Friday, December 7, 2012

በትግራይ ክልል ህወሀትን አትደግፉም የተባሉ ዳኞች እየታሰሩ ነው


በክልሉ የሚገኙ ዳኞች ለኢሳት እንደገለጹት በቅርቡ በክልሉ ከፍተኛ ግምገማ በመካሄድ ላይ ሲሆን አመለካከታቸው ከመለስ ራእይ ውጭ ነው የተባሉ ዳኞች ተይዘው ታስረዋል። ድምጻቸው እንዳይተላለፍ የጠየቁ ዳኞች ለኢሳት እንደገለጹት  በውቅሮ ከተማ ውስጥ በተደረገው ግምገማ 4 ዳኞች ታስረዋል።
አቶ መለስ ከሞተ በሁዋላ ሁኔታው ተባብሶ መቀጠሉን የገለጡት ዳኞች፣ ለምን የሚል ጥያቄ የሚያነሱ ዳኞች ድብደባ ሳይቀር ይደርስባቸዋል።
ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የሰሩ ዳኞች ሲሰለጥኑ 4 አመት ለማገልግል ከመንግስት ጋር ውል የተዋዋሉ በመሆናቸው ስራ ለመልቀቅ እና ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሄደው ለመስራት ተችግረዋል። ዳኞቹ ለመለቅቅ ከፈለጉ 36 ሺ ብር መክፈል እንዳለባቸው ዳኞች ተናግረዋል።
በክልሉ የሚገኙ መምህራንም በሚታየው የመብት አፈና እየተማረሩ መምጣታቸውን ለኢሳት ገልጸዋል።

    No comments:

    Post a Comment