Thursday, December 20, 2012

አራት የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የ 2112 ትን ዓለማቀፍ የሄልማን ሽልማት አሸኛፊ ሆኑ


የሄልማንን የክብር ሽልማት ያሸነፉት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች፦ በእስር ላይ የሚገኙት እስክንድር ነጋ፣የአውራምባ ታይምሱ ውብሸት ታዬ፣የፍትህ አምደኛዋ ርዕዮት ዓለሙ እና በስደት የሚገኘው የአዲስ ነገሩ መስፍን ነጋሽ ናቸው።
በሂዩማን ራይትስ ዎች አማካይነት የሚሰጠውን ይህን የክብር ሽልማት ያገኙት አራቱም ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ መንግስት የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸዋል።
አጠቃላይ ለዘንድሮው የሄልማን ሽልማት የበቁት ከ19 አገራት የተውጣጡ 41 ጋዜጠኞች ሲሆኑ፤ለሽልማት የበቁትም ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አስቸጋሪ በሆኑባቸው አካባቢዎች ሙያቸውን ለመተግበር መስዋዕትነት በመክፈላቸው እንደሆነ ተመልክቷል።
በሂዩማን ራይትስ ዎች አማካይነት የሚዘጋጀው  የሄልማን ሽልማት ሀሳባቸውን  በመግለፃቸው ሳቢያ የፖለቲካና የሰብዓዊ መብት ጥቃት ለሚፈጸምባቸው በዓለም ዙሪያ ላሉ ጋዜጠኞችና ጸሀፊዎች በየዓመቱ የሚሰጥ ነው።

    No comments:

    Post a Comment