ኢሳት ዜና:-ከአረና የተላከው መረጃ እንደሚያመለክተው ፣ ወጣቱ የታሰረው በተከራየው ግቢ ውስጥ ነዋሪ የሆነችው የህወሓት አባል “በግቢያችን ፖለቲካ እየሰበክ ሌሎች ሰዎችን ወደ ዓረና ትግራይ ልትወስድ ነው በማለት ባነሱት ኣታካራ ” ነው።
ያለ ምንም መጥሪያና በቅርብ ይጠባበቁ የነበሩ ፖሊሶች ይዘዋቸው በመሄድ ዓዲ ሀቂ ፖሊስ ጣብያ በተባለ እስር ቤት አስረዋቸውል ይላል መግለጫው።
የዓረና ትግራይ የፅሕፈት ቤት ዶኩሜንትና የፅሕፈት ቤቱ ቁልፍ እንደተወሰደበት ፓርቲው ገልጿል።
ድርጊቱ በተፈጸመ ማግስት ፣ ህዳር 7 ቀን 2005 ዓም፣ የመቀሌ ዞን ፖሊስ ፅሕፈት ቤት ሓላፊዎች በፖሊስ ጣብያው ተገኝተው የዓረና ትግራይ ዶኩመንቶችን ይዘው መሄዳቸውን መግለጫው አክሎ ገልጿል።
ወጣት አምዶምን የከሰሱት ግለሰቦች ለፖሊስ ከሰጡት ቃል መካከል ‘ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞተው እኛ ስናለቅስ ዝም ብለዋል”በዚህም ተደስተዋል።” የሚል ይገኝበታል።
የዓረና ትግራይ ከፍተኛ ኣመራሮች በፖሊስ ጣብያው ተገኝተው ምንድ ነው ጥፋቱ በማለት ቢጠይቁም የጣብያው ኣዛዥ ፖሊስ ወታሃደር የሀይስ ” እኔ ቀስ ብየ ነው ጉዳዩን የማየው፣ ለምን ኣቀላጥፈዋለሁ “ተዘጋ ስላላችሁት ፅህፈት ቤትና ተዘረፈ ስላላችሁት ዶኩመንት እኔን ኣያገባኝም” የሚል መልስ መስጠቱ ተመልክቷል።
ወጣት ዓምዶም ገ/ስላሴ 2002ዓ/ም በተካሄደው ሃገራዊ ምርጫ ዓረና ትግራይን ወክለው በደጉዓ ተምቤን ወረዳ(ሃገረ ሰላም) የተወዳደረ ሲሆን ፣ በወቅቱ የዓረና ትግራይ ኣባል በመሆኑ ብቻ ጋዜጠኛ ሆኖ ይሰራ ከነበረ በህወሓት ንብረትነት ከሚታወቀው ድምፂ ወያነ ትግራይ መባረራቸውም የሚታወስ ነው
No comments:
Post a Comment