮጵያ በኩል የቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የነበራትን ጨዋታ መሰረዙዋን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን መግለጹን ረዩተር ከትናንት በስቲያ ዘግቧል።
እነዚህ ዘገባዎች በስፋት በመገናኛ ብዙሀን በቀረቡበት ሁኔታ ነው፣ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ” ከኤርትራ ጋር ወዳጅነት ከፈለጋችሁ ለምን ከኤርትራ ጋር ለምታደርጉት የእግር ኳስ ጨዋታ የመጫዎቻ ቦታው እንዲቀየር ፈለጋችሁ?” በሚል ለቀረበላቸው ድንገተኛ ጥያቄ በመደናገጥ መረጃ የለኝም ሲሉ መለስ የሰጡት።
የአንድ አገር ጠቅላይ ሚኒስትር  በውጭ ፖሊሲ ዙሪያ የመጨረሻውን ውሳኔ የሚሰጥ አካል መሆኑ በህገመንግስቱ ተቀምጧል።  አቶ ሀይለማርያም ትልቅ አገራዊ የመነጋጋሪያ አጀንዳ የሆነውን ጉዳይ አለውቅም ማለታቸው አንድም ውሳኔው ከእርሳቸው ውጭ በሆነ አካል የተወሰነ ነው፣ ሌላም ለቃለምልልሱ ሲቀርቡ ረዳቶቻቸው አስቀድመው እንዲዘጋጁ ባለማድረጋቸው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አሻንጉሊት ናቸው የሚለውን መልእክት ሆን ብሎ ለማስተላለፍ ከእርሳቸው ጀርባ ባሉ ሰዎች የተቀነባበረ ሊሆን ይችላል” በማለት የኢሳት ዘጋቢ አስተያየቱን አስፍሯል።
አቶ ሀይለማርያም አስመራ በመሄድ ከአቶ ኢሳያስ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊም ከአቶ ኢሳያስ ጋር አስመራ በመሄድ ለመነጋገር ከ50 ጊዜ በላይ መጠየቃቸውን ተናግረዋል። የአቶ መለስ መንግስት ከኤርትራ ጋር ለመነጋገር 5 ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጦ እንደነበር ይታወሳል። አቶ መለስ  እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ካልተሙዋሉ በስተቀር ከአቶ ኢሳያስ ጋር እንደማይነጋጋሩ በፓርላማ ፊት በተደጋጋሚ ይናገሩ ነበር። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም ስለ5ቱ ቅድመ ሁኔታዎች ምንም አለማለታቸውን ዘገቢያችን ገልጿል።
” አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ ወደ አስመራ በመሄድ ከአቶ መለስ ዜናዊ ጋር ለመደራደር ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፤ የባድሜን ጉዳይ አላነሱም። በዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድነው ?’” ተብለው አስተያየታቸውን የተጠየቁት የግንቦት 7 ሊቀመንበር  ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ፣ “ወያኔዎች  ስልጣኑን ለማቆየት እንኳንስ ባድመን አዲግራትንም ስጡን ቢሉዋቸው  ሰጥተው ለመደረዳር ዝግጁ ናቸው” በማለት መልሰዋል።
ከኤርትራ ጋር ለመደራደር ከመለመን ይልቅ ቀላሉ መንገድ ከተቃዋሚዎች ጋር መደራደር አይደለም ወይ ተብለው ለተጠየቁት ደግሞ ፣ ዶ/ር ብርሀኑ ሲመልሱ ” ከተቃዋሚዎች ጋር መደራደር የዲሞክራሲ እና የስልጣን ጥያቄ የሚያስነሳ ነገር በመሆኑ አይፈልገውም” በማለት መልሰዋል
“አንዳንድ ምሁራን ‘ መንግስት ባድመን ካስረከበ ከትግራይ ህዝብና ከህወሀት ታጋይ ተቃውሞ ሊነሳበት ይችላል’  በማለት አስተያየት ይሰጣሉ  ተብለው ለተጠየቁት ደግሞ ፣  ዶ/ር ብርሀኑ ” ወያኔ የትግራይን ህዝብ በሀይል እጨፈልቀዋለሁ ብሎ እንደሚያስብ እና ስልጣኑን የሚያቆይለት መስሎ ከታየው ምንም ነገር ለማድረግ ወደ ሁዋላ አይልም” በማለት መልሰዋል።

    Friday, December 7, 2012

    በትግራይ ክልል ህወሀትን አትደግፉም የተባሉ ዳኞች እየታሰሩ ነው


    በክልሉ የሚገኙ ዳኞች ለኢሳት እንደገለጹት በቅርቡ በክልሉ ከፍተኛ ግምገማ በመካሄድ ላይ ሲሆን አመለካከታቸው ከመለስ ራእይ ውጭ ነው የተባሉ ዳኞች ተይዘው ታስረዋል። ድምጻቸው እንዳይተላለፍ የጠየቁ ዳኞች ለኢሳት እንደገለጹት  በውቅሮ ከተማ ውስጥ በተደረገው ግምገማ 4 ዳኞች ታስረዋል።
    አቶ መለስ ከሞተ በሁዋላ ሁኔታው ተባብሶ መቀጠሉን የገለጡት ዳኞች፣ ለምን የሚል ጥያቄ የሚያነሱ ዳኞች ድብደባ ሳይቀር ይደርስባቸዋል።
    ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የሰሩ ዳኞች ሲሰለጥኑ 4 አመት ለማገልግል ከመንግስት ጋር ውል የተዋዋሉ በመሆናቸው ስራ ለመልቀቅ እና ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሄደው ለመስራት ተችግረዋል። ዳኞቹ ለመለቅቅ ከፈለጉ 36 ሺ ብር መክፈል እንዳለባቸው ዳኞች ተናግረዋል።
    በክልሉ የሚገኙ መምህራንም በሚታየው የመብት አፈና እየተማረሩ መምጣታቸውን ለኢሳት ገልጸዋል።

