Saturday, December 8, 2012

በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ የንብረት ውርስ ላይ ትእዛዝ ተሰጠ


ከፍተኛው ፍርድ ቤት በ1ኛ ተከሳሽ በአቶ አንዷለም አራጌ ባለቤት ስም የተመዘገበው የቤት መኪና ፤ በ7ኛ ተከሳሽ አቶ እስክንድር ነጋ ስም የተመዘገበ 1 ቤትና ከእናታቸው በውርስ ያገኙት ተዳምሮ 2 መኖሪያ ቤቶች እና በባለቤታቸው ስም የተመዘገበ 1 የቤት መኪና ፤ እንዲሁም በሌሉበት በተከሰሱት በ16ኛ ተከሳሽ በአቶ አበበ በለው ባለቤት ስም ፥ የተመዘገበ መኖሪያ ቤት ላይ የቀረበውን የውርስ አቤቱታ ያደመጠ ሲሆን አቶ አንዱአለም ባለቤት በጠበቃቸው አማካኝነት መኪናዋ ልጆችን ትምህርት ቤት የምታመላልስ መሆኗን ጠቅሰዋል።  የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ወ/ሮ ሰርካለም ፋሲል ችሎት ቀርበው እንዳማይከራከሩ በችሎቱ ላይ ተገልጿል።
የ አቶ አበበ በለው  ባለቤትም ችሎት ስላልቀረቡ ለታህሳስ 18 መጥሪያ ደርሷቸው ችሎት እንዲገኙ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት ለታህሳስ 18 ቀን 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙ ታውቋል

No comments:

Post a Comment