ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ የትግል አቅጣጫውንና የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና የደህንነት ሀይሎች ለመንግስት ህዝብን የመጨቆኛ መሳሪያ መሆናቸውን አቁመው ከህዝብ ጎን እንዲቆሙ ጥሪውን አስተላልፎል::ታህሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ህውሀት ኢህአዴግ በህዝባችን ላይ የሚያደርሰው በደልና ግፍ ሊያበቃ ይገባል ያለው የሸንጎ መግለጫ በእስር ላይ ያሉት የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ባስቸኮይ እንዲፈቱም መንግስትን አሳስቦል::
አፋኝ የሆኑ የሚዲያና የሽብርተኝነት ህጎች በሙሉ እንዲሰረዙ ያሳሰበው የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ የመንግስት ሚዲያዎች ለምርጫ ግዜ ብቻ ለፕሮፓጋንዳ ሲባል የሚሰጥ ሽርፍራፊ ሰአት ቆሞ በመደበኛነት የተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚሳተፉበት እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል\::
የዲፕሎማቲክ የበላይነት በአንድ ወይም በሁለት ድርጅት ትግል እንደማይገኝ ያመለከተው የሸንጎ መግለጫ ለዘለቄታ ዲፕሎማሲያዊ የበላይነት ለመብቃት ጠቃሚ ስትራቴጂዎችን በመቀየስ ከሌሎች ሀይሎች ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አመልክቶል::
No comments:
Post a Comment