      በአንዋር መስጊድ ዛሬም የተቃውሞ ድምጾች ተስተጋቡ


      በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እስላም ኢትዮጵያውያን በታላቁ የአንዋር መስገድ በመገኘት በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እየተከተለ ያለውን ፖሊሲ አምርረው ተቃውመዋል።
      ምእመናኑ 27 ቁጥር የተጻፈበት ወረቀት በማውለብለብ ” አንቀጹ ይከበር፣ ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ፣ አሸባሪዎች አይደለንም” በማለት ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ ተሰምቷል።
      ምእመናኑ 27 ቁጥር በመያዝ ተቃውሞአቸውን ያስተጋቡት በህገመንግስቱ በአንቀጽ 27 ላይ የተደነነገገው የሀይማኖት እኩልነት መብት ይከበር በማለት ነው።
      አዲሱ መንግስት የመለስ መንግስት ይከተለው የነበረውን ችግሮችን በሀይል የመፍታት ዘዴ መከተሉ፣ ከኢትዮጵያውያን አልፎ በጸረ ሽብር ትግሉ ወዳጅ ተደርጋ የምትታየዋን አሜሪካ ሳይቀር እያሳሰበ የመጣ ጉዳይ ሆኗል።
      በእስር ላይ በሚገኙት የኮሚቴ አባላት ላይ የሚታየው የተንዛዛ የፍርድ ሄደትና በአባላኦቹ ላይ በእስር ቤት የፈጸመው አሰቃቂ እርምጃ ምእመኑን ማበሳጨቱን ወኪላችን ከአዲስ አበባ ዘግቧል።

      ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ለሕዝብና ለመንግስት ጥሪ አደረጉ


      -የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፕሬዚዳንት፤ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ መንግስት ሕገ መንግስቱን እንዲያከብር፤ የኢትዮጵያ ህዝብም ሕገ-መንግስታዊ መብቱ እንዲከበር እንዲታገል ጥሪ አደረጉ።
      ዶ/ር ነጋሶ ዛሬ አርብ ህዳር 28 ቀን ከኢሳት ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ባደረጉት ቃለምልልስ፤ ኢህአዴግ ከጥቂት አመታት ወዲህ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን እያለ የሚጠራው ህዳር 29 ቀን፤ በዋንኛነት ሕገመንግስቱ የጸደቀበት ቀን እንደሆነ በማስታወስ፤ ኢህአዴግ ቆም ብሎ በማሰብ የህገ መንግስቱን የሰብአዊ መብት አንቀጾች እንዲያከብርና እንዲያስከብር አሳስበዋል።
      የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንትና የአሁኑ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፤ ሕገ መንግስቱ በሚረቀቅበትም ግዜ ይሁን በሚጸድቅበት ግዜ ስህተቶች እንደተሰሩ አስታውሰው፤ ህገ መንግስት የማይለወጥ የመጽሀፍ ቅዱስ ቃል ስላልሆነ፤ ኢህአዴግ ህገመንግስቱን እንዲያሻሽልም ጠይቀዋል።
      ከጥቂት ቀናት በፊት፤ የገዢውን ፓርቲ የአምባገነንት ባህርይ በመተንተን፤ ገዢው ፓርቲ “ተገዶ እንጂ በልመናና በመለማመጥ በፈቃደኝነት በህዝብ የሚፈለገውን ለውጥ እንደማያመጣ” ገልጸው የጻፉትና ህዝቡም የተበታተነ ብሶቱንና ምሬቱን ወደአመጽና እምቢተኝነት መለወጥ እንዳልቻለ የተቹት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፤ ሀሳባቸውን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ውይይት አብራርተዋል።
      ከህዝቡ ምሬት ወደ አመጽ ያለማደግ ሁኔታ ጋር በተያያዘም ምክንያቱ የተለያዩ እንደሆነ ገልጸው፤ በተለይም ከምርጫ 97 በፊትም በሁዋላም ኢህአዴግ በህዝቡ ላይ ባደረሰው የጭካኔ ጥቃት ምክንያት በህዝቡ ላይ የፍርሀት ድባብ ሰፍኖ እንደሆነ ተናግረው፤ ህዝቡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሳይጠብቅ፤ መብቱን ለማስከበር መስራት አለበት ብለዋል።
      ከዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለምልልስ በሬድዮ ፕሮግራማችና ላይ ይከታተሉት።

      በጂዳ የብአዴን ዝግጅት ላይ የተገኙ ተጠርጣሪ ኢትዮጵያዊያን ተባረሩ

      የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) 32ኛ አመት ለማክበር አርብ ምሽት በጅዳና በአካባቢዋ በተዘጋጀ ዝግጅት ለመሳተፍ የሄዱ በርካታ ነዋሪዎች እንዳይገቡ መከልከላቸውንና ስብሰባው በጊዜ መበተኑን ጋዜጠኛ ነቢዩ ሲራክ ከስፍራው ገልጿል።

      ዛሬ በተጠራው የብአዴን ዝግጅት ላይ የተቃውሞ ድምጻችን እናሰማለን በሚል ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ወረቀት በህቡዕ የበተኑ ሲሆን፤ በስብሰባው ላይ ተቃውሞ እንዳያካሂዱ በሚል ፍራቻ ጥሪ የተደረገላቸው አንዳንድ ግለሰቦች ከስብሰባው ውስጥ እየተጠሩ እንዲባረሩ መደረጉን ነዋሪዎች ለነቢዩ ሲራክ ገልጸውለታል።

      ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መንገድ መታዎቂያ አሳዩ የሚል ምክንያት ለመስጠት የተሞከረ ቢሆንም፤ መታወቂያ ይዘው የተጠረጠሩና የተፈሩ አንዳንድ ነዋሪዎችም ወደ ስብሰባው እንዳይገቡ እንደተደረጉ ታውቋል፡፡

      የሟቹን ጠቅላይ ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ በባንዴራ አጅበው ከኮታቸው ላይ የለጠፉ የብአዴን አባላት ነዋሪዎችን በጥርጣሬ አንዳይገቡ ሲከለከሉና የፈለጓቸውን እየመረጡ ሲያስገቡ እንደታዘበ ነቢዩ ሲራክ ከስፍራው ዘግቧል።

