Monday, December 31, 2012

በአማራ ክልል 500 ፖሊሶች ስራቸውን ለቀቁ


ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው በክልሉ በአንድ አመት ውስጥ ብቻ 500 ፖሊሶች ስራቸውን ለቀዋል። ፖሊሶች ስራቸውን መልቀቃቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በአንድ ስብሰባ ላይ አምነዋል።
ፖሊሶች ስራቸውን የለቀቁት በአስተዳደር ጫና እና ከስራቸው ጋር የማይጣጣም እና የኑሮ ውድነቱን ለማቋቋም የማያስችል ክፍያ ስለማይከፈላቸው መሆኑን ይገልጻሉ።
በክልሉ ውስጥ የሚታየው የኑሮ ውድነት ፖሊሶችን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የመንግስት ሰራተኞችን እያስመረረ መምጣቱን ለኢሳት የሚደርሱት መረጃዎች ያመለክታሉ። በዚህ የኑሮ ውድነት ላይ ለአባይ ግድብ ማሰሪያና ለትራንስፎርሜሽን እቅዱ ማሳኪያ በሚል ሰራተኞች መዋጮ እንዲከፍሉ መገደዳቸው ኑሮአቸውን የከፋ እንዲሆን እንዳደረገው ሰራተኞች ይገልጻሉ።

    No comments:

    Post a Comment