አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለ ቦታ ባደረገው ውጊያ 14 የጠላት ወታደሮችን በመግደልና 12 በማቁሰል ከፍተኛ ወታደራዊ ድሎችን በማስመዝገብ ግንባሩ የተሰማራበትን ግዳጅ በድል እየተወጣ መሆኑን የግንባሩ ወታደራዊ መምሪያ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዘራፊውና ከነፍሰ-ገዳዩ የወያኔ አምባገነናዊ ገዥ ቡድን ለማላቀቅ ያለው ብቸኛ አማራጭ መንገድ በትጥቅ ትግል ስርዓቱን ማንበርከክ መሆኑን ጠንቅቆ ያወቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ሀገርንና ወገንን ለመታደግ ቆርጦ በመነሳት በሰሜኑ የሐገራችን ክፍል ወታደራዊ ስትራቴጅውን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ሰሞኑን አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለው ቦታ ባደረገው የማጥቃት ዘመቻ 26 የጠላት ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ወታደራዊ የበላይነትን የተቀዳጀ ሲሆን፣ ከሞቱት 14 የልዩ ሃይል ታጣቂ ቡድን መካከል አበበ የሚባለው የቀራቅር ተወላጅና አለልኝ የሚባል የደባርቅ ተወላጅ የሆኑት ከፍተኛ አመራሮች መሞታቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ወታደራዊ መምሪያ ገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለ ቦታ በፈፀመው ወታደራዊ የማጥቃት ዘመቻና በጠላት ላይ ባደረሰው ከፍተኛ ኪሳራ የተደናገጠው የወያኔ ቡድን ተጨማሪ ጦር ወደ አካባቢው እያጓጓዘ መሆኑንም ከአካባቢው የተሰራጩ የዜና ምንጮች አጋልጠዋል።
ይሁን እንጅ በዓላማቸው ፅናትና በሐገራዊ ፍቅር የተገነባው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በጀመረው ሕዝባዊና ሐገራዊ ተልዕኮ የፈረጠመ ክንዱን በጠላት ላይ በማሳረፍ አይበገሬነቱንና ቁርጠኝነቱን ሰሞኑን በተከታታይ ባደረጋቸው ውጊያዎች አስመስክሯል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
በመጨረሻም ውጊያው በተፈፀመባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት የጀመረውን ወታደራዊ የማጥቃት ዘመቻ አጠናክሮ እንዲገፋበትና እኛም የተለመደውን ሁለንተናዊ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር ግንባሩን ለመቀላቀል የሚያስችል መነሳሳትን የፈጠረ አኩሪ የአርበኝነት ገድል መፈፀሙን ነዋሪዎች አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በበኩሉ በስልጣን ላይ ያለው ፀረ-ሕዝብና ፀረ-ኢትዮጵያ ወንጀለኛ የወያኔ ቡድን የመጨረሻ ግብዓተ-መሬቱ እስኪፈፀም ድረስ ወታደራዊ የማጥቃት ዘመቻውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፆ የአገዛዙን እድሜ ለማሳጠርም የተለመደው ሕዝባዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለመላው ነፃነት ናፋቂና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሀገራዊ መልዕክቱን አስተላለፏል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር
No comments:
Post a Comment