      ከመግቢያው በር ያሉትን የሳውዲ ልዩ ኮማንዶ ወታደሮችን ያናገረው ነቢዩ ሲራክ፤ ”የቆንስሉ ሃላፊዎች ማንም እንዳይገባ ከልክሉ ብለውናል” በማለት እንዳስረዱትና ነዋሪውን በማግባባት ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ ሲማጸኑ እንደተመከተም ገልጿል።

      የብአዴን አባላት እገዳው የተደረገው በጸጥታ ምክንያት እንደሆነና ጋዜጠኞችን ጨምሮ የተጠረጠሩና የማይታወቁ ሰወች እንዳይገቡ እገዳ መጣሉን ገልጸዋል።

      አንዳንድ የብአዴን አባላት በጥሪ የመጡትንም እያንጓጠጡ ያስወጧቸው ሲሆን፤ ስብሰባው ያለወትሮው በጊዜ ሲጠናቀቅ ከስብሰባው የወጡ አንዳንድ ሰዎች ሲገቡ ችግር እንደገጠማቸውና በስብሰባው ላይ ምንም አይነት ፎቶም ሆነ ቪዲዮ እንዳይነሳ ቁጥጥር መደረጉንና ስብሰባው በተቃውሞና ፍራቻ ሲናጥ ማምሸቱን እንደገለጹለት ነቢዩ ሲራክ ከጂዳ ገልጿል።

      Thursday, December 6, 2012

      Amharic poem dedicated to Abune Petros statue

      ESAT Daliy News Amsterdam Dec 06 2012 Ethiopia

      የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የብሄር ብሄረሰቦችን በአል አከባበር ነቀፉ


       ኢሳት ያነጋገራቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የብሄር ብሄረሰቦች በአል አከባበር  የይምሰል ነው በማለት ተችተዋል።  የተረፈች ልጅ በሚል ቅጽል ስም የሚጠራው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስድስት ኪሎ ግቢ ተማሪ እንደተናገረው ኢትዮጵያ በጥቂቶች የምትገዛ ፣ አብዛኛው ህዝብ የበይ ተመልካች የሆነባት አገር ናት ።
      በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የብሄሮች መብት አለመከበሩ በግልጽ የሚታየው በስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ነው የሚለው ተማሪ፣ ተማሪዎች እርስ  በዘር በመከፋፈላቸው ለመገናኘትና በአንድ አገር ጥላ ስር ለመቆም እየከበደ መምጣቱን ተናግሯል ።
      አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ኢህአዴግ ያስገኘው የብሄር ብሄረሰቦች መብት ውጤት ተደርጎ እየታየነው ምን አስተያየት አለህ ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ፣ ሀይለማርያም ማለት ” የራሺያው ሜድቬደቭ  ነው፣ ስልጣን የለውም ለምልክት የተቀመጠ ነው” በማለት መልሷል።
      በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ  የተንሰራፋው ዘረኝነት ተማሪዎች ለአገራቸው ጉዳይ በአንድነት እንዳይቆሙና እንዳይታገሉ  እንዳደረጋቸው ተማሪው ገልጿል።
      በሌላ በኩል ደግሞ በዛሬው እለት በአዋሳ ዩኒቨርስቲ የብሄር ብሄረሰቦችን በአል ያከበረ ወጣት እንደገለጠው በኢትዮጵያ ውስጥ የብሄረሰቦች መብት ተከብሮአል ብሎ እንደማያስብ ገልጿል።
      የአንድነት ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆነው ወጣቱ ፖለቲከኛ ዳዊት አስራደ በበኩሉ ህገመንግስቱ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት መከበር እንደሚደነግግ ገልጾ፣ ይሁን እንጅ በህገመንግስቱ ውስጥ የሰፈሩት መብቶች ባለመከበራቸው የብሄሮች መብት ተከብሯል ብሎ መናገር እንደማይቻል ገልጿል።
      ክልሎች ራሳቸውን እያስተዳደሩ ነው ብሎ እንደማያምን የገለጠው ወጣት ዳዊት፣ በብሄር ደረጃ መብቱ የተከበረለት ብሄር አለመኖሩን  ይሁን እንጅ የገዢው ፓርቲ ሰዎች የሰዎችን መብት እስከ መድፈር የሚደርስ መብት እንደተከበረላቸው ገልጿል( 7፡08-7፡35)። በብሄሮች ጥያቄ ላይ ያቀናበርነውን በነገው እለት በትኩረት ዝግጅት ላይ የምናቀርብ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።
      ይህ በእንዲህ እንዳለ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ በመያዝ በአሉን እንዲያከብሩ እየተገደዱ መሆኑን ርእሰ መምህራን ለኢሳት ገልጸዋል። አንድ ስሙ እንዳይገለጥ የፈለገ ርእሰ መምህር ” ትምህርት ቤቶች የኢህአዴግ የፖለቲካ ትምህርት ቤት ሆነዋል” ሲል ገልጿል።
      ተማሪዎች ሳምንቱን ሙሉ በአል አክብሩ በመባላቸው የትምህርት ሂደቱ እየተስተጓጓለ መምጣቱን መምህሩ ገልጿል።

      በአማራ ክልል የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እያቋረጡ ወደ አረብ አገራት በብዛት በመሰደድ ላይ ናቸውህዳር


      ኢሳት ዜና:- በአማራ ክልል የሚገኙ መምህራን ለኢሳት እንደገለጡት በሰሜን ወሎ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ብቻ ከመስከረም እስከ ታህሳስ ወር  ከ 5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ባሉት ክፍሎች ውስጥ 44 ሴት ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ አረብ አገራት ሄደዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ፓስፖርት በማውጣት ጉዞአቸውን እየተጠባበቁ ነው። መምህራንም እንደ ተማሪዎች የሚሰደዱ መሆናቸው ችግሩን አሳሳቢ አድርጎታል።  መንግስት መምህራንን በመሰብሰብ ለማወያየት ሙከራ አድርጓል።

