ጋዜጠኛ አበበ ገላው ሞረሽ በመባል የሚታወቀው የአማራ ብሄርን መሰረት አድርጎ በቅርቡ የተቋቋመ ድርጅት ያወጣው መግለጫ አልተስማማኝም አለ።
አበበ ገላው በፌስቡክ ገጹ ላይ ጉዳዩን እንደሚከተለው ገልጾታል፣
“ሞረሽ ጋዜጠኛ አበበ ገላውን ለመግደል የተደረገው ሙከራ፣ የወያኔ ዐማራን አድኖ የማጥፋት ዘመቻ አካል ነው አለ::” ዘሃበሻ
ሞረሽ ስለሚባለው ድርጅት ብዙ የማውቀው ነገር ስለሌ ስለ መግለጫው አላማ ብዙም የምለው ነገር የለም። መልእክቱ ግን በፍጹም አልተስማማኝም። መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በህወሃቶች እየታደነና እየተሰቃየ ባለበት በዚህ የመከራ ግዜ ሁላችንንም በአንድነት የሚያንቀሳቅስ አላማ ያስፈልገናል። ከሁሉ በላይ ግን ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ከዘር በላይ ኢትዮጵያዊነታችን መገለጫችን ነው። እኔ በበኩሌ የምሰዋለትና የምታገልለት ዘር ፈጽሞ የለኝም። እኔ በኩራት የምሞትላት ኢትዮጵያ የምትባል ታላቅ አገር አንዲሁም ኢትዮጵያዊ የሚባል ታላቅ ህዝብ መሆኑን ገልጽ ሊሆን ይገባዋል። ዘሬ ኢትዮጵያዊነት ስለሆነ የዘር ፓለቲካ አዙሪት ውስጥ ፈጽሞ መግባት አልሻም።
No comments:
Post a Comment