Tuesday, December 18, 2012

ራሳቸውን ተበዳይ ኮሚዩኒተሮች በማለት የሚጠሩ የመንግስት የህዝብ ግንኙነት ሰራተኞች የተቀነባበሩ መረጃውን ለአለም ይፋ እንደሚያደርጉ አስጠነቀቁ


በአቶ በረከት ስምኦን በሚመራው የኮምኒኬሽን መስሪያ ቤት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ፣ መስሪያ ቤቱ የሚፈጽመውን አድሎአዊ አሰራር በመንቀፍ ለአቶ በረከት ስምኦን የጻፉትን ደብዳቤ ግልባጭ ለኢሳት ልከዋል።
በደብዳቤው  አቶ በረከት በሚመሩት መስሪያ ቤቱ ወስጥ በህዝብ ግንኙነት ስራ ላይ ተሰማርተው በሚገኙ ኮሚኒተሮች ላይ የሚፈጸመው አድሎ የማይቆም ከሆነ እንዲሁም ድብዳቤው የቀረበላቸው አቶ በረከት በተለመደ ንቀታቸውና ዝምታቸው የሚቀጥሉ ከሆነ ” በምስልና በድምጽ የተቀነባበሩ መረጃዎችን ለተለያዩ የውጭና የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች በመስጠትና ለህብረተሰቡ በማድረስ የምንቀጥል መሆኑን” ፣ እንዲሁም “እስከሚቀጥሉት 2 ሳምንታት መልስ የማይሰጠን ከሆነ ወደ ቀጣዩ የከፋ እርምጃ ለመሄድ እንገደዳለን።” ብለዋል።
በኮሚተር ሰራተኞች መካከል ያለው አድልኦ ቆሞ ሁሉም በእኩል አይን ታይተው አስፈላጊው ስልጠናና የደሞዝ ማስተካከያ የማይደረግላቸው ከሆነ ” በተከታታይ የሚወሰዱት እርምጃዎች እጅግ የከፉና እነሱንም ሆነ መንግስት ውድ ዋጋ የሚያስከፍሉ” እንደሚሆኑ ሰራተኞች ጠቅሰዋል።
የህዝብ ግንኑነት ሰራተኞች ስራ ለማቆም አድማ እንደሚጠሩና ከስራ እንደሚለቁ ለአቶ በረከት በጻፉት ደብዳቤ ላይ ገልጸዋል።
ሰራተኞቹ የአቶ በረከት መስሪያ ቤት ለተወሰኑ የህዝብ ግንኙነት ሰራተኞች ስልጠና እየሰጠ ልዩ ደሞዝ ይከፍላል በማለት ወቀሳ አቅርበዋል።
ሙሉውን ደብዳቤ በኢሳት ድረገጽ ላይ እንዲመለከቱ እንጋብዛለን።

    No comments:

    Post a Comment