      Add caption
      መንግስት የችግሩን ምንጭ ፈልጎ እንደማግኘትና መፍትሄ እንደመፈለግ  በመምህራን ላይ ማሳበብን መርጧል።  የመንግስት አቋም መምህራን ወደ አረብ አገራት ስለሚደረገው ስደት በቂ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ለተማሪዎች አልሰጡም የሚል ሲሆን፣ የመምህራን አቋም ደግሞ  ” ተማሪዎች የሚሰደዱት  ተስፋ በማጣታቸው ነው” የሚል ነው ።
      እድሉ ቢገኝ ከአገሪቱ ህዝብ 40 በመቶው አገሩን ጥሎ ለመሰደድ ፍላጎት እንዳለው በውጭ አገር የተደረገ አንድ ጥናት ከአመት በፊት ማመላከቱ ይታወሳል።
      ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ኢትዮጵያውያን በየመን የባህር ሰላጤ እንዲሁም በሰሀራ በረሀ የውሀ ሽታ ሆነው መቅረታቸውን አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን በተደጋጋሚ መዘገባቸው ይታወሳል።

      Wednesday, December 5, 2012

      ከአውሮፓና ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ኢትዮጵያዊያን በመንግስት ደህንነቶች እንደሚመረመሩና እንደሚታሰሩ ተገለጠ


      ዩናይትድ ስቴት አሜሪካ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ጋምቤላ ቤተሰቦቻቸውን ለመጎብኘት ተጉዘው የነበሩት ዶ/ር ማኝ አንግ ለኢሳት እንደገለጡት በጋምቤላ በክልሉ ፕሬዚዳንት ተጠርተው ደህንነቶች እንደሚፈልጎቸው ከተነገራቸው በሆላ ለ 2 ሰአት ያህል እንደመረመሮቸው አስታውቀዋል::
      ማንኛውም የጋምቤላ ተወላጅ ወደተወለደበት ሀገር ሲሄድ ያሬድ፡ ኤፍሬምና ዳዊት በሚባሉ የመንግስት ደህንነቶች ይመረመራል፤ በጋምቤላ ከሚገኙ የተቃዋሚ መሪዎች፤ ከግምቦት ሰባትና በጋምቤላ ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጋር ስላለው ግንኙነት ይጠየቃል ያሉት ዶ/ር ማኝ አንግ በሳቸው ላይም ተመሳሳይ ምርመራ ከተደረገ በሆላ በነጻ መለቀቃቸውን ተናግረዋል::
      ይሁንና በርካታዎቹ በደንነት ከተመረመሩ በሆላ እንደሚታሰሩ የገለጡት ዶ/ር ማኝ አንግ በቅርቡ በቦሌ አየር ማረፊያ የታሰሩና በአሜሪካ ኤምባሲ ጥረት ተፈተው ከቦሌ በቀጥታ ወደ አሜሪካ ስለተመለሱት ሁለት የአኝዋክ ተወላጆች ተናግረዋል:፡
      በተወለዱበትና ባደጉበት ሀገር ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ የሄደ ሰው በመንግስት ደህንነቶች መታደኑ፡ መመርመሩና መታሰሩ በጋምቤላ የተለመደ ነው ያሉት ዶ/ር ማኝ አንግ 20 አመት አሜሪካ ቆይተው በሀገራቸው ስለደረሰባቸውና በሌሎች ላይ የሚፈጸመውን ተግባር ኮንኖል::

        ነጋዴዎች አዲስ ራእይ መጽሄትን እንዲገዙ እየተገደዱ ነው


        ነጋዴዎቹ ለኢሳት እንደተናገሩት ፣ አንድ ነጋዴ በ100 ብር ቢያንስ ሁለት የአዲስ ራእይ መጽሄትን መግዛት ግድ ይለዋል። ይህን መጽሄት ለመግዛት ፈቃደኛ ካልሆ ጸረ ልማትና ጸረ ህገመንግስት ተደርጎ ይቆጠራል። መጽሀፉን የሚሸጡት የኢህአዴግ አባላት ሲሆኑ ፣ አንድ አባል በነፍስ ወከፍ እስከ 50 አዲስ ራእይ መጽሄቶችን መሸጥ ይጠበቅበታል።
        ኢሳት ከመንግስት በኩል ማረጋጋጥ ባይቻልም ስለመለስ ዜናዊ ማንነት የምትተርከው አዲስ ራእይ መጽሄት በሚሊዮን  የሚቆጠር ቅጅ እንዲታተም መደረጉን የደረሰን መረጃ ያመለክታል ። አንዳንድ ወገኖች የታተመው መጽሄት ቁጥር እስከ 6 ሚሊዮን ይደርሳል በማለት ለኢሳት ገልጸዋል።
        መጽሄቱን ለማስተዋወቅ በቀረበው ማስታወቂያ ላይ ” ጀርመናዊው ፈላስፋ ዊልያም ፍሬዴሬክ ሄግል ” አለማዊ ምጡቅ የታሪክ ስብእና ከአፍሪካ አይፈልቅም” ሲል ከምእተ አመት በፊት የዘጋውን ድርሳን የከፈተው ኢትዮጵያዊው አፍሪካዊ መለስ ዜናዊ መሆኑን ያውቃሉን?” የሚል ተጽፎ ይገኛል።
        ማስታወቂያው በማያያዝም ” ርእዮተ አለም ያልገደባቸው ታላላቆቹ  የአለም መሪዎች የማይሰለች፣ የሚመኩበት፣ የአዳዲስ እውቀቶች ቀዳሚ ተመጋቢ በማለት አሞካሽተውና ብሩህ አእምሮውን አድንቀው ሊጠግቡት ያልቻሉት በምን ምክንያት ይሆን? ለእነዚህ ጥያቄዎች ቱባ ምላሽ ያላት አዲስ ራእይ ብቻ ናት ” ሲል ገልጿል
        በመጽሄቱ ግርጌ ላይ ”  ታጋይ መለስ ያዘጋጃት የነበረችው አዲስ ራእይ ተዝቆ ከማያልቀው የመለስ ስራዎች የቅምሻ ያህል እንካችሁ የምትለው እንደ ወትሮው ለኢህአዴግ አባላት ብቻ አይደለም፣ በመሪው ሞት ጥልቅ ምሬትና ድንጋጤ ፣ ሀዘንና ቁጭት ውስጥ ገብቶ መለስ ያወረሰንን እናሳካለን ብሎ ቃል ለገባው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው።” በማለት መጽሄቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚሸጥ ኢህአዴግ ግልጽ አድርጓል።
        አዲስ ራእይ መጽሄት ቀድሞ 10 ብር ይሸጥ ነበር። ልዩ እትሙ ደግሞ 100 ብር እየተሸጠ ነው። “ኢህአዴግ ህዝቡ የመለስን ታሪክ እንዲያውቅለት ቢፈልግ ኖሮ ዋጋውን  100 ብር ከማድረግ 10 ብር  ያደርገው ነበር፣ ኢህአዴግ በመለስ አስከሬን ቢዝነስ እየሰራ ነው፣ ንግድ ነው የያዘው”  በማለት አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ጋዜጠኛ ለኢሳት ገልጿል። ” 6 ሚሊዮን ቅጅ በመቶ ብር ከተሸጠ 600 ሚሊዮን ብር ይሆናል። ይህ አሀዝ ኢህአዴግ ለመለስ ለቅሶ ያወጣውን ዋጋ ሸፍኖ እጅግ በርካታ ትርፍ ያጋብስበታል፣ ፓርቲው በመለስ ስም  የኢትዮጵያን ህዝብ እየዘረፈ ነው፡ ” ሲል ጋዜጠኛው አክሏል ።
        መጽሄቱን በግድ እንዲገዛ የተገደደ በጎንደር ከተማ የሚኖር ነጋዴ ደረሰኙ የብአዴን መሆኑንና “የብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ድርጅትን ማጠናከሪያ የሚውል” የሚል አረፍተ ነገር እንዳለበት ተናግሯል።
        በአዲስ ራእይ ስም የሚገኘው ገንዘብ ለአራቱ ድርጅቶች ሊካፈል እንደሚችል መረጃዎች ጠቁመዋል።  መጽሄቱን የሚያትመው የህወሀት ኩባንያ የሆነው ሜጋ አሳታሚ ድርጅት ነው። ህወሀት ለትግራይ ኮታ ከተመደበው ሽያጭ ብቻ ሳይሆን በሜጋ ማሳተሚያም በመጽሄቱ ሽያጭ ከፍተኛ ገንዘብ ያጋብሳል ተብሎ ይታመናል ።

