በጋዜጠኛና አክቲቪስት አበበ ገላው ላይ ሊቃጣ የነበረውን የግድያ ወንጀል ተከትሎ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኖርዌይ ጥገኝነት ጠይቀው የሚኖሩ የመንግስት ሰላዮችን ለማጋለጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ ቆርጠው መነሳታቸውን ለኢሳት በላኩት መግለጫ አስታውቃል።
“በአበበ ገላው ላይ ሊሰነዘር የነበረው የግድያ ወንጀል በኤፍቢአይ መርማሪዎች መክሸፉ ቢያስደስተንም፣ በስደት፣ ዲሞክራሲና ነፃነት በሰፈነበት አገር ወያኔዎች እንዲህ አይነት አስከፊ ወንጀል ለመፈፀም ማሰባቸው እጅግ አስቆጥቶናል፤በጣምም አበሳጭቶናል” በማለት ኢትዮጵያኑ ስሜታቸውን ገልጸዋል።
በኖርዌይ በተለያዩ አጋጣሚዎች የመንግስት ሰዎች ለነፃነት፣ለዲሞክራሲና ለፍትህ በሚታገሉና በኖርዌይ በሚገኙ ወገኖች ላይ በአካል፣ በስልክ፣በኢ-ሜይልና በሌሎች መንገዶች ዛቻና ማስፈራሪያ ማድረጋቸውን ያስታወሱት ኢትዮጵያኑ፣ ለወደፊቱ እንዲህ አይነት ሁኔታ እንዳይከሰት ፀረ ዲሞክራሲና ኢሰብአዊ ድርጊት ፈፃሚዎችን አጋልጠው በማውጣት ህጋዊ ምርመራ እንዲደረግባቸው እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
ከዚህ በፊት በተለያዩ የዜና አውታሮች እንደተዘገበው ወደ ኢትዮጵያ መመለስ የማይችሉና የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ ተደርጎባቸው በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በኖርዌይ መኖራቸው ይታወቃል፡
No comments:
Post a Comment