Wednesday, January 16, 2013

አበበ ገላው፣ ሄኖክ ሰማእዝጌር እና የቪኦኤ ቃለ-ምልልስ


ECADF – ሰሞኑን የወያኔ ነብስ ገዳዮች አበበ ገላውን ለመግደል ሲያሴሩ FBI እንደደረሰባቸው መሰማቱን ተከትሎ የቪኦኤው ጋዜጠኛ ሄኖክ ሰማእግዜር ጋዜጠኛ አበበ ገላውን እና

Henok Semaegzer Fente, VOA Amharic journalist
 የሴራውን ጠንሳሽ ግለሰብ በቪኦኤ አቅርቦ ነበር።

ቃለ-ምልልሱ ከመጀመሩ ሄኖክ ሰማእዜር ሆን ብሎ “የመግደል ሙከራ” እያለ መናገርን መረጠ… ጋዜጠኛ አበበ ገላው ያገኘውን አጋጣሚ ተጠቅሞ የቪኦኤውን ጋዜጠኛ ለማረም ሙከራ አደረገ “በመግደል ሙከራ” እና “በመግደል ሴራ” መካከል ልዩነት እንዳለ አስረድቶ FBI ያከሸፈው እና አሁንም ምርመራ እያደረገ ያለው “በሴራው” ላይ እንጂ “በመግደል ሙከራ” ላይ እንዳልሆነ ለሄኖክ አስረዳው…
ይሁንና የቪኦኤው ጋዜጠኛ አበበ ገላው “የመግደል ሙከራ ተደረገብኝ ያለው ዉሸት ነው” የሚለውን መልዕክት ለማስተላለፍ ተዘጋጅቶ ስቱዲዮ በመግባቱ አበበ ገላው ደጋግሞ ጉዳዩ “ሴራ” እንጂ “የመግደል ሙከራ” እንዳልሆነ የነገረውን ጆሮ ዳባልበስ ብሎ አለፈው።
ይህን አስመልክቶ ጋዜጠኛ አበበ ገላው በፌስ ቡክ ገጹ ላይ የሚከተለውን አስፍሯል፣
የቪኦኤው “ጋዜጠኛ” ሄኖክ ሰማእግዜር በግንቦት 2004 (May 18, 2012) በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ላይ ያሰማሁትን ተቃውሞ ምንም እንዳልተፈጠረ አድርጎ በማቅረቡ ብዙ ተቃውሞ ገጥሞት እንደነበር ይታወሳል። በትናንትናው የቪኦኤ ዝግጅት ላይ ከኔ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ደግሞ ኤፍቢአይ በኔላይ የመግደል ሙከራ ስለ መቃጣቱ የማውቀው ነገር የለም አለ ብሎ ዘግቧል። በስፋት እንደተዘገበው እቅዱ ገና ጥስስ (plot) እንጂ ሙከራ ደረጃ ላይ አልደረሰም ። በሴራና በሙከራ መካከል ያለው ትልቅ ልዩነት ለማንም ግልጽ ግልጽ ነው። ይሄንኑ ግልጽ አድርጌለት የነበረ ሲሆን እርሱ ግን ሙከራ እያለ ሲደጋግም ሰማሁ። ይሄ ሲደጋገም ደግሞ በሰዎች ላይ የጥርጣሬ ስሜት ይፈጥራል። ምርመራውም ያተኮረው ሴራው ላይ እንጂ ሙከራ ላይ አይደለም። ሄኖክ ከኔ ጋር ችግር እንዳለው ግልጽ ይመስላል። ለጋዜጠኛ የማዛባት አባዜ አያዋጣውም። ስለ G8ቱ ስብሰባ ዘገባ የሰጠውን ቃለምልልስ መመልከት ይበቃል። ለምን ኢዮጵያዊያን በዘገባህ ላይ አቤቱታ አቀረቡ ተብሎ ሲጠየቅ (የመጨረሻው ጥያቄ) የሰላማዊ ሰልፈኞችን ቁጥር አሳንሃል ብለው ስለሚያስቡ ነው ነበር ያለው። ይገርማል! ከዚህ በሗላ ከሄኖክ ጋር ዳግም ቃለ ምልልስ አይኖረንም!!
የቪኦኤ ዘጋቢ ሄኖክ ሰማእግዜር በለውጥ አራማጅ ኢትዮጵያውያን ዘንድ እጅግ የተጠላ ጋዜጠኛ ሲሆን፣ የለውጥ አራማጅ ኢትዮጵያውያን ከዚህ በፊት የአሜሪካ ራድዮ ባለስልጣናት የሄኖክን ለገዢው (ወያኔ) ቡድን ማድላት እንዲያስቆሙላቸው ፊርማ (petition) ማሰባሰብ ይዘው እንደነበር አይዘነጋም።
አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ሄኖክ ሰማእግዜር ቪኦኤ ዉስጥ ወያኔዎች አስርገው ያስገቡት የጋዜጠኛ ካባ የደረበ ካድሬ ነው እስከ ማለት ይደርሳሉ።

No comments:

Post a Comment