          የለገጣፎ/ለገዳዲ ነዋሪዎች አዲሱን ከንቲባ አንቀበልም አሉ


          ከመሬት ዝርፊያ ጋር በተያያዘ የከተማው ነዋሪዎች ያሰሙትን ከፍተኛ ተቃውሞ ተከትሎ በቅርቡ ከንቲባውን አቶ መገርሳ ገለታን ጨምሮ 5 የካቢኔ አባላትን ከስልጣን ያወረደው መንግስት፣ ከአካባቢው ህዝብ ያልተመረጠ አዲስ ከንቲባ በመሾም ለህዝቡ ለማስተዋወቅ የጠራው ስብስባ በተቃውሞ እንዲበተን ተደርጓል።
          ህዳር 21 ቀን 2005 ዓም ከፍተኛ የኦህዴድ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ቀነአ ኩማ የለገጣፎ ለገዳዲን ህዝብ በመሰብሰብ አዲስ ተሾመው የመጡትን አቶ አለማየሁ ውለታን ለማስተዋወቅ ሲሞክሩ፣ ህዝቡ ” ከንቲባ የሚመረጠው ከምክር ቤት ነው፣ ምክር ቤቱን የመረጥነው ደግሞ እኛ ነን፣  እናንተ ያመጣችሁልን ከንቲባ እኛ ያልመረጥነው ነው፤ ባልመረጥነው መሪ አንደራደርም ፣ ባልመረጥነው መሪም አንመራም።” በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል።
          የመንግስት ባለስልጣናት አዲሶቹን ተሿሚዎች አንቀበልም ካላችሁ ከጀርባችሁ የፖለቲካ ድርጅቶች አሉ ማለት ነው፣ ብትቀበሉ ይሻላችሁዋል በማለት ለማስፈራራት ቢሞክሩም ህዝቡ ግን አሻፈረኝ ብሎአል።
          ህዝቡን ይበልጥ ያስቆጣው ደግሞ ሌላው በሙስና ተገምግመው የወረዱት ምክትል ከንቲባው ተመልሰው ወደ ቦታቸው እንዲቀመጡ መደረጉ ነው። የፍትህ ሚ/ር ፣ ሚ/ር ዲኤታ የሆኑት አቶ ብርሀኑ ጸጋየ የቀድሞው ከንቲባና ባልደረቦቹ በህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ገልጸው የነበረ ቢሆንም፣ በግለሰቦቹ ላይ እስከአሁን ምንም አይነት ክስ አለመቅረቡም ነዋሪውን አበሳጭቷል።
          በከተማው ነዋሪና በመንግስት መካካል ያለው ውዝግብ አሁንም እንደቀጠለ ነው።
          ከአዲስ አበባ ከተማ በሰሜን ምስራቅ በኩል 21 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው የለገጣፎ/ለገዳዲ ከተማ በኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ ልዩ ዞን ሥር በከተማ አስተዳደርነት እንድትመሰረት መደረጉ ይታወሳል፡፡በአሁኑ ሰዓት ከተማዋ 2ሺ431 ሄክታር የመሬት ስፋት ያላት ሲሆን የተዋቀረችውም በሁለት ቀበሌዎች ነው፡፡የከተማው ማዘጋጃ ቤት ባሳተመው ብሮሸር የህዝብ ብዛቷ ከ18 ሺ እንደሚበልጥ ቢገልጽም የከተማው አስተዳደር ከንቲባ ቁጥሩ ከአምስት ሺ እንደማይበልጥ መናገራቸውን ሰመጉ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ መጥቀሱ ይታወሳል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ ከሕዝቡ ቁጥር በላቀ መልኩ ወደሃያ ሺ የሚጠጋ ካርታ በከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ከሌላ አካባቢ ለመጡ ሰዎች መሰጠቱ የአካባቢው ነዋሪዎች በቅሬታ መልክ እንደሚያኑሱም በመግለጫው መጠቀሱ ይታወሳል።

          መንግስት የህዝብን ብሶት አልሰማ ብሎአል ሲሉ ፕሮፌሰር በፈቃዱ ደግፌ ተናገሩ


          ታዋቂው የኢኮኖሚክ ባለሙያ የሆኑት ፕ/ር በፈቃዱ ደግፌ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ መንግስት የህዝብን ብሶት አልሰማ በማለቱ አንድ ቀን ያልጠበቀው አደገኛ ሁኔታ ሊፈጠርበት እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ” ህዝቡ የሚሄድበት ቦታ አጥቷል፣ ብሶታል” ያሉት ፕ/ር በፈቃዱ ከአረብ አብዮት የምንማረው ህዝብ መሪ ሳያስፈልገው በብሶቱ ብቻ ሆ ብሎ ሊነሳ የሚችል መሆኑን ነው ሲሉ ገልጸዋል።
          በኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ቃለ ምልልስ የሰጡት ፕ/ር በፈቃዱ ደግፌ የኢትዮጵያ ባለቤት የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ኢህአዴግ ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለሙስና ስራ መስራት እንደማይቻል የገለጹት ፕሮፌሰሩ፣ ጉቦ ባይኖር ኖሮ ይህ አገር አይኖርንም ነበር ሲሉ በአገሪቱ የተስፋፋው ሙስና የደረሰበትን ደረጃ አመላክተዋል።
          ሙስናን ለማጥፋት በህግ የሚተዳዳር፣ በህግ የሚገዛ መንግስት መኖር እንዳለበትም ፕ/ር በፈቃዱ መክረዋል።
          ምንም እንኳ ለእድገት የሚያስፈልጉ መሰረተ-ልማቶች ቢሰሩም፣ የህዝቡ ኑሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መሄዱን ፕሮፌሰሩ  ተናግረዋል። “ህዝቡ ቀጭጯል፣ የሚበላው   የለውም ” ያሉት ፕ/ር በፈቃዱ፣  መንግስት ለግብርናው ዘርፍ ትኩረት በመስጠት የህዝቡን የምግብ ፍላጎት ማርካት እንዳለበትም መክረዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው የዋጋ ግሽበት በዋናነት ከገንዘብ ፖሊሲ ጋር የተያያዘ ነው የሚለውን ለመቀበል እንደሚቸግራቸው የገለጹት ፕ/ር በፈቃዱ፣ በእርሳቸው እምነት የዋጋ ግሽበቱ ዋነኛው መንስኤ በአገሪቱ ውስጥ በቂ ምርት አለመመረቱ ነው ።

            Tuesday, December 4, 2012

            Tigrai Rep. officially disowns the indomitable lion of Dogali, Ras Alula


            The Horn Times Newsletter, Dec 2, 2012

            By Getahune Bekele  “ The great Abyssinian chief Ras Alula is at present a person of much interest to the Italians, and the Reforma is publishing a sketch of his life, in the course of which it is stated that he is the son of Abyssinian peasants.”

            The Paul mall Gazette, April 12, 1887
            “Ras Alula developed great military skill, and for many years was regarded as one of the greatest Abyssinian Generals.”
            The New York Times, Feb 27, 1879
            Eritrean born top TPLF warlord Bereket Simeon is currently on a new mission alongside another anti-Ethiopian hireling Sibehat Nega, an Ignoramus who regards Ethiopia’s rich history as an offence that should be erased.
            Few days after the ruling minority junta announced the pending removal of statues of martyred bishop Abune Petros and emperor Menilik, Tigraye republic officially disowned her own anti- colonial war hero, Ras Alula Engida (pictured) by removing the obelisk which commemorates the battle of Dogali from the only school named after him in his home province of Tigraye, Tembein zone of Abi-Adie town.
            According to the Horn Times Tigrai zone reporters, the up graded and modernized high school was renamed “Meles Zenawi comprehensive high school” on November 21, 2012.
            Speaking at the ceremony, TPLF cc member commander Yetbarek Aleneh told the visibly unhappy crowd that “ those who call  themselves opposition parties  must worship Ras Alula in Addis Ababa or Asmara…or even in Washington Dc, where they live as fugitives…not here in Tigraye. We have created a new Tigrai with the blood of our children, not with Alula’s blood.”
            However, after the ceremony, a miner scuffle broke out between armed TPLF security personnel and the residents of Abi-Adie town who strongly objected to the name change and threatened to burn down the school.
            Several arrests were made
            Ras Alula, the gallant military commander who historians usually compare to Hannibal of the ancient Cartage, was born
            Ras Alula, the gallant military commander
             near the town of Mekele, the capital of Tigrai and became a household name when he ambushed an Italian battalion of 500 men, led by Colonel Tommaso De Cristofori, in Dogali near the port city of Massawa, present day Eritrea, on 26 January 1887 and killed almost all the invaders in just few hours of fierce battle.

            His huge statue topped with a red star was erected in Dogali during the communist rule in Ethiopia and January 26 used to be a national holy day before TPLF came to power in May 1991.
            Nevertheless, Ras Alulas’ monument was blasted by EPLF, Eritrean People’s Liberation Front (shabia) commander Petros Solomon in 1989 in the presence of the late fuehrer Meles Zenaw’s father, Ato Zenawi Asres, a traitor who fought alongside the Italians during the second Italo-Abyssinian war.
            To the 500 Italians killed by the patriots, the massive monument erected in their honor is still standing in Rome’s famous Piazza Dei Cinquecento while TPLF warlords, who descended from families of traitors, try to destroy Ethiopia’s own war memorials.
            Furthermore, despite the juntas vile attempt to eradicate history, in the pristine smoggy ravines of the north, the golden belt of Ethiopian patriotism, shepherds are singing about the heroics of this gallant soul called Ras Alula Aba-Nega…as they did for generations…
            “He is as fair as angel,
            And strong as a lion,
            Swift-footed as a leopard,
            Sly as a fox,
            Wise as Solomon,
            Generous as a king,
            Is most valiant of all,”

            Monday, December 3, 2012

            ሰማያዊ ፓርቲ የአቡነ ጴጥሮስን ሀውልት መፍረስ ተቃወመ


            ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ማንኛውም ልማት ወጪን ቆጣቢ ሆኖ መሰራት እንዳለበት የሚታመን ቢሆንም በዋጋ ሊተመኑ የማኢችሉ ቅርሶችን በማጥፋት ግን ወጪን ለመቀነስ ማሰብ የእብደት አስተሳሰብ ነው ብሎአል።
            የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌታሁን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ  ኢህአዴግ ከፍ ብሎ ለመታየት ባለው ፍላጎት የተነሳ ከዚህ በፊት የተሰሩትን ስራዎች ሁሉ ለማሳነስ እንደሚሞክር ገልጠው፣ የአቡነ ጴጥሮስን ሀውልት ለማፍረስ ቀድሞውን ነገር መታሰብ አልነበረበትም ብለዋል
            የመንግስት ባለስልጣናት የአቡነ ጴጥሮስን ሀውልት ለማፍረስ ሲወስኑ አጥር እንደማፍረስ አድረገው እንደቆጠሩት የተናገሩት አቶ ይልቃል ፣ ህዝብ ባይጮህ ኖሮ መልስ ለመስጠትም አይፈልጉም ነበር ብለዋል
            የግራዚያኒ ሀውልት ጣሊያን ውስት ሲሰራ በዛው ሳምንት የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት መፍረሱ የታሪክ ምጸት ነው በማለት የመንግስትን የታሪክ አረዳድ አቶ ይልቃል ተችተዋል
            ይህ በእንዲህ እንዳለ ሉሲ በመጪው የፈረንጆች አመት አጋማሽ ላይ ወደ ኢትዮጵያ እንደምትመለስ መንግስት አስታውቋል።
            የህወሀት/ኢህአዴግ ንብረት የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ እንደዘገበው  የ5 ዓመታት ቆይታ ለማድረግ ወደ አሜሪካ ያመራው የሉሲ ቅሪተ አካል በመጪው የፈረንጆች ዓመት አጋማሽ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳል።
            ቅሪተ አካሉ ከመመለሱ በፊት የመጨረሻ ኤግዚቪሽኑን በካሊፎርኒያ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ራዲዮው ዘግቧል።
            በመጪው የ2013 የፈረንጆች አመት አጋማሽ ላይ ከሉሲ ጋር አብረው የሄዱትን ፥ ሌሎች 149 ቅርሶች በተሸኙበት መልኩ በጥሩ ሁኔታ ለመቀበል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ደስታን ዋቢ አድርጎ ራዲዮው ዘግቧል
            ከሉሲ ጉብኝት የሚገኘው ገንዘብ በፕሮጀክቱ ስም በተከፈተው አካውንት ገቢ በመደረግ ላይ መሆኑንና ፥ ፕሮጀክቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ሙዚየሞችን ለማሳደግና ለማስፋፋት እንደሚውል ራዲዮው ዘግቧል።
            ይሁን እንጅ የሉሲ አጽም ትክክለኛው ይመለስ ቅጅው አይታወቀም። በሉሲ አማካኝነት ስለተገኘው ገንዘብ ዝርዝር ማብራሪያም አልተሰጠም። ራዲዮው  በሚቀጥለው የፈረንጆች አመት አጋማሽ ላይ አለ እንጅ በየትኛው ወርና ቀን ሉሲ ወደ አገሯ እንደምትመለስ አልተገለጸም።

            Obama Africa policy must change to help get rid of Dictators


            Don’t blame me, I didn’t vote for Obama

            President Obama must change the policy of looking at Africans as expandable for the adventure of his Administration’s officials-bandaged with foreign aid to dictators. His Administration policy must come to its senses to understand Africans had it with the policy of delaying their liberties by coddling up with tyrants of Africa.
            by Teshome Debalke
            In the last hour of Election Day I decide not to vote for anyone of the two candidates offered.  Don’t get me wrong, I like
            Don’t blame me, I didn’t vote for Obama. African dictators must go.
            Obama’s personality and most of his first campaign promises and voted for him in the first round. He was convincing and seems visionary enough to take the country and the world in the next century.  I was impressed with his desire to bring people together for a higher cause than petty politics unlike his competitors from both sides of the political divide. His promised foreign policy was even more impressive; choosing diplomacy over confrontation, democracy over tyranny, economic development over corruption and poverty… on and on.

            But, the second time around was different. I had the opportunity to look at his records. As good as some of his domestic policies under the circumstances he faced he failed my final test; principle over politics, especially when it involves the lives of people under authoritarian regimes in Africa and elsewhere.  His promises didn’t translate to deeds in the last four years of his first term to make my decision easier not to vote for him.
            Look, if it wasn’t for the clumsy Mitt Romney campaigning as if he is used car salesman and his party (The Republican Party) acting as an intoxicated fraternity house in college campus than a national party with serious work ahead for the country I would have voted for the Republican ticket. So, my vote was wasted this time until a better candidate shows up in the next round where word matches deeds and principle override political rhetoric-when it comes to important issues of democracy and liberty. After all, the very democracy and library of America’s future depends on it.
            I never vote for someone because s/he looks like me by race, creed, gender, sex or if s/he came from the same region or worship the same religion. It is too primitive to think in terms of our natural similarities we have no control over or what we choice to worship.
            As Martin Luther King Junior, the greatest moral leader America produced in the last century I believe the content of a person’s character weighs in big in my decision to vote for someone or not and do anything that matters. After all, everybody seems to be cute in public but short on substance in private. What matters for me is the principle one stand for when nobody is looking.

            Peaceful and Armed Struggles: They Are Not Necessarily and Mutually Exclusive or Inclusive


            Commentaryby T.Goshu

            This very brief commentary of mine is just to reflect a few points of view on the question of peaceful or armed struggle as

            TPLF to take down Ethiopian flag in San Jose
             methods of achieving a political goal set by opposition force (s) in Ethiopia.  In other words, the very challenging question is whether to apply peaceful or armed; or the combination of the two based on a given internal political reality, and external circumstance. Needless to say, this had been and continues to be an unavoidable challenge in a country like ours which has never experienced a political transformation characterized by a well- thought, well-planned, well-organized and persistent popular uprising and disobedience in line with the fulfillment of the interests of the general public. Let me make clear myself here that it is neither my interest nor intention to discuss this very deep and complex subject matter in length. But I strongly believe that it would be great if intellectuals and other genuinely concerned Ethiopians could come forward with their own critical views and solution-oriented recommendations, and help the people how to deal with this seemingly very argumentative issue.

            I sincerely believe that we should be seriously concerned about our tendency of approaching the question of which method of political struggle should we apply in a very categorically defined fashion. In other words, the argument of either exclusiveness or inclusiveness is not only undesirable but it is also distractive as far as the huge and deep political challenge we are facing is concerned.
            Although raising the question of how to approach a given political struggle that aims at the realization of a democratic political system has never been uncommon, its intensity and urgency   varies from time to time, and from situation to situation.  Because of our political culture which is characterized by mere inheritance, conspiracy within royal families and a bloody fight between or among groups (civil war), we are not yet fortunate enough to listen to each other’s arguments and counter- arguments in such a way that our differences on using not the same tactics or methods should not hamper our journey toward the same goal

            Sunday, December 2, 2012

            TPLF Manifesto, Amhara was labeled as #1 enemy of Tigray


            “The forgotten people” Why is the Ethiopians’ blood so thin? 

            TPLF Manifesto Amhara was labeled as number 1 enemy of Tigray
            Mekonnen Workineh, Norway, Nov 2012
            Writer from Norway, Mekonnen Workineh
            Mekonnen Workineh
            Analogously ,  the Nazi manifesto of 1920 was anti-Semiticanti-capitalistanti-democraticanti-Marxist, and anti-liberal.
            Anti-Semitic was number one manifesto of Nazi Hitler and Anti-Amhara is number one manifesto of TPLF.
            Hitler murdered 6 Million Jews. What happened 60 years ago is still fresh in the minds of Jews and is still haunting Germans, especially those whose family members were involved. Nazi criminals are still being hunted around the world and being brought to justice.
            TPLF murdered more than 8 Million Ethiopians to date (G/Medhin 
            TPLF Manifesto Amhara was labeled as enemy of Tigray
            Araya, former TPLF financial head). In the 2007/2008 senses 2.5 Million Amharas perished into the thin air;http://ethioskytv.com/view/570/25-million-amharas-missing-confirmed-in-parliament-part-1.html . Ethiopia has been under siege for the last 21 years by TPLF backed by the European Union, USA, and the United Kingdom. 1000s of Anuakes residences were red labeled and were massacred in a day light by this regime. Ogaden region was curtailed from international eye and mass murder, gang rape and  torture crime is being committed by this same regime( http://www.genocidewatch.org/ethiopia.html) , tens of thousands of Oromos,  the majority group of the country, are languishing in jail all over the country. Tens of thousands are being evicted even this time, TPLF regime is dehumanizing the Ethiopian people, torturing and committing savage crime against poor farmers, elders and children. Involved in human trafficking crime,

            Hundreds of thousands are leaving the country every year, thousands dying in the desert, drawing in seas and rivers, facing abuse, prison and death in Middle East, queuing  in front of immigration offices around the world, crowding foreign prisons, the list of ordeal could go for days.  When will the international community open its eyes and see what is happening to Ethiopian people.
            Why do Ethiopians go exile?  Because Ethiopia is poor?  Because Ethiopians are not hard working? Because Ethiopia does not have natural resources to feed its people?
            The answer to all the above questions is NO
            The reason for all this is administration problem. Billions of dollars is flying out of the country illegally 11.7 Billion until 2009 (, http://danielberhane.com/2011/12/22/ethiopia-the-illicit-financials-outflow-in-perspective/).
            Fertile land of Ethiopia is being given away almost for nothing; Multinational corporate brag of feeding the world from Gambella region alone.
            True Ethiopian people are weak at this time; True TPLF is strong with the help of the west in the name of stability. But how long will that last, why and how did Ruanda genocide happened?  What was the recipe for that? What is the guarantee that such thing would not be repeated in Ethiopia if pushed to the edge? How long does iron fist last?
            I urge all international community specially the Obama administration, the Cameroun administration, the European Union, to stop propping minority ethno centric fascist regime to undermine Ethiopian people.
            Victory for Ethiopians!
            Contact me: Mekonnen_32@yahoo.com

            Ethiopia: Open Letter to President Barack H. Obama

            The Hon. Barack H. Obama
            President of the United States of America,The White House
            Washington DC,November 29, 2012
            Mister President,
            In view of your long standing concern for Human Rights, the Rule of Law and the profound inequities prevailing around the World, I would like to bring to your attention the terrible plight of human and social economic conditions in Ethiopia.

            The US State Department Human Rights 2011 report on Ethiopia states:

            Human rights abuses reported during the year included unlawful killings, torture, beating, and abuse and mistreatment of detainees and opposition supporters by security forces, especially special police and local militias, which took aggressive or violent action with evident impunity in numerous instances; poor prison conditions; arbitrary arrest and detention, particularly of suspected sympathizers or members of opposition or insurgent groups; detention without charge and lengthy pretrial detention; infringement on citizens’ privacy rights, including illegal searches; use of excessive force by security services in counterinsurgency operations; restrictions on freedom of speech and of the press; arrest, detention, and harassment of journalists; restrictions on freedom of assembly and association; restrictions on freedom of movement; ruling party intimidation, threats, and violence during the elections; police, administrative, and judicial corruption; harassment of those who worked for human rights organizations; violence and societal discrimination against women and abuse of children; female genital mutilation (FGM); exploitation of children for economic and sexual purposes; trafficking in persons; societal discrimination against persons with disabilities and religious and ethnic minorities; forced labor and child labor; and government interference in union activities.

            The Ethiopian Human Rights Council, Amnesty International, Genocide Watch and many other reputable organizations have reported irrefutably of these crimes. Since then and even after the change of leadership these conditions have not changed. In fact they have worsened due to the progressive faltering authority of the regime and growing discontent amongst the population. Coercive measures that pit ethnic, religious and cultural communities against each other are being deliberately carried out by interfering in their organizations and practices. For instance, Muslim communities are being harassed; their members arrested and persecuted.

            Raw Video Footage: Government brutality in Ethiopia